12/08/2026
ጄዛንዳ🤜🤛ዥማር!
ተቤት ቦጬም ቤት የዝጉጂ!
📢 7ኛው ዙር የጄዛንዳ ታላቅ የልማት እና የበጎአድራጎት ጥሪ! 🤝❤️
“ተቤት ቦጬም ቤት የዝጉጂ!” ❤️
አንድነት በቃል ብቻ ሳይሆን፣ በመገኘት፣ በመሳተፍና በአንድነት በመቆም ፕሮግራሙን እንሳተፍ !
የጄዛንዳ የልማትና የአንድነት ማህበር 7ኛው ዙር ታላቅ ልማት እና የበጎ አድራጎት የማህበረሰብ መርሃ ግብር በዚህ ዓመትም በድምቀት ይካሄዳል።
📅 እሁድ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም
📍 አረቅጥ ከተማ
🔥 ይህ ቀን ማንም የሚቀርበት ቀን አይደለም!
በእለቱ በርካታ አስደሳችና አነቃቂ ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ፦
🏆 ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት
🏆 የአቅም ውስንነት ላላቸው ተማሪዎች ሽልማት
🎓 በጠቅላላው 140 ተማሪዎች የሚሸለሙበት ልዩ መርሃ ግብር
👨🏫 በተለየ መንገድ ለላቀ አፈጻጸም ላሳዩና በጡረታ ለተገለሉ መምህራን ሽልማት እና እውቅና ይበረከታል
🌱 አረንጓዴ አሻራ የሚካሄድበት በጉመር ፈርጥ የአረቅጥ ከተማ ይካሄዳል
🏠 ለአቅመ ደካማ የቤት መስሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎች ይበረከታሉ
🤝 እንዲሁም ሌሎች የልማት፣ የአንድነትና የበገጏ አድርጎት ፕሮግራሞች ይካሄዳሉ።
🚌 የትራንስፖርት ወጪ የለም!
ስለዚህ ውድ አንባቢያን ፣ ይህን ታላቅ ቀን አንድም ሰው ሳይቀር በነቂስ እንውጣ! ❤️
👨👩👧👦 ቤተሰቦቻችንን ይዘን እንምጣ!
🤝 ወዳጅ ዘመዶቻችንን ጋብዘን እናምጣቸው !
📢 መልዕክቱን ለሌሎች እናድርስ!
❤️ በአንድነት መገኘታችን ለልጆቻችን፣ ለመምህራኖቻችንና ለመላው ማህበረሰባችን ታላቅ ማበረታቻ ነው!
ይህ የአንድ ሰው ፕሮግራም አይደለም፤ የሁላችንም ነው!
🔥 እንውጣ! ፕሮግራሙን እንሳተፍ! ፕሮግራሙን እንደግፍ!
🔥 ማንም አይቅር! ሁላችንም እንገኝ!
🔥 በነቂስ በመውጣት 7ኛውን ዙር የአንድነት ቀን ታሪካዊ እናድርገው!
❤️ ተቤት ቦጬም ቤት የዝጉጂ!
🤝 7ኛው ዙር —መርሃግብር
ጄዛንዳ የልማትና የአንድነት ማህበር
በአንድነት እንገኝ፤ በአንድነት በልማትና በጎአድራጎት እንሳተፍ! ❤️🤝