12/06/2026
የቁሳቁሰ እና የአልባሳት ድጋፍ
🌟 ዛሬ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት አመራር አካላት በማዕከላችን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል ፤ ከጉብኝታቸውም ጎን ለጎን ማዕከላችን ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ እየሰራ ስላለው ስራ በሰፊው ግንዛቤን ማግኘት እና ስለ ማዕከላችን የተብራራ ገለፃን ማግኘት ችለዋል ፤ ይህም ጠቃሚ ጉብኝት እየሰራን ያለውን ስራ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያደርስ እና ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ከየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እና ከሌሎች የመንግስት ቢሮዎች እና አካላት ጋር የበለጠ አብሮ የመስራት እድልን የሚፈጥር ሆኗል።
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት ለማዕከላችን ድጋፍ ካደረጉት መካከል የመማሪያ ቁሳቁስ ፤ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ፣ የህፃናት አልባሳት ጨምሮ ብዙዎች ተጠቃሽ ናቸው ፤ እነዚህም ቁሳቁሶች ልጆቻችንን ለማስተማር እና እነሱን ለማሰልጠን በእጅጉ የሚረዳን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
✨ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ጽ/ቤት አመራሮች እኛን በማክበር ካላችሁ ጊዜ ላይ አመቻችታቹ ማዕከላችንን በአካል ተገኝታችሁ ስለጉበኙ እና እጅግ ጠቃሚ የሚባል ጊዜን በማዕከላችን ስላሳለፋቹ የተሰማንን ደስታ እየገለፅን ላሳዩን ቀና መተባበር እና ድጋፍ በምናስተምራቸው ልጆቻችን ስም ከልብ ልናመሰግን እንወዳለን። በቀጣይም በብዙ ነገር አብረን ስለምንሰራ እጅግ ደስ ይለናል።💙
✨ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ✨
Material and Clothing Support
🌟 Today, the leadership of the Women and Social Affairs Implementation Office visited our center; during their visit, they were able to gain a broad understanding of the work our center is doing related to autism and receive a detailed explanation about our center; this was a valuable visit that will take the work we are doing to a better level and create an opportunity for the Nehemiah Autism Center to work more closely with the Ministry of Foreign Affairs and other government offices and entities.
Among the support that the Women and Social Affairs Implementation Office provided to our center, there are many items including learning materials; hygiene items, and children's clothing; we have found that these materials are very helpful in educating and training our children.
✨ We would like to express our sincere gratitude to the leaders of the Women and Social Affairs Implementation Office for your kind words and for your sincere cooperation and support, expressing our joy at the time you visited our center and spent a very valuable time at our center. We look forward to working together in many ways in the future. 💙