አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት

አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት, Non-Governmental Organization (NGO), Addis Ababa.

ARDO (አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት) Official page Link: https://www.facebook.com/ardoeth
በጤና ዘርፍ :
በትምህርት ከኬጂ - ኮሌጅ
ለአቅመ ደካሞች ድጋፍና ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የሚሰራ ድርጅት ነው!

የጨረታ ማስታወቂያቀን ነሐሴ 14/2018አወሊያ ቴሌግራም👉 t.me/awoliaschool5
20/08/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

ቀን ነሐሴ 14/2018

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት በአወሊያ ለውጥ መደሰታቸውን ገለፁቀን7/12/2018የዲያስፖራ አባላት አወሊያን በጉብኙበትና በተደረገላቸው ገለፃ አወሊያ ላይ ትልልቅ ለውጦችን በማየታቸ...
14/08/2026

ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት በአወሊያ ለውጥ መደሰታቸውን ገለፁ

ቀን7/12/2018

የዲያስፖራ አባላት አወሊያን በጉብኙበትና በተደረገላቸው ገለፃ አወሊያ ላይ ትልልቅ ለውጦችን በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

አወሊያ ለሙስሊሞች የመብት ትግል መነሻና በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጡ ትልልቅ ለውጦች መነሻ መሆኑዋን አውስተው፤ አወሊያ ከዚህ በፊት ካጋጠማት ስብራት አገግማ ለዚህ መብቃቷን ትልቅ ብስራት ነው ብለዋል፡፡

ከጠበቅነው በላይ ተደስተናል የተለያዩ ቦታዎችንን ብንጎበኝም አወሊያን በማየታችን ትልቅ ደስታና ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ከአወሊያ ጋር በስፋት መስራት እንደሚፈልጉና በተለይም የአወሊያ 75ኛ አመት ምስረታ ከድርጅቱ በተገለጸው መሰረት በድምቀት እንዲከበርና በሌሎችም ስራዎች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን በውይይት ወቅት ቃል ገብተዋል፡፡

የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት አወሊያን ጎበኙቀን7/12/2018ከተለያዩ የአለም አገራት ለአገራዊ ምክክር ወደ አገራችን የመጡ ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት የአወሊያ ዕርዳታ...
14/08/2026

የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት አወሊያን ጎበኙ

ቀን7/12/2018

ከተለያዩ የአለም አገራት ለአገራዊ ምክክር ወደ አገራችን የመጡ ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የዲያስፖራ አባላት የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ ስር ያሉ፤ ትምህርት ቤት፤ አወሊያ ኮሌጅ፤ አወሊያ ጤና ጣቢያ፤የጀናዛ እጥበት እና የነፃ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ጎብኝታል፡፡

በጉብኝታቸው እንደገለፁት አወሊያ በዚህ ልክ መቆቱዋና የመጡ ለውጦችን አድንቀዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀማል መሀመድ እና በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ም/ስራ አስኪያጅ ገለፃዎች ተደርጎለቸዋል፡፡

የሙስሊም ዲያስፖራ ልዑካን በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ! ቀን ሐሙስ ነሐሴ 7/2018👉 ​ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ የሙስሊም ዲያስፖራ ተ...
13/08/2026

የሙስሊም ዲያስፖራ ልዑካን በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ!

ቀን ሐሙስ ነሐሴ 7/2018

👉 ​ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ የሙስሊም ዲያስፖራ ተወካዮች፤ በአወሊያ ዕርዳታና ልማትና ድርጅት እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት፣ የትምህርትና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

👉 አወሊያ ከሰው ልጅ ውልደት ጀምሮ እስከ ሞት ድረስ ያለውን የሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደት የሚያስተናግድ ሲሆን፤ የተለያዩ የሰው ልጅ ፍላጎቶችን በአንድ ማዕከል አጠቃሎ አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛ ኢስላማዊ ተቋም መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት ተብራርቷል።

👉 የዲያስፖራ ተወካዮቹ በድርጅታችን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ያደነቁ ሲሆን፤ “ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስንጎበኝ የተሰማንን ደስታ፣ በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ሥራዎች ላይ በድጋሚ አረጋግጠናል” በማለት የተቋማችንን ዳግም ማንሰራራት አድንቀዋል።
አክለውም አወሊያ ዕድሜ ጠገብ ተቋም እንደመሆኑ፣ ታሪኩን የሚመጥን ሥራ ለማከናወን በአመራሩ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚደግፉና ከድርጅቱ ጎን እንደሚቆሙ ቃል ገብተዋል።

​በጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉት የዲያስፖራ ተወካዮች መካከል፦

👉 ኡስታዝ ሙክታር ጀማል (በእንግሊዝ የነጃሺ መስጂድ ኢማም)
👉 ማህሙድ ሳዲቅ (በካናዳ ቶሮንቶ የኖርዝ ኢስላሚክ ሴንተር ሊቀመንበር)
👉 አሳድ ሙሐመድ (በስዊድን የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወካይ)
👉 ሙሐመድ ደጉ (የፈርስት ሂጅራ መስጂድ ኢማም)
👉 ነዋዊ ሙሳ (የደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ማህበር ሊቀመንበርና ተወካይ)
👉 አብዱራዛቅ ሙሐመድ (የኦሮሞ ማህበር ሊቀመንበር) እና
👉 ኢንጅነር አሊ ላሳን (በስዊድን የአፋር ማህበር ተወካይ) ይገኙበታል።

​አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን የፊደራል ፖሊስ አባላትን አሰመረቀ!ቀን ሐሙስ ሐምሌ 30/2018👉 አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን የፌደራል ፖሊስ አባላት ...
06/08/2026

አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን የፊደራል ፖሊስ አባላትን አሰመረቀ!

ቀን ሐሙስ ሐምሌ 30/2018

👉 አወሊያ ኮሌጅ በአረብኛ ቋንቋ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን የፌደራል ፖሊስ አባላት በዛሬው እለት አስመርቋል።

👉 በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ አወሊያ ለሀገር እያበረከተ ያለወን አስተዋጾ በማንሳት በአድናቆት አመሰግነዋል።

👉 በምረቃው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአ.ዕ.ል.ድ ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ሰይድ አስማረ ባደረጉት ንግግር በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠናዎችን አጠናክረው መስጠት እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

congratulation! Awolia Collage
01/08/2026

congratulation! Awolia Collage

አወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎቹን በታላቅ ድምቀት አስመረቀቀን ሐምሌ 25/2018አወሊያ አረበኛ ኮሌጅ  ለ11ኛ ዙር በዲፕሎማ እንዲሁም ለ3ኛ ዙር በድግሪ ተማሪዎቹን በአወሊያ አዳራሽ አስመርቋል፡፡በአ...
01/08/2026

አወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎቹን በታላቅ ድምቀት አስመረቀ

ቀን ሐምሌ 25/2018

አወሊያ አረበኛ ኮሌጅ ለ11ኛ ዙር በዲፕሎማ እንዲሁም ለ3ኛ ዙር በድግሪ ተማሪዎቹን በአወሊያ አዳራሽ አስመርቋል፡፡

በአጠቃላይ በድግሪና ዲፕሎማ 68 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ ታላለቅ መሻኢኮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮግራሙን የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ም/ስራ አስኪያጅ ዑስታዝ ጀማል ፈንታው ያሰጀመሩ ሲሆን ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላፉ ሲሆን ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

አወሊያ አረበኛ ኮሌጅ ከተመሰረተ ከ20 አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ለአገር ባለውለታ የሆኑ ብዛት ያላቸውን ግለሰቦች ለቁምነገር አብቅቷል፡፡ ኮሌጁ በቅርብ አመታት ተማሪዎቹን ሲኦሲ ፈተና 100% በማሳለፍ ብቸኛና ተመራጭነቱን እያሳደገ ይገኛል፡፡

በኮሌጁ በ2018 የመምህራን ማሰልጠኛ መጀመሩን ኮሌጁ ም/ዲን ዑስታዝ ናስር ዩሱፍ የገለፁ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

ለ2019 የትምህርት ዘመንም ምዝገባ ሊጀመር መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ኮሌጁን በተሻለ ደረጃ ለማስቀጠል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀማል መሀመድ ገልፀዋል፡፡

Congratulation!!  ታላቅ የተማሪዎች  የምርቃ ፕሮግራም በአወሊያ ዛሬ ሐምሌ 25/2018ቀደምቱና ፋናወጊው አወሊያ ኮሌጅ በዛሬው እለት ለ11ኛ ዙር ተማሪዎችን ያስመርቃል ተጋብዘዋል!
01/08/2026

Congratulation!!
ታላቅ የተማሪዎች የምርቃ ፕሮግራም በአወሊያ

ዛሬ ሐምሌ 25/2018

ቀደምቱና ፋናወጊው አወሊያ ኮሌጅ በዛሬው እለት ለ11ኛ ዙር ተማሪዎችን ያስመርቃል ተጋብዘዋል!

የተማሪ ምዝገባ ማስታወሻቀን ጁምዓ ሐምሌ 24/2018            👉 አወሊያ ሙስሊም ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ል የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ቅርንጫፍ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።👉 በ...
31/07/2026

የተማሪ ምዝገባ ማስታወሻ

ቀን ጁምዓ ሐምሌ 24/2018


👉 አወሊያ ሙስሊም ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ል የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ቅርንጫፍ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

👉 በመሆኑም እስከ አሁን ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች ምዝገባ እንድታካሂዱ እናስታውሳለን።

የምዝገባ መርሃ ግብር
👉 ዘውትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
ጠዋት ከ 2፡30 - 6፡30
ከሰዓት ብኋላ ከ 8፡00 - 9፡30
👉 ጁምዓ(አርብ) ምዝገባ የለም!

የነባር ተማሪዎች ምዝገባ
👉 ከሐምሌ 06/2018 እስከ ነሐሴ 21/2018 ያለቅጣት ሲሆን
👉 ከነሐሴ 23/2018 እስከ 30/2018 በቅጣት ይሆናል

👉 ነባር ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ
1. አንድ ጉርድ ፎቶና
2. ሪፖርት ካርድ(ሰርተፊኬት) እና
3. የተማሪ ብሔራዊ መታወቂያ(ፋይዳ) ይዘው መምጣት ግዴታ ይኖርባቸዋል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ
👉 ለጀማሪ (ነርሰሪ) የኬጂ ተማሪዎችና ለ1ኛ ክፍል ከሐምሌ 06/2018 እስከ ሐምሌ 30/2018
👉 ለሌሎች ክፍሎች (ከ2ኛ እስከ 12ኛ ክፍክ) ከሐምሌ 06/2018 አስከ ነሐሴ 21/2018(ባሉን ክፍት ቦታዎች ብቻ)

ለቅድመ አንደኛ ደረጃ (ኬጂ) ት/ት ቤት ተማሪዎች መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
👉 ዕድሜያቸው 4 ዓመት የሞላ
👉 የልደት ሰርተፊኬት ዋናውን እና ኮፒ
👉 የተማሪው ሁለት (2) ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
👉 የወላጅ አንድ (1) ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
👉 ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ኮፒ

ከ1 ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መስፈርቶች
👉 አማካይ ውጤት 65 እና ከዛ በላይ ብቻ
👉 ያላቋረጠና ያልደገመ
👉 የልደት ሰርተፊኬት ኮፒ (ግዴታ ነው)
👉 የተማሪ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ኮፒ (ግዴታ ነው)

አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

ማስታወቂያ             ለአወሊያ ማህበረሰብ በሙሉ!ቀን ሐሙስ ሐምሌ 23/2018                      👉 አንጋፋው እና አረብኛ ቋንቋን በማስተማር ግንባር ቀደም የሆነው አወ...
30/07/2026

ማስታወቂያ
ለአወሊያ ማህበረሰብ በሙሉ!

ቀን ሐሙስ ሐምሌ 23/2018


👉 አንጋፋው እና አረብኛ ቋንቋን በማስተማር ግንባር ቀደም የሆነው አወሊያ ኮሌጅ በድግሪ እና በዲፕሎማ መርሃ ግብር በአረብኛ ቋንቋ ላለፉት አመታት ያስተማራቸውን ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ል በታላቅ ድምቀት በአወሊያ አዳራሽ ያስመርቃል።

👉 ስለሆነም በዚህ ደማቅ የተማሪዎች የምርቃ ፕሮግራም ላይ እንድትገኙ ስንል በታላቅ አክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

አወሊያ ኮሌጅ

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share