በጥበብ ኢስላማዊ ማህበር/ Betibeb Islamic Association

በጥበብ ኢስላማዊ ማህበር/ Betibeb Islamic Association ሁለነንተናዊ በሆኑ ሀገራዊ ማህበረሰባዊ የለውጥ የልማትና የትምህርት ስራዎች እንዲሁም በስነ ምግባር እና በእውቀት የታነጸ ትውልድ በመቅረጽ ላይ የተሰማራ ተቋም!

ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ። በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ። በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ» አትበላቸው። አትገላምጣቸውም...
08/12/2025

ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ። በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ። በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ» አትበላቸው። አትገላምጣቸውም። ለእነርሱም መልካምን (የአክብሮት) ቃልን ተናገራቸው።
ለእነርሱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው። «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ እዘንላቸውም» በል።

አላህ (ሱ.ወ) እርሱን በብቸኝነት የማምለክን ታላቅ ትዕዛዝ ካስቀመጠ በኋላ ወዲያውኑ ያስከተለው ትዕዛዝ ለወላጆች መልካም መሆንን ነው። ለወላጆች የምናደርገው እንክብካቤ በህይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን፣ ከሞቱ በኋላም በዱዓ ልናስታውሳቸው እንደሚገባ ያስገነዝባል:: ይህንን ግዴታ መወጣት የአላህን ውዴታ ከምናገኝባቸው ታላላቅ መንገዶች አንዱ ነው።

አላህ ወላጆቻችንን እድሜያቸውን በኢማን፣ ጤናቸውን በአፊያ አጊጦ ያቆይልን።
በእዝነቱ ወደ እርሱ የወሰዳቸውንም፣ ቀብራቸውን የጀነት ጨፌ ፣ ማረፊያቸውን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግልን።አሚን!✨

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!
#ዱዐ
#ቁርዐን
https://t.me/beTibeb_In

የቀናት ድምቀት፣ የሳምንቱ ጸጋ... ጁምዓ!ጁምዐ የሰው ልጆች ሁሉ አባት የሆነው ነቢዩሏህ አደም(ዐ.ሰ) የተፈጠረበት፣ ጀነት የገባበት ፣ እንዲሁም ቂያማም የምትቆምበት ታላቅ ቀን ነው። ይህን...
05/12/2025

የቀናት ድምቀት፣ የሳምንቱ ጸጋ... ጁምዓ!

ጁምዐ የሰው ልጆች ሁሉ አባት የሆነው ነቢዩሏህ አደም(ዐ.ሰ) የተፈጠረበት፣ ጀነት የገባበት ፣ እንዲሁም ቂያማም የምትቆምበት ታላቅ ቀን ነው። ይህንን ውድ ቀን አላህ መርጦልናልና በዱዐ፣ በዚክርና በመልካም ስራዎች ወደርሱ እንቃረብ::

አላህ መልካሙን ሁሉ ይወፍቀን።
ጁምዓ ሙባረክ 🌙

اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.

#ጁምዐ
#ሰለዋት
https://t.me/beTibeb_In

 #ሒጃብበዚህ ውብ ርዕስ ዙሪያ የምንወያይበት፣ ልምዳችንን የምንካፈልበትና የምንማማርበት ልዩ ቆይታ ይኖረናል።ሐሙስ ህዳር 25, ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ በበጥበብ ኢስላሚክ አሶሲዬሽን የቲክቶክ ...
03/12/2025

#ሒጃብ

በዚህ ውብ ርዕስ ዙሪያ የምንወያይበት፣ ልምዳችንን የምንካፈልበትና የምንማማርበት ልዩ ቆይታ ይኖረናል።

ሐሙስ ህዳር 25, ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ በበጥበብ ኢስላሚክ አሶሲዬሽን የቲክቶክ ገጻችን ላይ በቀጥታ ሥርጭት ሁላችሁም ተጋብዛችሗል።✨

https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZM-91fNAmVH7xz

ከአላህ(ሱ.ወ) ክብርና ልዕልና የሚመነጨው እውነተኛ እምነትና ፍራቻ ለዘላለም የመረጋጋትና የስኬት መንገድ ቁልፍ ነው:: መንገዱ ግን ቀላል አይሆንም፣ የነፍስያና የሸይጧን መሰናክሎች ጉዞውን ...
01/12/2025

ከአላህ(ሱ.ወ) ክብርና ልዕልና የሚመነጨው እውነተኛ እምነትና ፍራቻ ለዘላለም የመረጋጋትና የስኬት መንገድ ቁልፍ ነው:: መንገዱ ግን ቀላል አይሆንም፣ የነፍስያና የሸይጧን መሰናክሎች ጉዞውን ሊያከብዱብን ይታትራሉ:: መሰናክኖሎቹ ባጋጠሙንና የጌታችንን ትዕዛዝ ተላልፈን በወንጀል እንድንዘፈቅ በገፉን ቁጥር እርሱ ፊት የምንቆምበትን እለት እናስታውስ::

አላህም(ሱ.ወ) እርሱ ፊት መቆምን ፈርተው ከወንጀል ለሚታቀቡት ባሮቹ ታላቅ ምንዳ እንዳዘጋጀ ያበስረናል:: ከዚህ ታላቅ ምንዳ ተቋድሰን፣ ደግሞም ለሰፊው ፍቅሩና ወሰን ለሌለው እዝነቱ የተገባን ባሮቹ እንድንሆን ያድርገን:: አሚን::

ድንቅና ፍሬያማ ሳምንት እንዲሆንላችሁ ተመኘን!

#ቁርዐን
https://t.me/beTibeb_In

በዚያ ሰፊና ሁሉን አዋቂ በሆነው ዕውቀቱ ውስጥ፣ አላህ: ባሮቹ የሚሰሩትን፣ የሚያስቡትን፣ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ጠንቅቆ ያውቃል። ከእርሱ ምንም ነገር አይሰወርም::ለጌታችን ብለን በየዕለ...
28/11/2025

በዚያ ሰፊና ሁሉን አዋቂ በሆነው ዕውቀቱ ውስጥ፣ አላህ: ባሮቹ የሚሰሩትን፣ የሚያስቡትን፣ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ጠንቅቆ ያውቃል። ከእርሱ ምንም ነገር አይሰወርም::
ለጌታችን ብለን በየዕለቱ የምናደርጋት ሱጁድ፣ የሱን ውዴታ ተስፋ አድርገን የምናወጣው ሰደቃ፣ በጤንነትም ሆነ በህመም ላይ ሆነን የምናከናውናት እያንዳንዷ ተግባራችን አላህ ዘንድ በትክክል ትመዘገባለች። በዚያው ልክ ደግሞ፣ የምንሰራው ጥፋትም ሆነ የምንዘነጋው ሀቅ በርሱ እይታ ስር ናቸው::

አላህ አይዘነጋምና በስራዎቻችን አንዘናጋ::
በሰደቃና ሰለዋት የተዋበ ጁምዐ ይሁንላችሁ✨

اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
#ጁምዐ
#ሰደቃ
#ሰለዋት
https://t.me/beTibeb_In

Address

Addis Ababa

Telephone

+251904438888

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጥበብ ኢስላማዊ ማህበር/ Betibeb Islamic Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በጥበብ ኢስላማዊ ማህበር/ Betibeb Islamic Association:

Shortcuts

Share