Wehe meya ወሄ መያ

Call Directions Website

Wehe meya ወሄ መያ ገጠር ላለው ህዝባችን ለተጋረጡበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች በጋራ በመደራጀት መፍትሄ እናገኝ ዘንድ የምንሰራበት
ወሄ ሜና በወሄ መያ
ኧገኜ ልማት ብእማት

20/09/2026
18/09/2026
ወሄ መያ የልማትና በጎ አድራጎት ድርጅቶች የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሚያደርጉት ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ውጤታማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ...
18/09/2026

ወሄ መያ የልማትና በጎ አድራጎት ድርጅቶች የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሚያደርጉት ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ውጤታማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገለፀ።

መስከረም 7/2019(ወልቂጤ)

ወሄ መያ የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር በጉራጌ ዞን በእኖር እንዲሁም እኖር ኤነር መገር ወረዳዎችና በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ከ850 በላይ ተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የእኖር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽ /ቤት ሀላፊ አቶ ሽኩረታ አብድልከሪም መንግስት፣ ባለሀብቱና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በመቀናጀት በትምህርት ልማቱ ዙርያ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ እጅግ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሚያደርጉት ድጋፍ የትምህርት ጥራትን ውጤታማ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ነው የተናገሩት።

ወሄመያ የልማትና በጎ አድራጎት ማህበርም በ2ቱ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ጊዜያት እያደረገ ላለው ተሳትፎ አመስግነው በቀጣይም መሠል በጎ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ወሄመያ የልማትና በጎ አድራጎት ማህበር የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶች ከ850 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ማህበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በተለይም በትምህርት፣ በጤናና በሌሎችም ዘርፎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

በስነስርአቱ ላይ የማህበሩ አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም የተማሪ ወላጆች፣ ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ዘጋቢ፣ ፉአድ አብደላ

20/02/2026
19/02/2026
11/02/2026

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ።እንኳን ለ1447ኛው ለተከበረው ታላቁ ረመዳን አላህ በሰላም አደረሳችሁ።
🌴የተወደዳችሁ የተከበራችሁ የደግነት ምሳሌ የምስኪኖች አንባ አባሾች በያላችሁበት የአላህ እዝነት ሰላም በረከትና ጥበቃው አይለያችሁ እያልን የተለመደውን ✅የወሄ መያ ልማትና በጎ አድራጎት ማህበር: የችግረኛ ቤተሰቦች የረመዳን ማፍጠሪያ የማሰባሰብ መርሀግብር እነሆ በይፋ ጀመረ።

በየ ገጠሩ እጅግ ብዙ የሚባሉ ችግረኛና ደካማ ጠያቂም ሆነ አይዞህ ባይ ያጡ :ይበሉት ይቀምሱት የሌላቸው:በማፍጠሪያ እጦት ቀኑን ፆመው አዳሩንም ለመፆም ለሚገደዱ ወገኖቻችን ካለን ላይ ቀንሰን የአላህን ውዴታ በመሻት በአላህ ፍቃድ ለችግራቸው በመድረስ ከጎናቸው አለን በማለት እንባቸውን የምናብስበት የደግነት ጥሪ።

✅ ለ1000 ቤተሰብ ጠቅላላ 3,300,000 ብር የሚፈጅ ሲሆን:የአንድ ቤተሰብ 3,300ብር ብቻ ነው።ዝርዝሩን እንደሚከተለው ሰፍሯል።👇👇👇
ወሄ መያ በጎ አድራጎት የማስፈጠሪያ ቁሳቁስ ዝርዝር
አይነት ብዛት ዋጋው በብር
ሩዝ 5 ኪሎ 925
ዘይት 3 ሊትር 1400
ቅንጬ 5 ኪሎ 975

እኛ የስንት ሰው እንባ አብሰን የደስታቸው ሰበብ እንሆናለን???
🌴በእርግጥም ሰደቃ ሀብትን ያፋፋል እንጂ አይቀንስም።

ወሄ ሜና
በወሄ መያ

ወ መ ል በ አ ማ
وملبعما

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wehe meya ወሄ መያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share