Ethiopia Reads/ኢትዮጵያ ሪድስ

Ethiopia Reads/ኢትዮጵያ ሪድስ Ethiopia Reads is a Non-profit organization to support children's literacy and enhance the reading c

"የንባብ ከተማ" የህፃናት ቴአትር ተመረቀ‎‎  በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት የተዘጋጀው "የንባብ ከተማ" የተሰኘ አዲስ የህፃናት ቴአትር ዛሬ ዕሁድ  ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በፍላሚንጎ...
12/07/2026

"የንባብ ከተማ" የህፃናት ቴአትር ተመረቀ

‎ በህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት የተዘጋጀው "የንባብ ከተማ" የተሰኘ አዲስ የህፃናት ቴአትር ዛሬ ዕሁድ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ኮምፕሌክስ ተመርቋል።

‎በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ሪድስ "ገበታ" ቤተ-መጻሕፍት ተጠቃሚ ህፃናት፣ ወላጆች፣ አርቲስቶችና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።

‎ከቴአትሩ በተጨማሪ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የተረት ንባብ እና አዝናኝ ዝምተኛ ተውኔት (Mime Drama) ለታዳሚዎች ቀርቧል።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራም አማካሪና አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገ/ መድህን " ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋ ለህፃናት ምቹ የሆነች ከተማ እንድትሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ሲሆን ቀዳማይ ልጅነት ላይ ከሚሰሩ ሥራዎች መካከል የልጆች ንባብ አንዱ ነው ።" ብለዋል።

‎በቀጣይም ተውኔቱ በየክፍለ ከተማ ለሚገኙ ህፃናትና ወላጆች እንዲቀርብ ከህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ጋር የትብብር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

‎በትግስት ተስፋዬ ተደርሶ በደምሴ በየነ የተዘጋጀው "የንባብ ከተማ" የህፃናት ቴአትር፣ ህፃናት ሀገራቸውን፣ አካባቢያቸውንና ባህላቸውን እንዲያውቁ እንዲሁም የንባብ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ የሚያበረታታ መልዕክት ይዟል።
‎በተጨማሪም ወላጆች፣ አሳዳጊዎችና መምህራን ለህፃናት በመደበኛነት የማንበብ ልምድን እንዲያዳብሩ እና ለንባብ ምቹ አካባቢ እንዲፈጥሩ ያበረታታል።




‎**********************
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

‎************************

📢✨የልጆች  የመጽሐፍ ምርቃት ግብዣ !ኮሜዲያን እና የህፃናት መጽሕፍት ደራሲ አስረስ በቀለ (ቼሪ) አዲሱን የልጆች መጽሐፍ “ኮሚኩ ሙዝ” ለምርቃት አዘጋጅቷል።🗓 ቀን:- እሁድ ሰኔ 14 ቀን ...
16/06/2026

📢✨የልጆች የመጽሐፍ ምርቃት ግብዣ !
ኮሜዲያን እና የህፃናት መጽሕፍት ደራሲ አስረስ በቀለ (ቼሪ) አዲሱን የልጆች መጽሐፍ “ኮሚኩ ሙዝ” ለምርቃት አዘጋጅቷል።

🗓 ቀን:- እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት:- ከቀኑ ጀምሮ 8:00
📍 ቦታ:- የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት
📚 አአስረስ በቀለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን የመጀመሪያዋን የልጆች ካራክተር “ቼሪ” በመፍጠር በልጆች መዝናኛ እና ትምህርት ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

📖 ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን የጻፈው ደራሲ አስረስ በቀለ በሀገራችን የህፃናት ንባብና መዝናኛ ባህል ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

🏆 በ2022እ.ኤ.አ በEthiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ ለህፃናት ሥነ-ጽሑፍ አበርክቶው እውቅና ተሰጥቶታል። እንዲሁም ኢትዮጵያ ሪድስ ስራዎቹን በዳግም ህትመት ፕሮጀክት ውስጥ አካትቷል።

👨‍👩‍👧‍👦 ምርቃቱ ለሁሉም ክፍት ነው — ልጆቻችሁን ይዘው በመገኘት ይህን የልጆች በዓል አብረን እናክብር!
📌 እንዳታረፍዱ — እንጠብቃችኋለን!

‎******************************
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

የአዲስ አበባ ከተማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ጉዞ !‎በዶ/ር እሸትአየሁ ክንፉ‎በ6ኛው የኢትዮጵያ ሪድስ የልጆች ንባብ ጉባኤ።‎ ‎***‎የሚያነብቡ ያብቡ!! ‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ...
06/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ጉዞ !
‎በዶ/ር እሸትአየሁ ክንፉ
‎በ6ኛው የኢትዮጵያ ሪድስ የልጆች ንባብ ጉባኤ።

‎***
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

‎************************
‎The Journey of Addis Ababa city in Early Childhood Development.
‎Dr. Eshetayehu Kinfu
‎Ethiopia Reads The 6th Annual Children’s Reading Summit

‎*******************

‎Those who Read Bloom!!
‎Let’s work Together for Enhancing Children Reading Culture!!
‎Share, like and subscribe Ethiopia Read’s You Tube Channel and be a Family.

Se alla dina favoriter bland videor och musik, ladda upp originalinnehåll och dela allt med vänner, familj och hela världen på YouTube.

A very successfull event ! Congrats for all !!
15/05/2026

A very successfull event ! Congrats for all !!

‎‎‎"ኢትዮጵያ ሪድስ በቀዳማዊ ልጅነት ንባብ ክህሎት ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው "‎‎ኢትዮጵያ ሪድስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም...
30/04/2026


‎‎"ኢትዮጵያ ሪድስ በቀዳማዊ ልጅነት ንባብ ክህሎት ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው "

‎ኢትዮጵያ ሪድስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም እና Van Leer Foundation ጋር በመተባበር ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአብረሆት ቤተ መጽሐፍት የወላጆች ወይም የአሳዳጊዎች የምክር አቅም ግንባታ ሰራተኞችን ለሚደግፉና ለሚከታተሉ ተቆጣጣሪዎች እና አስተባባሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።

‎ስልጠናው ከ4 ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 45 ሰልጣኞችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹ በአዲስ አበባ ቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ስር የሚገኙ የወላጆች ወይም የአሳዳጊዎች የምክር አቅም ግንባታ ሰራተኞችን ለሚደግፉና ለሚከታተሉ ተቆጣጣሪዎች፣ አስተባባሪዎች እንዲሁም የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ባለሙያዎች ናቸው።
‎ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ ስልጠና በቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ውስጥ የልጆችን የንባብ ክህሎትና ልምድ ማካተት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ህፃናት በቀዳማዊ ልጅነት ዕድሜያቸው ከመጽሐፍ እና ከንባብ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዙ ክህሎቶችን ለማሳደግ ያለመ ነው።
‎ይህ ትብብር በአዲስ አበባ ውስጥ የቀዳማዊ ልጅነት እድገትን በማጠናከር ፣ህፃናት የተሻለ የመማር መሠረት እንዲኖራቸው እና የንባብ ባህል ከልጅነት ጀምሮ እንዲጎለብት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።


‎***
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

“Ethiopia Reads is Providing Training for Trainers on Early Childhood Literacy Skills”
‎Ethiopia Reads, in collaboration with the Addis Ababa City Administration, the Addis Ababa Early Childhood Development Program, and the Van Leer Foundation, is conducting a training of trainers for supervisors and coordinators who support and monitor parent or caregiver counseling capacity-building workers at the Abrehot Library on April 29, 2018 E.C.
‎The training brings together 45 participants drawn from four sub-cities. The participants are supervisors, coordinators, and professionals from childcare centers who support and oversee parent or caregiver counseling capacity-building workers under the Addis Ababa Early Childhood Development Program.
‎This two-day training focuses on integrating children’s reading skills and reading practices into early childhood development programs. It aims to enhance skills that help strengthen children’s engagement with books and reading from an early age.
‎It has been noted that this collaboration contributes to strengthening early childhood development in Addis Ababa, helping children build a stronger foundation for learning and fostering a reading culture from early childhood.

‎*****************************************

‎Those who Read Bloom!!
‎Let’s work Together for Enhancing Children Reading Culture!!
‎Share, like and subscribe Ethiopia Read’s You Tube Channel and be a Family.

ቻይናዊያን እንዲህ ይላሉ  ‹ሺህ ዘመን እያለፍክ ፣ በህይወት ዘመን ቆመህ እንድትናገር ተፈጥሮ አትፈቅድልህም፤ ከፃፍከው ግን የተፈጥሮን የክልከላ ድንበር አልፈህ  ለብዙ ሺህ ዘመናት ያለከልካ...
26/04/2026

ቻይናዊያን እንዲህ ይላሉ ‹ሺህ ዘመን እያለፍክ ፣ በህይወት ዘመን ቆመህ እንድትናገር ተፈጥሮ አትፈቅድልህም፤ ከፃፍከው ግን የተፈጥሮን የክልከላ ድንበር አልፈህ ለብዙ ሺህ ዘመናት ያለከልካይ ትናገራለህ፡፡› የሀገራችን ሊቁ ዶ/ር እጓለ ገ/ ዮሐንስስ ምን አሉ ? ሙሉውን ገብተው መመልከት ይችላሉ፡፡


የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!

"The Chinese say: as you pass through thousands of years, nature does not allow you to stand and speak beyond your lifetime; but through what you write, you transcend the limits set by nature and speak freely for many thousands of years."
What did our country's scholar Dr. Eguale Gebre Yohannes say? You can watch the full version to find out.
*****************************************

‎Those who Read Bloom!!
‎Let’s work Together for Enhancing Children Reading Culture!!
Share, like and subscribe Ethiopia Read’s You Tube Channel and be a Family.

The 6th Annual Children,s Reading Summit(6ኛው የልጆች ንባብ ጉባኤ )

ኢትዮጵያ ሪድስ ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ የማህበረሰብ ሳይንስ ዲፓርትመንት ጋር በልጆች ንባብና ትምህርት ላይ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ኢትዮጵያ ሪድስ በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ ...
09/04/2026

ኢትዮጵያ ሪድስ ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ የማህበረሰብ ሳይንስ ዲፓርትመንት ጋር በልጆች ንባብና ትምህርት ላይ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮጵያ ሪድስ በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ ያሉ ልጆች የትምህርትና የንባብ ችሎታ ለማሻሻል ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ የሶሻል ሳይንስ ትምህርት ክፍል ጋር የትብብር ስምምነት አደረገ።
የተፈረመው ስምምነት በአካባቢው ህፃናት መካከል የንባብ ባህልን ማሻሻል ፣ ቤተ መፅሃፍትን ማስፋፋት ፣ የተለያዪ የስልጠና እና የምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት ፣ እንዲሁም በንባብ እና ትምህርት ዙሪያ ህብረተሰቡን ማሳተፍ ፣ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ይመለከታል።

ይህ ትብብር በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ ያሉ ልጆች የንባብ ክህሎት እና ልምድ ለማጎልበት አስፈላጊ ሚና ይኖረዋል።


የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!

Ethiopia Reads has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with the Department of Social Sciences at Hawassa University to collaborate on children's reading and education.
has entered into a partnership agreement with the Social Sciences Department of Hawassa University to improve the educational and reading skills of children in Hawassa city and its surrounding areas.
‎The signed agreement focuses on enhancing reading culture among children in the community, expanding libraries, jointly conducting various training and research activities, as well as engaging the community in reading and education initiatives, along with other multidisciplinary efforts.
‎This collaboration will play a significant role in strengthening the reading skills and habits of children in Hawassa and nearby areas.

‎*****************************************

‎Those who Read Bloom!!
‎Let’s work Together for Enhancing Children Reading Culture!!
Share, like and subscribe Ethiopia Read’s You Tube Channel and be a Family.

ኢትዮጵያ  ሪድስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከአዲስ አበባ ሴቶች ፣ሕፃናት እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ Van Leer Foundation እና ፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር በመተባበ...
23/03/2026

ኢትዮጵያ ሪድስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከአዲስ አበባ ሴቶች ፣ሕፃናት እና ማኀበራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ Van Leer Foundation እና ፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር በመተባበር አቧሬ በሚገኘው የልጆች መጫወቻ ፓርክ የንባብ ፌስቲቫል አካሂዷል።
‎በቦታው ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር የተገኙ ሲሆን ልዩ
‎ልዩ አዝናኝና አስተማሪ ትርኢቶችን በመመልከት፣በጨዋታ ፣ በንባብ ፣ ተረት በማድመጥ እና ሥዕል በመሣል ጊዜያቸውን አሳልፈዋል።
‎ተረት በማንበብ ውድድር ያደረጉ ወላጆችና ልጆችም ከኢትዮጵያ ሪድስ የሐገር ውስጥ ተጠሪ ወ/ሪ የምስራች ወርቁ እጅ የመጽሐፍ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


‎………………………………………..
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!

Ethiopia Reads in collaboration with A.A city admnistration , A.A woman and children affair office, Van L‎eer foundation, and French Embassy have organized a children reading event in one of the playgrounds of Addis Ababa. Children attended the event together with their parents and spent their time enjoying various fun and educational activities. These included watching performances, playing games, reading, listening to stories, and drawing.
‎Parents and children who participated in the storytelling reading competition were awarded books by Ms. Yemisirach Worku, the Country Director of Ethiopia Reads.

‎*****************************************

‎Those who Read Bloom!!
‎Let’s work Together for Enhancing Children Reading Culture!! Share, like and subscribe Ethiopia Read’s You Tube Channel and be a Family.

"6 ኛው የልጆች ንባብ ጉባኤ እየተካሄደ ነው"‎‎ኢትዮጵያ ሪድስ በየአመቱ የሚያካሂደው የልጆች ንባብ ጉባኤ "የንባብን ችግኝ በቀዳማዊ ልጅነት መትከል " በሚል መሪ ቃል ካሳንችስ በሚገኘው ኢ...
18/03/2026

"6 ኛው የልጆች ንባብ ጉባኤ እየተካሄደ ነው"

‎ኢትዮጵያ ሪድስ በየአመቱ የሚያካሂደው የልጆች ንባብ ጉባኤ "የንባብን ችግኝ በቀዳማዊ ልጅነት መትከል " በሚል መሪ ቃል ካሳንችስ በሚገኘው ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል መጋቢት 8ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።

‎የዘንድሮውን ንባብ ጉባኤ ኢትዮጵያ ሪድስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስትራጄክ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽፈት ቤት (SPMO)፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ቫን ሊር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው ።

‎በመድረኩ በሁለት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጁ ከ0 እስከ 3 ዓመት እና 4 እስከ6 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት የሚሆኑ 20 ሺህ መፅሐፍት አስመርቋል።

‎በጉባኤው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች በልጆችና ሕፃናት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሐላፊዎችና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በሕፃናት የንባብ ልምድ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ውይይቶች እና የልምድ ልውውጥ አድርገዋል ። መርሐ ግብሩ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ውሏል።


‎………………………………………..
‎የሚያነብቡ ያብቡ!!
‎የልጆች የንባብ ባህልን ለማሳደግ ኑ በጋራ እንስራ!!
‎የኢትዮጵያ ሪድስ የ ዩቲዩብ ቻናል ሼር፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!









09/03/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Reads/ኢትዮጵያ ሪድስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopia Reads/ኢትዮጵያ ሪድስ:

Shortcuts

Share