እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር/Ehew Lade Charity Association

እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር/Ehew Lade Charity Association 📍የእሔውላዴ በጎ አድራጎት ማህበር የፌስቡክ ገፅ ነው
✍️ የእሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር ከመንግስት ህጋዊ ሰውነት ያለው የልማትና በጎ አድራጎት ማህበር ነው።
👉 እሔው ላዴ የእናቶቻችንን እምባ ለማበስ የተቻለውን ያደርጋል።

እንኳን ለ 1447 ኛው አ/ሂ  የረመዷን ወር እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!ይህ የተከረው ወር የቁርኣን፣ የሰሏት፣ የዚክር፣ የመፈቃቀር፣ የመረዳዳት፣ እና የመግፊራ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!© ...
17/02/2026

እንኳን ለ 1447 ኛው አ/ሂ የረመዷን ወር እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!

ይህ የተከረው ወር የቁርኣን፣ የሰሏት፣ የዚክር፣ የመፈቃቀር፣ የመረዳዳት፣ እና የመግፊራ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

© እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር

ይህ እቅድ ብቻ ሳይሆን የቀጣይ አመት ቃል ነው!!🌟አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ ውድ የኢሔውላዴ ቤተሰቦች!ይህ ለቀጣይ አመት አላህን ከዚያም እናንተን ይዘን የያዝነው እቅድ ነው!የማህበረሰባች...
16/02/2026

ይህ እቅድ ብቻ ሳይሆን የቀጣይ አመት ቃል ነው!!🌟

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ ውድ የኢሔውላዴ ቤተሰቦች!

ይህ ለቀጣይ አመት አላህን ከዚያም እናንተን ይዘን የያዝነው እቅድ ነው!

የማህበረሰባችንን ችግር ለመቅረፍ ወገባችንን አስረን የምንሰራበት ጊዜ አሁን ነው።

አላህ ያበርታን🙏

ሀሳብን ወደ ስራ- እቅድን በተግባርእሔውላዴ በጎ አድራጎት ማህበር  የማስተማር ዘዴና ጥበብ እንዲሁም የአዕምሮ ጤና እና የሳይኮሎጂ ድጋፍ ስልጠና ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት መምህራን እ...
12/02/2026

ሀሳብን ወደ ስራ- እቅድን በተግባር

እሔውላዴ በጎ አድራጎት ማህበር የማስተማር ዘዴና ጥበብ እንዲሁም የአዕምሮ ጤና እና የሳይኮሎጂ ድጋፍ ስልጠና ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት መምህራን እና ለወረዳ የትምህርትፅ/ቤት አስዳደር አካላት በተሳካ ሁኔታ ሰጥታል።

በአይነቱ ልዩ የሆነ የመምህራን ስልጠና የተዘጋጀው በዘርፉ የረጅም አመት ልምድ ያላቸው የዲላ ዩኒቨርስቲ እጩ ፕሮፌሰር አቶ ብርሃኑ ደንደኣ (ዶ/ር) ጋር በመተባበር ነው።

ዶ/ሩ ያዘጋጁት ስልጠና ለረጅም አመታት በማስተማር በተለይም የማስማር ዘዴን ለዩኒቨርሲቲ መምህራን በማሰልጠን ያከበቱትን ልምድ በመጠቀም እና እንደ ሀገር ብሎም እንደ ማህበረሰብ የተስተዋለውን ችግር በማጥናትና መፍትሔውን ሳይናሳዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ ለመምህራን በእጅጉ ጠቃሚ ስልጠና ሊሰጡ ችለዋል።

በተጨማሪም የሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ም/ል ርዕሰ መምህር አቶ አብደላ ልምዳቸውን አጋርተዋል። የተለያዩ አጋዥ የፈተና ጥያቄዎች፣ የጥያቄዎች ስብስቦችና ሌሎች አጋዥ ማስተማሪያ ዘዴዎችን አጋርተዋል።

ለሁለት ቀናት በቆየው ይህ ስልጠና በንቃት የተሳተፉበትና መምህራን ከስልጠናው ያገኙትን ልምድና እውቀት በመጠቀም በቀጣይ በራሳቸውና በማህበረሰባቸው ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ይህንን ላዘጋጀው እሔውላዴ በጎ አድራጎት ማህበር ለዶ/ር ብርሃኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም በማህበረችን ለሁሉም ለሙጎና ኤትሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስና ጋዎን የተበረከተ ሲሆን በዚህም መምህራንና ትምህርት ቤቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የመማር ማስተማር ሂደቱን በተጨማሪ ማጣቀሻዎች ለመደገፍ እና ለመምህራን የመዝናኛ ሰዓታቸውን የሚያሳልፉበት የዋይፋይ አገልግሎት መስጫ ራውተሮች ተበርክቷል።

ትምህርት ቤቶችን ውብ ለማድረግና ሳቢ ለማድረግ በተጀመረው እንቅስቃሴም አንድ ሙሉ ብሎክ በማደስ በማስረከብ ለቀጣይ ሌሎች እንዲሳተፉና ሌሎች ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ በተሳካ መንገድ መንገዱን ጀምሯል።

እሔውላዴ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ሀላፊነቱን ለመወጣት ያቀደውን ተግባር በተሳካ ሁኔታ ወደ መሬት ያወረደበትን እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ለተመለሱ አባላቶቻችን ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የማህበረሰብ ለውጥ ቀጣይ ራዕያችን ነው። ከጎናችን ሰላሆናችሁ እናመሰግናለን🙏
05/02/2026

የማህበረሰብ ለውጥ ቀጣይ ራዕያችን ነው። ከጎናችን ሰላሆናችሁ እናመሰግናለን🙏

04/02/2026

"ያግዛን ያብዘ፣ መላያሙ የቃን፣ በስርማም ያግዛን ቦሾ የተለቅ"
🤲🤲🤲🤲
አቦ ዱኣ!

https://vt.tiktok.com/ZSatEbt2X/

የሙጎ የቅን ልቦች ቶርናመንት በዛሬው እለት ፍፃሜውን አግኝቷል። ማህበራችንም የፍፃሜው ፕሮግራሚ የክብር ተሳታፊ ሆኗል።የሙጎ የተለያዩ መንደሮችን በማሳተፍ ሲደረግ የነበረው የእግር ኳስ ውድድ...
01/02/2026

የሙጎ የቅን ልቦች ቶርናመንት በዛሬው እለት ፍፃሜውን አግኝቷል። ማህበራችንም የፍፃሜው ፕሮግራሚ የክብር ተሳታፊ ሆኗል።

የሙጎ የተለያዩ መንደሮችን በማሳተፍ ሲደረግ የነበረው የእግር ኳስ ውድድር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ውድድሩንም አውሮ በበላይነት በማጠናቀቅ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በእለቱ በክብር እንግድነት የተጋበዘው እሔውላዴ በጎ አድራጎት ማህበር አመራሮች በውድድሩና በስብስቡ የተሰማቸው ደስታ ገልፀው ስፖርቱ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩሉን እንደሚያደርግ ገልፀው ስብስቡ በቀጣይ በሙጎና አካባቢው ማህበራዊ ስራዎች በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም በተለያዩ ዘርፎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የእውቅና ሰርተፊኬት እንዲሁም ለአሸናፊዎች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶች በክብር እንግዶች ተበርክቷል።

በዚሁ አጋጣም ለአውሮ እግር ኳስ ቡድን እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በፕሮግራሙ በክብር የጋበዛችሁን አዘጋጆና አስተባባሪዎ በማህበራችን አባላት ስም እናመሰግናለን።

©እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር

ከከፍታ⬆️  ወደ ቁልቁለት⬇️ 💔.... ተስፋ🌟በዚያ በድቅድቅ ጨለማ በ25 ሳንቲም 🪙 የተለኮሰው ብርሃን🕯️በርካታ ዶክተሮችን፣ፕሮፌሰሮችን፣ ባለሀብቶችና አምራች ዜጎችን እያፈራ ለዘመናት ሳይጠ...
30/01/2026

ከከፍታ⬆️ ወደ ቁልቁለት⬇️ 💔.... ተስፋ🌟

በዚያ በድቅድቅ ጨለማ በ25 ሳንቲም 🪙 የተለኮሰው ብርሃን🕯️በርካታ ዶክተሮችን፣ፕሮፌሰሮችን፣ ባለሀብቶችና አምራች ዜጎችን እያፈራ ለዘመናት ሳይጠፋ ዘልቋል። ሆኖም የተሻለ እውቀት፣ የኢኮኖሚ አቅምና የላቀ አስተሳሰብ ደረጃ ላይ ነን ብለን በምናስብበት በዚህ ወቅት በተቃራኒው ሆኖ ይገኛል።
በቴክኖሎጂና በፈጠራ ታግዘን ከግዜው እኩል መራመድ ሲገባን ቴክኖሎጂው ወደፊት🔝 እኛ ወደ ኃላ🔙 እየተጓዝን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ስለ ትምህርት ውድቀታችን ከዚህም በላይ የሚገለፅ ቢሆንም በትንሹም ቢሆን ለለውጡ መስራቱ የሁሉም ሚና ሊሆን ይገባል።

እነሆ እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር ለለፉት 14 አመታት ሳያቋርጥ የት/ት ቁስቁስ ድጋፍ ለ500 በላይ ተማሪዎች አድርሶ በርካቶች ከት/ት ገበታቸው እንዳይቀሩ እያደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም ተማሪዎቻችን ለ6 ሰዓታት የሚቀመጡበት ወንበራቸው ምቹ እንዲሆን የቀድሞ ተማሪዎች ጋር በመሆን ደረጃውን የጠበቀ ወንበሮችን አስረክቧል። ይህም ለትምህር አሰጣጥ ሂደቱ የላቀ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

በቀጣይም የቴክኖሎጂውን ውጤት በመጠቀምና የአስተሳሰብ ደረጃን በማሳደግ የትምህርት ውጤትን ለማሻሻል ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

✨እነሆ የጋራ ውድቀታችንን በጋራ እንጋፈጠው እያልን ጥሪያችንን እናቀርባርባለን።✨

"ምን ምን ይሰራ?".... እንመለሳለን✍️
🌟ሸጋ ጁሙዓ❤

28/01/2026

Address

Betel
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እሔው ላዴ በጎ አድራጎት ማህበር/Ehew Lade Charity Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share