Hirnoye Foodstuffs

Hirnoye Foodstuffs EXPORT TRADE IN PROCESSED FOODSTUFFS, SPICES, GRAINS, PULSES, CEREALS, HERBS, HOME APPLIANCES AND ARTIFACTS

02/11/2025
21/05/2025

የነጭ ሽንኩርት 34 የጤና በረከቶች!
=====================
1. የደም ቅዳ (Artery) ግድግዳዎችን በማደደርና በማጥበብ የሚታወቀውን አቲሮስክሊሮሲስ የተሰኘውን በሽታ ይዋጋል፡፡
2.የኮልስትሮል መጠንን ይቀንሳል፡፡
3. የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡
4. ጉንፋንንና ሌሎች መሰል የላይኛው የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ይከላከላል፣ ይፈውሳልም፡፡
5.የባክቴሪያ መራባትንና መዛመትን ይከላከላል፡፡
6. ቲቢን ለማከም ይረዳል፡፡
7. መግል የቀላቀለ ቁስልን ለማከም ይረዳል፡፡
8. የብልት በሽታ (Trichomoniasis) የሚሰኘውን የአባላዘር በሽታ ለማከም ይረዳል፡፡
9.በህዋሳት ውስጥ የሚካሄደውን ዋንኛውን ኬሚካላዊ ውህደት (Metabolism) ያነቃቃል፡፡
10.ከነቀርሳ (Cancer) ዓይነቶች አንዱ የሆነውን የኮለን ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
11. የሐሞት ከረጢት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
12. የፊንጢጣ ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
13. የጡት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
14. በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
15. ለምግብ መፈጨት ሂደት ይረዳል፡፡
16. በልጆች ላይ የሚከሰተውን የማያቋርጥ ሳል ለመከላከል ይረዳል፡፡
17. የእርጅናን ሂደትን በተወሰነ መልኩ ለመግታት ይረዳል፡፡
18. የአንጀት ውስጥ ትላትልና ተህዋስያንን ይገድላል፡፡
19. የምግብ ፍላጎትን ይጨምራል፡፡
20 በአብዛኛው በእድሜ ሳቢያ የሚከሰተውን ካታራክት የተሰኘውን የአይን እይታ ችግርን ለማከም ይረዳል፡፡
21 . የደም መርጋትን ለማሟሟት ይረዳል፡፡
22 . ለስኳር በሽታ ህክምና ይረዳል፡፡
23 . የጥርስ ህመም ስሜትን ይቀንሳል፡፡
24 . የእንቅልፍ እጦት ችግር ላለባቸው ይመከራል፡፡
25 . የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ይገነባል፡፡
26 . የእርሾ ኢንፌክሽንን ለማከም ይረዳል፡፡
27 . የመገጣጠሚያ አካላት በሽታን ለማከም ይረዳል፡፡
28 . በባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰተውን ስታፊሎኮካል ኢንፌክሽንን ለማከም ይረዳል፡፡
29 . ኪንታሮትን ለማከም ይረዳል፡፡
30 . የቆዳ ላይ ብጉንጅና እብጠቶችን ለማከም ይረዳል፡፡
31 . አንዳንድ የቆዳ በሽታዎችን ለማከም ይረዳል፡፡
32 . ለአንጀት ጤንነት ተመራጭ ነው፡፡
33 . ፋይቶንሳይድስ የተሰኘ ኬሚካል የሚገኝባቸው የነጭ ሽንኩርት ዓይነቶች የአስም በሽታን ለማከም ይረዳሉ፡፡
34 . አደገኛ የብሮንካይተስ ህመምን ለማከም ይረዳል፡፡
ለተጨማሪ neewict.com

🙏🙏🙏ለሌሎችም ያጋሩ 🙏🙏🙏

12/05/2025

The Narcissist’s Denial: “I Did Nothing to You”

A narcissist will hit you with everything in their arsenal—lies, betrayal, silent treatment, manipulation, threats, rage, gaslighting, and abandonment. One minute they’re promising the world, the next they’re punishing you for holding them accountable. They’ll isolate you, criticise you, accuse you of things they’re doing themselves, and dig at your deepest insecurities.

They don’t just hurt you—they confuse you. Twist reality. Make you question your own memory. You’ll find yourself apologising just to keep the peace, shrinking yourself to avoid another blow-up, and walking on eggshells in a relationship that feels more like survival than love.

And after all that? They’ll stand there, stone-faced and calm, and say, “I did nothing to you.”

That’s the final twist of the knife. The denial. The rewriting of history. Because if they admit what they’ve done, they lose control. So instead, they paint themselves as the victim and you as the problem.

But you’re not the problem. You’re the one who lived through their chaos and made it out the other side. Don’t let their denial erase your truth. You know what you felt. You know what you lived.

And you deserve peace, not a life built on gaslit pain.

For more information about understanding and overcoming narcissistic and emotional abuse, click the links below.

https://overcoming-narcissist-abuse.teachable.com/p/break-free-from-the-narcissist

Check these out!

Behind The Mask: The Rise Of The Narcissist

https://a.co/d/czX7KT2

15 Rules To Deal With Narcissistic People.: How To Stay Sane And Break The Chain.

https://www.amazon.com/gp/aw/d/B0BYRLLGRJ/ref=tmm_hrd_swatch_0?ie=UTF8&qid=1679325458&sr=8-1

A Narcissists Handbook: The ultimate guide to understanding and overcoming narcissistic and emotional abuse.

https://www.amazon.com/dp/B0C87NNBNP?ref_=cm_sw_r_mwn_dp_VKQZHN0VXE8W4WXTQQ20

Boundaries with Narcissists: Safeguarding Emotional, Psychological, and Physical Independence.

https://www.amazon.com/dp/B0CQ583RL8

Healing from Narcissistic Abuse: A Guided Journal for Recovery and Empowerment: Reclaim Your Identity, Build Self-Esteem, and Embrace a Brighter Future

https://amzn.eu/d/044yGFS8

(Sponsored.). https://betterhelp.com/elizabethshaw

Advertisements

A small number of coaching slots are currently available

overcoming-narcissist-abuse.teachable.com/p/private-1-2-1-coaching

12/05/2025

Narcissists thrive on control, deception, and the belief that they are always one step ahead. So, when you catch them in a lie—especially one they assumed you were too naïve, scared, or loyal to question—it hits them hard. Not because they’re ashamed or sorry, but because their illusion of control has just crumbled.

Being caught threatens their fragile ego. They’ll often respond with rage, denial, or deflection. You might be accused of “twisting things,” “being dramatic,” or even “making it up.” Suddenly, you’re the problem for daring to challenge the version of reality they worked so hard to create.

The narcissist’s anger in these moments is less about the lie itself and more about your refusal to accept it. Your awareness becomes a threat, and their priority shifts to regaining control—often through gaslighting, blame-shifting, or guilt-tripping.

But here’s the truth: questioning the lie is a powerful step. It’s the beginning of seeing through the mask. And that’s exactly why it enrages them.

For more information about understanding and overcoming narcissistic and emotional abuse, click the links below.

https://overcoming-narcissist-abuse.teachable.com/p/break-free-from-the-narcissist

Check these out!

Behind The Mask: The Rise Of The Narcissist

https://a.co/d/czX7KT2

15 Rules To Deal With Narcissistic People.: How To Stay Sane And Break The Chain.

https://www.amazon.com/gp/aw/d/B0BYRLLGRJ/ref=tmm_hrd_swatch_0?ie=UTF8&qid=1679325458&sr=8-1

A Narcissists Handbook: The ultimate guide to understanding and overcoming narcissistic and emotional abuse.

https://www.amazon.com/dp/B0C87NNBNP?ref_=cm_sw_r_mwn_dp_VKQZHN0VXE8W4WXTQQ20

Boundaries with Narcissists: Safeguarding Emotional, Psychological, and Physical Independence.

https://www.amazon.com/dp/B0CQ583RL8

Healing from Narcissistic Abuse: A Guided Journal for Recovery and Empowerment: Reclaim Your Identity, Build Self-Esteem, and Embrace a Brighter Future

https://amzn.eu/d/044yGFS8

(Sponsored.). https://betterhelp.com/elizabethshaw

Advertisements

A small number of coaching slots are currently available

overcoming-narcissist-abuse.teachable.com/p/private-1-2-1-coaching

የጥቁር አዝሙድ የጤና በረከቶችና አጠቃቀሙ🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🥁 ለካንሰርና እባጮችአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር...
27/03/2025

የጥቁር አዝሙድ የጤና በረከቶችና አጠቃቀሙ
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

🥁 ለካንሰርና እባጮች

አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከ አንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ ግማሽ ሠዓት በፊት ይጠቀሙ።

🥁 ለስኳር በሽታ

የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከተፈጥሮ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች በመጨመር ስኳርን በማቆም የአመጋገብ ለውጥ ያድርጉ።

🥁 ለተቅማጥ

አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ እርጎ ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ።

🥁 ለደረቅ ሳል

ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከቡና ጋር በመቀላቀል በቀን ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ። ጀርባዎና ደረትዎን በዘይት ይሹት።

🥁 ለጆሮ ሕመም

በስሱ የተቆላ አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ይውሰድ ከዚያም ጥቂት የኦሊቭ ዘይት ጠብታዎች በመጨመር በደንብ ይቀላቅሉት። ሰባት ጠብታ በሲሪንጅ ውስጥ ይክተቱ ከዚያም ጠዋት እና ማታ ጆሮዎ ውስጥ ይጨምሩ።

🥁 ለዓይን ሕመም እና ለዕይታ ችግር

ወደ መኝታ ከመሄድዎ ከግማሽ ሠዓት በፊት የዓይን ቆብዎን በጥቁር አዝሙድ ዘይት ይሹት። ግማሽ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ኩባያ የካሮት ጭማቂ ጋር በመቀላቀል ይጠጡ።

🥁 ለጉንፋን እና ፍሉ
አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት ይውሰድ። በእያንዳንዳቸው የአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ይጨምሩበት።

🥁 ለሃሞት ጠጠር እና ለጉበት ጠጠር

አንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝምድ ፍሬ ከማር ጋር በብርጭቆ ውስጥ ይቀላቅሉት ጥቂት ለብ ያለ ውሃ ይጨምሩበት። በመጨረሻም በመጨረሻም አንድ የሻይ ማንኪያ ዘይት ይጨምሩበት ይህን ውህድ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ይጠጡ።

🥁 ለአጠቃላይ ጤንነት እና ደህንነት

አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በየቀኑ ይጠቀሙ። ወይም ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት ከማር ጋር በመቀላቀል ከቁርስ በፊት በየቀኑ ይጠቀሙ።

🥁 ለፀጉር መሳሳት እና ያለ ዕድሜ ሽበት

በመጀመሪያ ፀጉርዎን ይታጠቡ ከዚያም በቂ የሆነ የኦሊቭ ዘይት ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር በመቀላቀል ይቀቡት። ከአንድ ሠዓት ቆይታ በኋላ ያለቅልቁት ወይም ይታጠቡት።

🥁 ለራስ ሕመም እና ማይግሬን

ከግንባርዎ ግራ ክፍል ትንሽ ዝቅ ብሎ ወይም ቴምፕል በሚባለው የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመቀባት ይሹት። ጥቂት ጠብታዎች በአፍንጫዎ ቀዳዳ እና ጭንቅላትዎ ላይ ያድርጉ። በቀን ሁለት ጊዜ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬና ማር ይብሉ።

🥁 ለማስታወስ ችሎታ

ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመቀላቀል በቀን ሶስት ጊዜ ይመገቡ።

🥁 ለአፍ ኢንፌክሽን ቫይረስ

ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ በአፍዎ ውስጥ ከ 10 - 15 ደቂቃ ይያዙት።

🥁 ለጡንቻ ሕመም

አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ከማር ጋር በመቀላቀል በቀን ለሶስት ጊዜ ይውሰድ። የቅልጥም መረቅ በየቀኑ ይጠጡ። የቻሉትን ያክል ዘቢብ በየቀኑ ይመገቡ።

🥁 ለሪህና ጀርባ ሕመም

የጥቁር አዝሙድ ዘይት ሞቅ በማድረግ የሚያምዎትን ቦታ ይሹት። በየቀኑ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ እና ማር ይመገቡ።

🥁 ለሆድ ሕመም

በአንድ ትልቅ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከማር ጋር በመቀላቀል ይጠቀሙ። ጥቂት የፔፐርሜንት ሻይ ይጠጡ ከዚያም የረሃብ ስሜት ከተሰማዎት የተቀቀለ ሩዝ ውሃ ይጠጡ።

🥁 ለጥርስ ሕመም እና ድድ ኢንፌክሽን

በኩባያ የሎሚ ጭማቂ በማድረግ ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ይጨምሩበት ከዚያም ያፍሉት። ከዚያም የፈላው ሎሚ ቀዝቀዝ ሲል በዚህ ውህድ ፈሳሽ አፍዎን ይጉመጥመጡበት/ይታጠቡበት።

🥁 ለሆድ ትላትል

ሁለት የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ፍሬ ከግማሽ ኩባያ ሎሚ ጋር በመቀላቀል ይህን ውህድ ያሙቁት። ከዚያም ቡርሽ ወይም ሌላ ነገር በመጠቀም የሆድና ጉበትዎን አካባቢ ይሹት።

🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹

ጤና ይስጥልን 👋

ምንጭ:- (ኢዜአ)

27/03/2025

ሰውነታችን 70% ውሃ መሆኑን ያውቁ ኖሯል?
ውሃ ለጤናችን ወሳኝ ነው። ለአብዛኞቹ የሰውነት ተግባራት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በሰውነትዎ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሕዋሳት፣ ቲሹዎች እና የአካል ክፍሎች በትክክል ለመስራት ውሃ ያስፈልጋቸዋል። ከጥቅሞቹም መካከል:
1. ✅የተሻሻለ የአንጎል ስራ፡ በሰውነት ውስት እስከ 2% ያህል ፈሳሽ ማጣት የማስታወስ ችሎታን፣ ስሜትን፣ ትኩረትን እና ምላሽን ሊጎዳ ይችላል። በዕለት ተዕለት ምግብዎ ውስጥ ጥቂት ብርጭቆ ውሃ ማከል በአእምሮ ስራ ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል።
2. ✅ለምግብ መፈጨት፡ ሰውነት ምግብን በትክክል ለመፍጨትና ለማዋሃድ ውሃ ይፈልጋል። በቂ መጠን ውሃ ካልተወሰደ መደበኛ ያልሆነ የአንጀት እንቅስቃሴ ፣ ጋዝ ፣ የሆድ መወጠር፣ ቃር እና ሌሎች ስሜቶች ሊሰማዎት ይችላል። የፈሳሽ መጠንን መጨመር የአንጀት ጤናን ሊያግዝ ይችላል። የምግብ መፍጨት ሂደትን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት ከምግብ ውስጥ የሚሟሟ ፋይበርን ለመስበርም ይረዳል።
3. ✅ተጨማሪ ጉልበት፡ የሰውነት ድርቀት የደም ዝውውር እንዲቀንስና ወደ አንጎል የሚሄደውን የኦክስጂን ፍሰት ሊጎዳ ይችላል። የፈሳሽ እጥረት ደግሞ ልብ በሰውነት ውስጥ ኦክሲጅንን ለመርጨት ብዙ ሀይል እንዲጠቀም ሊያደርግ ይችላል። ይህ ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለ ጉልበት ድካም ሊያመጣ ይችላል። ብዙ ውሃ በመጠጣት ብቻ የሰውነት ድርቀትን በመከላከል ነቃ ብሎ መዋል ይችላሉ።
4. ✅ክብደት ለመቆጣጠር፡ ብዙ ውሃ መጠጣት የጥጋብ ስሜት ስለሚሰጥ ብዙ ምግብ እንዳይመገቡ ሊረዳዎት ይችላል። እንዲሁም ሜታቦሊዝምን ከፍ ለማድረግ ይረዳል።
5. ✅የመገጣጠሚያ ህመም ለመቀነስ፡ በመገጣጠሚያዎቻችን ውስጥ ያለው አጥንትን የሚጠብቀው አካል 80% ውሃ ይይዛል። ስለሆነም ውሃ በብዛት መውሰድ መገጣጠሚያ በደንብ እንዲለሰልሱ ይረዳል፣ ይህም በአጥንቶች መካከል ብዙ ጠባቂ በመፍጠር ግጭትን ለመቀነስ ይረዳል። ያነሰ ግጭት ማለት መገጣጠሚያዎች እንድዲለሰልሱና ህመም እንዳይኖር ያደርጋል።
6. ✅የሙቀት መቆጣጠሪያ ስርአት፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰውነት ፈሳሽ በሚቀንስበት ጊዜ ሰውነት ብዙ ሙቀትን ያከማቻል። ይህ ደግሞ የሙቀት መጠንን የመቋቋም ችሎታዎን ይቀንሳል። ብዙ ውሃ መጠጣት በእንቅስቃሴ ላይ ከመጠን በላይ ሙቀት በሚፈጠርበት ጊዜ ላብ እንዲፈጠር ይረዳል። ይህ ደግሞ ሰውነትን ያቀዘቅዛል። ይህ የማቀዝቀዣ ዘዴ የሙቀት ስትሮክንና ሌሎች ገዳይ ሊሆኑ የሚችሉ ከሙቀት ነክ ሁኔታዎችን ለመከላከል ወሳኝ ነው።
7. ✅የኩላሊት ጠጠርን መከላከል፡ የኩላሊት ጠጠር በሽንት ቱቦ ውስጥ የሚፈጠሩ የማዕድን ክሪስታል ክምችቶች ናቸው። በየቀኑ በቂ መጠን ያለው ውሃ መውሰድ በሽንት ቱቦ ውስጥ ያለውን የማዕድን ክምችት እንዲቀንስና የጠጠሮች ክምችት እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። ውሃ ጎጂ የሆኑ ባክቴሪያዎችን ከፊኛ ውስጥ በማስወጣት የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽንን (UTI) ለመከላከል ይረዳል።
8. ✅ጤናማ ልብ፡ ደም በአብዛኛው ከውሃ የተሰራ ነው። በቂ ውሃ በማይጠጡበት ጊዜ የአስፈላጊ ማዕድናት (ኤሌክትሮላይቶች) አለመመጣጠን ያስከትላል። እንደ ፖታሲየምና ሶዲየም ያሉ ማዕድናት ለልብዎ ትክክለኛ አሠራር ቁልፍ ናቸው።
9. ✅ተረፈ ምርት ለማስወገድ፡ በቂ ውሃ መውሰድ የሰውነትዎን ተፈጥሯዊ ተረፈ ምርት የማስወገድ ስርዓትን ይደግፋል ይህም ቆሻሻንና ጎጂ ንጥረ ነገሮችን በሽንት፣ በትንፋሽ፣ በላብ እና በሰገራ መልክ ያስወግዳል። አጠቃላይ ጤናን ለማሻሻል ይረዳል።
10. ✅ራስ ምታትን ለመቀነስ፡ ቀላል የፈሳሽ ማነስ አንጎል ከራስ ቅል እንዲርቅ ስለሚያደርግ ራስ ምታትና ማይግሬን ያስከትላል። ውሃ በደንብ መጠጣት የጭንቅላት ህመምን ለመቆጣጠር ይረዳል።
11.✅ ለአጠቃላይ የቆዳ ጥራትና ጤና

➡️በአጠቃላይ ዉሃ መጠጣት ለጤናችን እጅግ አስፈላጊ ነው። በቀላሉ ዉሀ ለመጠጣት እንዲረዳን የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ እንችላለን።
⚡️ዉሃ እስኪጠማን አለመጠበቅ
⚡️በቻልነው አቅም በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ዉሃ ይዘን መንቀሳቀስ
⚡️ብቻውን ለመውሰድ የሚከብደን ከሆነ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በመጠኑ ጨምረን መጠቀም 🍋🍓🥒

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 🤙+251935402078 በተጨማሪም በአጭር የስልክ መስመራችን 🤙9000 ቢደውሉ ያገኙናል ።
አድራሻችን : ሰፈረ ሰላም

27/03/2025
27/03/2025

ማርን ለአስም በሽታ በቤት ውስጥ እንዴት እንጠቀመው?
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

✴️ (4 የአጠቃቀም ዘዴዎች) ሼር ሼር ✴️

🥁 ማር እና አዝመሪኖ
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉 አዘገጃጀት | Preparation
➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖

በመጀመሪያ በአንድ የሻይ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አዝመሪኖ (የጥብስ ቅጠል) ቀላቅሎ ማፍላት፡፡

ከዚያም በደንብ ከተንተከተከ በኋላ ከእሳቱ ላይ በማውረድ ለጥቂት ደቂቃዎች እንዲቀዘቅዝ ማድረግ፡፡

በአዝመሪኖ ወይም የጥብስ ቅጠል ውሃ ላይ አንድ ማንኪያ ማር ጨምሮ መበጥበጥ፤ ከዚያም መጠጣት።

ይህ ፈሳሽ ወይም ውህድ አስም ላለባቸው ሰዎች ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

ይህን ውህድ በቀን ሁለት ጊዜ ወስደው ካልተሻለዎት ወይም ለውጥ ከሌለዎት፤ መጠኑን በመጨመር በቀን ከሶስት እስከ ስምንት ጊዜ መውሰድ ይቻላል፡፡

🥁 ማርና ነጭ ሽንኩርት
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉 አዘገጃጀት | Preparation
➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖

ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት ወስዶ በሚገባ አድቅቆ መፍጨት፡፡

የተፈጨውን ነጭ ሽንኩርት ከአንድ ማንኪያ ማርጋር መለወስ፡፡

በመቀተልም ይህንን ጠዋትና ማታ በቀን ሁለት ጊዜ ለአስራ አምት ቀናት ያህል መውሰድ፡፡

ይህ ውህድ የሚወሰደው በተለይ የአስም ህመም በሚነሳበት ወይም በተቀሰቀሰበት ሰሞን ከሆነ ፍቱንነቱንና ፈዋሽነቱንበሚገባ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

🥁 ማር እና ቀረፋ
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉 አዘገጃጀት | Preparation
➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖

አንድ ማንኪያ ማር እና ግማሽ ማንኪያ የቀረፋ ዱቄት አብሮ መለወስና በቀን 3 ጊዜ እንደ እንክብል መውሰድ፡፡

🥁 ማር፣ ነጭ ሽንኩርት እና የተነጠረ ቅቤ
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉 አዘገጃጀት | Preparation
➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖

🐝 7 ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
🐝 10 ማንኪያ የተነጠረ ቅቤ
🐝 12 ማንኪያ ማር

በአንድ ጎድጓዳ እቃ ውስጥ ማደባለቅ እና ለብ እስኪል ድረስ (በመጠኑ) ማሞቅ፡፡

በመቀጠልም ጥብቅ ክዳን ባለው ጠርሙስ ውስጥ መገልበጥ፡፡

ይህንን ውህደት በየቀኑ ከምግብ በፊት የአስሙ ሁኔታ አመርቂ ለውጥ እስኪያሳይ ድረስ መውሰድ።

(በነገራችን ላይ ማርን ከመጠን በላይ ማሞቅ አይመከርም፤ ምክንያቱም ማር ከሚገባው በላይ በእሳት ከተመታ ወይም ከሞቀ በውስጡ ያሉት ጠቃሚ ንጥረ-ነገሮች ከጥቅም ውጭ ስለሚሆኑ ነው)።

🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢

ጤና ይስጥልን 👋

ለበለጠ የጤና መረጃ የማህበረሰብ ትስስር ገጾቻችንን ይጎብኙ!

ወደ ገጾቻችን ለመግባት የሚከተለውን ሊንክ ጠቅ ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

27/03/2025

የኦቾሎኒ ቅቤ የሚሰጠን የጤና ጥቅሞች
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

የኦቾሎኒ ቅቤ ከተፈጨ ኦቾሎኒ የሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ጣፋጭ እና በንጥረ-ምግቦች የተሞላ ምግብ ነው።

በጤናማ ስብ፣ ፕሮቲን፣ ቫይታሚኖች እና ማዕድናት የበለፀገ ሲሆን፤ የልብ ጤንነትን መደገፍ፣ ክብደትን መቆጣጠር፣ እና ቀጣይነት ያለው ሃይልና ጉልበትን መለገስ ያሉ በርካታ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል።

🦚 የጤና ጥቅሞች
🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿🚣🏿

👉👉 የኦቾሎኒ ቅቤ ለጤና ጠቃሚና አስፈላጊ ከሆነባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል 🥜✨

🛎️ የኦቾሎኒ ቅቤ ቫይታሚን ኢ፣ ማግኒዝየም፣ ፖታሲየም እና ቫይታሚን ቢ6ን ጨምሮ የበርካታ ቫይታሚኖችና ማዕድናት መገኛ ምንጭ ነው።

እነዚህ ንጥረ-ነገሮች ለተለያዩ የሰውነት ተግባራት ወይም ሥራዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።

ከእነዚህም መካከል ኃይልና ጉልበትን ማምረት፣ ጡንቻዎቻችን ተግባራቸውን በትክክል እንዲወጡ፣ እና ጤናማ ቆዳ እንዲኖር ማድረግ ይገኙበታል።

🧫 በውስጡ ሞኖውንሳቱሬትድ እና ፖሊ-አንሳቹሬትድ ፋቶችን የያዘ ሲሆን፤ እነዚህ ቅባቶች ወይም ፋቶች ለልብ ጤናማ ተደርገው ይቆጠራሉ።

እነዚህ ቅባቶች መጥፎ የኮሌስትሮል መጠን (LDL) እንዲቀንስ እንዲሁም ጥሩ የኮሌስትሮል መጠን (HDL) እንዲጨምር በማድረግ፤ ለልብ ህመም ያለንን ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳሉ።

🛁 የኦቾሎኒ ቅቤ ህብረህዋሳትን ለመገንባትና ለመጠገን፣ ኢንዛይሞችን እና ሆርሞኖችን ለመሥራት፣ እንዲሁም አጠቃላይ እድገትንና ለውጥን ለመደገፍ በጣም አስፈላጊ የሆነ ከፍተኛ መጠን ያለውን ፕሮቲን ይሰጠናል።

🧻 ኦቾሎኒ እንደ ሬስቬራትሮል፣ ኮመሪክ አሲድ እና ፋይቶስትሮል (resveratrol, coumaric acid and phytosterols) ያሉ ባዮአክቲቭ ውህዶችን የያዘ ሲሆን እነዚህ ውህዶች አንቲኦክሲዳንት ባህሪያት አሉት።

አንቲኦክሲደንቶች የኦክሲዴቲቭ ውጥረትን (oxidative stress) ለመቋቋም የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ፤ ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳል።

🧽 የኦቾሎኒ ቅቤ በካሎሪ የታጨቀ ቢሆንም፤ የሰውነት ክብደትን ለመቆጣጠር የሚረዳ የዕቅድ አካል ሊሆን ይችላል።

የፕሮቲንና የፋይበር ይዘቱ ረዘም ላለ ጊዜ የመጥገብ ወይም የመርካት ስሜት እንዲሰማን ስለሚያደርግ፤ ከመጠን በላይ የመብላት አጋጣሚን ይቀንሳል።

🧼 በኦቾሎኒ ቅቤ ውስጥ ያለው ጤናማ ቅባትና ፋይበር ወደ ደም ውስጥ የሚገባውን የስኳር መጠን እንዲቀንሱ በማድረግ፤ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ያስችላል።

ይህ በተለይ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።

🥁 አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የኦቾሎኒ ቅቤ አዘውትሮ መመገብ በሐሞት ጠጠር የመያዝን አጋጣሚ ይቀንሳል።

ይህም በኮሌስትሮል መጠን ላይ ባለው በጎ ተጽእኖ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

🥧 በኦቾሎኒ ቅቤ ውስጥ ያለው የፕሮቲን ይዘት ለአትሌቶች ወይም ጡንቻቸውን መገንባት ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ መክሰስ ያደርገዋል።

በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካከናወንን በኋላ ጡንቻዎች እንዲያገግሙ ይረዳል።

🧁 የኦቾሎኒ ቅቤ ማግኒዝየም ስላለው ለአጥንት ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው።

ማግኒዥየም ከካልሲየም ጋር በአንድነት በመስራት ጠንካራ አጥንትን ለመገንባት እና ኦስቲዮፖሮሲስን ለመከላከል ይረዳል።

🍜 የፕሮቲን፣ የስብ እና የፋይበር ውህደት ዘላቂነት ያለው የኃይል ምንጭ እንዲሰጠን ያደርጋል።

ይህም የኦቾሎኒ ቅቤ ከቅድመ ወይም ከድህረ አካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ ጥሩ የመክሰስ ምርጫ ያደርገዋል።

🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮🥮

የኦቾሎኒ ቅቤ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት። በውስጡ ያለው የካሎሪ መጠን ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ፤ በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚመጣ ስኳር (added sugar) እና ጤናማ ያልሆነ ቅባት ሊይዝ እንደሚችል ልብ ማለት ያስፈልጋል።

የጤና ጥቅሞቹን ከፍ ለማድረግ ወይም ለመጨመር፤ ምንም አይነት በፋብሪካ ተቀነባብሮ የሚጨመር ስኳር (added sugar) ወይም ሃይድሮጂኔትድ ዘይት የሌለው የተፈጥሮ የኦቾሎኒ ቅቤን ይምረጡ፤ እንዲሁም የተወሰነ መጠን ብቻ መመገብ እንዳለብዎት ልብ ይበሉ።

🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢🚢

ጤና ይስጥልን 👋

ለበለጠ የጤና መረጃ የማህበረሰብ ትስስር ገጾቻችንን ይጎብኙ!

ወደ ገጾቻችን ለመግባት የሚከተለውን ሊንክ ጠቅ ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

የቴምር 10 ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው1. የደም ማነስ ካለብዎት በሚገባ ያድንዎታል።2. ለአይን ጤንነት እና አይንን ከመታወር ይታደጋል።3. ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን ነው።4. የሆ...
27/03/2025

የቴምር 10 ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው

1. የደም ማነስ ካለብዎት በሚገባ ያድንዎታል።
2. ለአይን ጤንነት እና አይንን ከመታወር ይታደጋል።
3. ለስንፈተ ወሲብ ፍቱን ነው።
4. የሆድ ድርቀትን ይከላከላል/ይፈውሳል፤ እንዲሁም ተቅማጥን ይከላከላል።
5. ክብደትን ለመጨመር ይረዳል።
6. ጤናማ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል።
7. ጉልበት/ኃይል ይሰጠናል ወይም እንዲጨምር ያደርጋል።
8. ጤናማ የሆነ የነርቭ ስርዓት እንዲኖረን ያደርጋል።
9. ጥርሳችን ጤናማ እና ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል።
10. ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚ ነው።

ቴምር እና ጤና በዝርዝር ስንመለከታቸው

በርካቶቻችን በብዛት የምንጠቀመው እና በተለይም በረመዳን ጾም ወቅት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚዘወተረው ቴምር በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት። በቫይታሚን፣ ማዕድናትና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዲኖሩት አስችሎታል፡፡

የቴምር የጤና በረከቶች

1. ስብና ኮልስትሮል፡- ከየትኛውም የኮልስትሮል ዓይነቶች የጸዳና በጣም አነስተኛ የስብ መጠን ያለው መሆኑ ክብደት መቀነስ ለሚፈልጉ ተመራጭ ነው፡፡

2. ፕሮቲን፡- ቴምር በፕሮቲንና አስፈላጊ ማዕድናት የበለጸገ መሆኑ ለሰውነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል፡፡

3. ቫይታሚን፡- በቫይታሚን የበለጸገ ነው ቴምር፡ ፡ ከቫይታሚን ዓይነቶች ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ3፣ ቢ5፣ ኤ1 እና ሲ ንም አካትቶ ይዟል፡፡

4. ሀይል እና ጉልበት፡- ቴምር ቀላል የማይባል የሀይል ክምችት ስላለውም ንቁና በሀይል የተሞላን እንድንሆን ያስችለናል፡፡

5. ፖታሲየምና ካልሲየም፡- ቴምር የፖታሲየም ክምችቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም በልብ በሽታ እንዳንጠቃና አካላችን ውስጥ ያለው የኮልስትሮል መጠን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡ ቴምር በአንጻሩ አነስተኛ የሶዲየም መጠን ነው ያለው፡፡ ብዙ ፖታሲየምና ትንሽ ሶዲየም ደግሞ ለጤናማ የነርቭ ስርዓት ወሳኝ ነው፡፡

6. ብረት፡- ቴምር በብረትና በፍሎሪን የበለጸገ መሆኑ ደግሞ ብረቱ የብረት ማዕድን እጥረት ላለባቸው ሰዎች፣ ፍሎሪኑ ደግሞ ጥርስን ከመበስበስ ይከላከላል፡፡

7. ድርቀት፡- ለድርቀትም ቢሆን ውሃ ውስጥ የተነከረ ቴምር መመገብ ፍቱን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

8. ሰውነትን ማጽዳት፡- በአልኮል መጠጣት ሳቢያ ሰውነት ውስጥ የሚከማቸውን መርዛማ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድም ይረዳል፡፡

9. ካንሰር እና የዓይን ችግር፡- የዓይን ህመም ችግርንና የሆድ ነቀርሳ (ካንሰር)ን ለማከምም ብቃት እንዳለው ይታወቃል – ቴምር፡፡

10. የቆዳ ችግር፡- ቴምር የቆዳ ችግሮችን በማስወገድም መልካም ዝና አለው፡፡ ጸጉርን በማፋፋት የጸጉር መሳሳትንም ይከላከላል፡፡

በርከት ያሉ ቪታሚኖችን እና ማዕድናትን በመያዙ ለጤናችን በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይነገርለታል። ሀይል ሰጪ፣ ፋይበር፣ እንዲሁም ካልሺየም፣ አይረን፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ማግኒዚየም፣ እና ዚንክ ሚኔራሎች በቴምር ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ቴምርን ለጤና ጠቃሚ ያደርጉታል።

ስለዚህም ቴምርን አዘውትረን መመገብ ለጤናችን ከሚሰጠው ጠቀሜታዎች ውስጥም፦

• የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡- ቴምር በባህሪው የማለስለስ ባህሪ ስላለው ምግብ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ እንዲዘዋወር በማድረግ የሆድ ድርቀት ለመከላከል ይረዳል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ ቴምሩን በውሃ ውስጥ ዘፍዝፈን በማሳደር ጠዋት ላይ መመገብ ይመከራል።

• ለአጥንት ጤንነት እና ጥንካሬ፡- በቴምር ውስጥ የሚገኙት ማዕድናት ለአጥንታችን ጥንካሬ እና ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ እንደሆኑ ይነገራል። Selenium, Manganese etc..

25/03/2025

የቀረፋ የጤና ጥቅሞች | Health Benefits of Cinnamon
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

ቀረፋ ሲናይሞመም (Cinnamomum) የሚባል ዝርያ ካላቸው ዛፎች የውስጠኛው የቅርፊት ክፍል የሚገኝ ቅመም ነው።

ብዙውን ጊዜ ሽታቸው ከሩቅ የሚጠራ እና የሚጣፍጡ ምግቦችን ለማዘጋጀት ይጠቅማሉ።

በተጨማሪም እንደ ወይን ወይም ሳይደር (Mulled Wine or Cider) ያሉ መጠጦችን ለማዘጋጀት ያገለግላል።

➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖

✅ የቀረፋ የጤና ጥቅሞች
🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️

👉👉 ቀረፋ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት፤ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-

1️⃣ ፀረ-ኦክሲደንት ባህሪያት | Antioxidant properties!

ቀረፋ በፀረ-ኦክሲዳንቶች የበለፀገ ነው። ይህም ሰውነታችን በፍሪ-ራዲካሎች ከሚደርስበት የኦክሲዴቲቭ ጉዳት (oxidative stress) ለመከላከል ይረዳል።

2️⃣ ፀረ-ኢንፍላማቶሪ ውጤቶች | Anti-inflammatory effects!

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀረፋ ኢንፍላሜሽንን ለመቀነስ ይረዳል። ይህም የአርትራይተስ በሽታ ላለባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጥቅምን ይሰጣል።

3️⃣ የልብ ጤናን ማሻሻል | Improved heart health!

ቀረፋ የኮሌስትሮል መጠንን እና የደም ግፊትን በመቀነስ፤ ለልብ ህመም ያለንን ተጋላጭነት ይቀንሳል።

4️⃣ የደም ስኳር መጠንን መቆጣጠር | Better blood sugar control!

ቀረፋ የኢንሱሊን ሴንሲቲቪቲን (insulin sensitivity) እንደሚያሻሽል እና የደም ስኳር መጠንን ዝቅ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል።

ይህ ደግሞ የስኳር በሽታ ወይም ኢንሱሊንን የመቋቋም ችግር ላላቸው ሰዎች ጠቃሚ ነው።

5️⃣ ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያት | Antimicrobial properties!

ቀረፋ ፀረ-ተሕዋስያን ባህሪ ያላቸው ውህዶችን የያዘ ሲሆን፤ ይህም ኢንፌክሽንን ለመዋጋት እና የባክቴሪያ እና የፈንገስ እድገት ለመግታት ይረዳል።

6️⃣ ካንሰርን ይከላከላል | Potential cancer prevention!

ቀረፋ የካንሰር ህዋሳት እድገትንና ስርጭትን ለመከላከል ሊረዳ እንደሚችል አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

ይህንን ጥቅም ለማረጋገጥ ግን ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ።

7️⃣ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባርን ማሻሻል | Improved cognitive function!

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀረፋ ነርቮችን የመከላከል ባህሪያቶች አሉት።

ይህም የማስታወስ ችሎታን፣ ትኩረት መስጠትን እና አጠቃላይ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባርን ለማሻሻል ይረዳል።

8️⃣ ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል | Support for weight management!

ቀረፋ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዲስተካከል እና የምግብ ፍላጎት እንዲቀንስ ይረዳል።

ይህም የጥጋብ ስሜትን በመጨመር እና ከመጠን በላይ መብላትን በመከላከል ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል።

9️⃣ የምግብ መፍጫ ሥርዓት ጤንነት | Digestive health!

ቀረፋ ለምግብ መፈጨት እና የምግብ መፍጨት ሥርዓት ህመምን ለማስታገስ በባህላዊ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል።

ጋዝን፣ የሆድ መነፋትን እና የምግብ አለመፈጨት ችግርን ለመቀነስ ይረዳል።

🔟 ፀረ-ካንሰር ባህሪያት | Potential anti-cancer effects!

አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቀረፋ የፀረ-ካንሰር ባህሪያቶች አሉት።

ከእነዚህም መካከል የካንሰር ሕዋሳትን እድገት መግታት እና አፖፕቶሲስን (የሴል ሞትን) በካንሰር ሕዋሳት ላይ ማነሳሳትን ያካትታል።

1️⃣1️⃣ የቆዳ ጤንነት | Skin health!

ቀረፋ በባህላዊ መድኃኒትነት ለፀረ-ኢንፍላሜሽን እና ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያቱ ጥቅም ላይ ይውላል።

ይህም የቆዳ ጤንነትን ለማሻሻል እና እንደ ብጉር እና ኤክማ ያሉ ችግሮችን ያስወግዳል።

👉👉 በአጠቃላይ ቀረፋን በምግብ ገበታችን ውስጥ ማካተት ብዙ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል፤ ሆኖም ግን እንደ የተመጣጠነ ምግብ እና የአኗኗር ዘይቤ አካል አድርጎ መውሰድ ወይም መጠቀም አስፈላጊ ነው።

🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋🚋

ጤና ይስጥልን 👋

ምንጮች | Sources!
➖➖➖➖➖➖➖
National Institutes of Health (NIH), Mayo Clinic, WebMD & Medical News Today

ለበለጠ የጤና መረጃ የማህበረሰብ ትስስር ገጾቻችንን ይጎብኙ!

ወደ ገጾቻችን ለመግባት የሚከተለውን ሊንክ ጠቅ ያድርጉ!

👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://linktr.ee/ethiotena

#ቀረፋ #ኢትዮጤና

Address

Hirnoye
Addis Ababa
2957

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hirnoye Foodstuffs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share