14/09/2025
📌 !
▸ በሌሎች ለመወደድ ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ ምንም ሰራህ ምን ሁሌም ድርጊትህን የሚቃወሙ ሰዎች መኖራቸው አይቀርም።
▸ መርዘኛ ባህሪ ያላቸው ሰዎችን አስወግድ፦ መልካም አመለካከት የሌላቸውን ሰዎች በዙሪያ ይዞ ስኬታማ መሆን አይቻልም።
▸ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ የተወሰኑ ነገሮች ለኛ አብዛኞቹ ደሞ ለኛ እንዳልሆኑ መረዳት ።
▸ ሁሌም ፍፁም ለመሆን ያለህን ፍላጎት አስወግድ፦ ፍፁም ለመሆን ማሰብ ባንተ ላይ ከፍተኛ ግፊት ያሳድራል ስለሆነም በተግባርህ ጥሩ ከሆንክ ይበቃል።
▸ በፍጥነት ስኬት ላይ ለመድረስ ያለህን እምነት አስወግድ (Overnight Success)፦ ስቲቭ ጆንስን ጨምሮ ማንም በአንዴ ስኬታማ የሆነ የለም።
▸ ትንንሽ ህልሞችን አስወግድ፦ ራዕይህ ትልቅ ካልሆነ መቼም ትልቅ ነገር አታሳካም።
▸ ጤናማ ያልሆኑ የህይወት መንገዶችን አስወግድ፦ አካልህ ቤትህ ነው ስለሆነም ስኬትህ ላይ ለመድረስ ጤናማ መሆን አለብህ።