Deborah Foundation

Deborah Foundation A child with special needs will inspire you to be a special person.
(1)

በኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ፣ አንድ የጋራ ራዕይ። 🇪🇹🤝🇨🇳✨የ ሀንድስ ኤንድ ስታርስ ፕሮጀክት መሪ የሆኑት ማስተር ቼንግ ሊፋንግ፣ አቶ ሁ ፋንግሊን እና አቶ ዠን ሁዋናን ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር በ...
18/09/2026

በኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ፣ አንድ የጋራ ራዕይ። 🇪🇹🤝🇨🇳✨

የ ሀንድስ ኤንድ ስታርስ ፕሮጀክት መሪ የሆኑት ማስተር ቼንግ ሊፋንግ፣ አቶ ሁ ፋንግሊን እና አቶ ዠን ሁዋናን ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለ6ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ።

በእደ ጥበብ ስልጠና የጀመረው ይህ ትብብር ዛሬ ክህሎትን ለማዳበር እና ዘላቂ የእድል ፈጠራን የሚያጠናክር ጉዞ ሆኗል።

ወደፊት አዳዲስ ገበያዎችን ለመድረስ፣ ጠንካራ ወዳጅነትን ለመፍጠር እና በመጋቢት 2027 ቤጂንግ ውስጥ ኤግዚቢሽን ለማካሄድ ያለውን እድል በመመልከት፣ ችሎታን ወደ እድል የመቀየር ተልዕኮአችንን እንቀጥላለን።

ጉዟችን ይቀጥላል።

Sixth time in Ethiopia, one shared vision. 🇪🇹🤝🇨🇳✨

Honored to welcome Master Cheng Lifang, Mr Hu Fanglin and Mr Zhen Huanan back to Ethiopia for the 6th time for the HANDS & STARS Public Welfare Project, in collaboration with the Deborah Foundation.

What began as a craft-training initiative is growing into a journey of skills, inclusion, empowerment, and sustainable opportunity for people with intellectual disabilities.

As we look ahead to new markets, deeper partnerships, and a potential Beijing exhibition in March 2027, we remain committed to turning ability into opportunity. ✨

The journey continues.

2 ሚሊዮን ብር የተስፋና የለውጥ ስጦታ!ለዚህ አስደናቂ የአዲስ ዓመት ስጦታ እና ከዲቦራ ፋውንዴሽን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከጎናችን ስለቆያችሁ ኢትዮ ቴሌኮም ከልብ እናመሰግናለን። የገቢ ማሰ...
15/09/2026

2 ሚሊዮን ብር የተስፋና የለውጥ ስጦታ!

ለዚህ አስደናቂ የአዲስ ዓመት ስጦታ እና ከዲቦራ ፋውንዴሽን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከጎናችን ስለቆያችሁ ኢትዮ ቴሌኮም ከልብ እናመሰግናለን።

የገቢ ማሰባሰቢያ አጭር ቁጥራችንን ከመደገፍ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ከማቅረብ፣ ዳውን ሲንድሮም ላላቸው ምሩቃችን የሥራ ዕድል ከመፍጠር፣ ግንዛቤን ከማስፋፋት እስከ ተማሪዎቻችንን በማዕከላችሁ በደስታ እስከመቀበል ኢትዮ ቴሌኮም አጋርነት ወደ ተጨባጭ ለውጥ እንደሚቀየር በተግባር አሳይታችኋል።

በልጆቻችን ስላመናችሁ፣ ለእኩልነትና ስላበረከታችሁ እና ለልጆቻችን የተሻለ የወደፊት ተስፋ ለመፍጠር ከጎናችን ስለቆማችሁ እናመሰግናለን።

አብረን ስንሠራ፣ ተስፋን ወደ ለውጥ እንቀይራለን።

❤️ 2 Million Birr of hope and impact!

A heartfelt thank you to Ethio Telecom for this generous New Year donation and for standing beside Deborah Foundation since our very beginning.

From our fundraising short code, school supplies, and employment opportunities for our graduates with Down syndrome, to creating awareness and welcoming our students at their centers Ethio Telecom has consistently turned partnership into impact.

Thank you for believing in inclusion and investing in our children’s future. 🇪🇹❤️

ያለፈውን ዓመት ስንቋጭ፣ እንደ ድርጅት ያከናወናቸውን ነገሮች ሁሉ በማሰብ በምስጋና ተሞልተናል። እነዚህ ፎቶዎች የፈጠርነውን አዎንታዊ ለውጥ የሚያሳዩት በከፊል ነው። አዲስ አመት የእድገት እ...
11/09/2026

ያለፈውን ዓመት ስንቋጭ፣ እንደ ድርጅት ያከናወናቸውን ነገሮች ሁሉ በማሰብ በምስጋና ተሞልተናል። እነዚህ ፎቶዎች የፈጠርነውን አዎንታዊ ለውጥ የሚያሳዩት በከፊል ነው። አዲስ አመት የእድገት እና ለውጥ እንዲሆን እንመኛለን። መልካም አዲስ ዓመት!

As we close the chapter on another year, we're filled with gratitude reflecting on all that we've accomplished as an organization. These photos only capture a glimpse of the lives we've been able to touch, the communities we've helped, and the positive change we've created.This vital work was made possible not only by your unwavering support, but also by the incredible partnerships we’ve forged this year. Here's to a new year of growth, opportunities, and making an even bigger difference. Happy New Year!

🇹🇷❤️🇪🇹 ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ፦ ለበጎ ዓላማ በጋራ ለመቆም ካለ ፅኑ ቁርጠኝነት ጋር!​የ TİKA የበጎ ፈቃደኛ የሕክምና ባለሙያዎች ተማሪዎቻችንን በመጎብኘት፣ ትርጉም ያለው ጊዜ አብረዋቸው...
10/09/2026

🇹🇷❤️🇪🇹 ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ፦ ለበጎ ዓላማ በጋራ ለመቆም ካለ ፅኑ ቁርጠኝነት ጋር!

​የ TİKA የበጎ ፈቃደኛ የሕክምና ባለሙያዎች ተማሪዎቻችንን በመጎብኘት፣ ትርጉም ያለው ጊዜ አብረዋቸው በማሳለፍ እና ለዲቦራ ፋውንዴሽን ስላደረጉት ለጋስ ከልብ እናመሰግናለን። 🫂❤️

​TİKA የተማሪዎቻችንን ሕይወት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁልጊዜም አጋራችን ነቸው፤ በ2025 የተማሪዎቻችን የጨዋታ ቦታ ጥላ በመገንባት ለልጆቻችን ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የመማሪያና የመጫወቻ ቦታ እንድናዘጋጅ ላደረገልን ድጋፍ ትልቅ ምስጋና አለን።

​በልጆቻችን ስለተማመናችሁ እናመሰግናለን TİKA! ❤️

🇹🇷❤️🇪🇹 From Türkiye to Ethiopia, with kindness, care, and a shared commitment to inclusion.

We are deeply grateful to the TİKA medical professional volunteers for visiting our students, spending meaningful time with them, and generously donating to the Deborah Foundation. 🫂❤️

TİKA has been a valued partner in making our students’ lives better, including supporting the construction of our playground shade structure in 2025—creating a safer, more comfortable space for our children to learn and play.

Thank you, TİKA, for believing in our children and standing with us for a more inclusive future. ❤️

የጥርስ ጤና ምርመራ ቀን በዲቦራ ፋውንዴሽንሀምሌ 25 ቀን 2018 በዲቦራ ፋውንዴሽን የባቢ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ የህክምና ባለሙያዎች በመገኘት ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር ለተ...
06/08/2026

የጥርስ ጤና ምርመራ ቀን በዲቦራ ፋውንዴሽን

ሀምሌ 25 ቀን 2018 በዲቦራ ፋውንዴሽን የባቢ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ የህክምና ባለሙያዎች በመገኘት ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር ለተወለዱ ህጻናት የጥርስ ጤና ምርመራ አድርገዋል። ለእነዚህ ህጻናት አስፈላጊውን የጥርስ ህክምና ምርመራ እና እንክብካቤ በማድረግ ከጎናችን ለቆሙት የባቢ ስፔሻሊቲ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ባለሙያዎች እና ቡድን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Dental Check-Up at Deborah foundation

On August 1, 2026, a team from Babi Speciality Dental Clinic visited Deborah Village in Legatafo to provide essential dental health check-ups for children with Down syndrome and other intellectual disabilities. The visit was dedicated entirely to comprehensive dental examinations and preventive oral care. We extend our sincere thanks to the dedicated Babi team for their commitment to early detection, oral healthcare, and well-being for our children. We present our heartfelt gratitude to Babi Speciality Dental Clinic for helping us in our mission.

አረንጓዴ አሻራ በዲቦራ ፋውንዴሽን​ዛሬ በዲቦራ መንደር የተካሄደውን የታላቁ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በታላቅ ደስታ አከናውነናል!​የዛሬው መርሃ ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 8...
03/08/2026

አረንጓዴ አሻራ በዲቦራ ፋውንዴሽን

​ዛሬ በዲቦራ መንደር የተካሄደውን የታላቁ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በታላቅ ደስታ አከናውነናል!

​የዛሬው መርሃ ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ያቀደችውን ታላቅ ብሔራዊ ግብ ለማሳካት የተከናወነ ሲሆን፣ የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ሰራተኞች እና ውድ አጋሮቻችን በጋራ በመሆን አሻራችንን አኑረናል።

​ለቀጣዩ ትውልድ የሚሆን የተሻለች፣ የጸናች እና አረንጓዴ ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት በምናደርገው በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ከጎናችን ለነበራችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን!

Today, we proudly gathered at Deborah Village for our annual tree-planting event as part of Ethiopia’s national Green Legacy initiative!

​The founder of Deborah Foundation H.E Abadula Gemeda, our students, parents, staff, and dedicated partners stepped up to leave a lasting mark for generations to come. We contributed our part toward the ambitious nationwide target of planting 800 million seedlings in a single day.

​Thank you to everyone who joined hands with us today to nurture our environment, support sustainability, and build a brighter future for our children.

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የዲቦራ ፋውንዴሽን ቡታጅራ ቅርንጫፍን ጎበኙየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፣ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማዕከላ...
25/07/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የዲቦራ ፋውንዴሽን ቡታጅራ ቅርንጫፍን ጎበኙ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፣ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ፣ የቢሮው የመናጅመንት አባላት፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞንና የቡታጅራ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ አቶ ቶፊቅ ሞሳ የቡታጅራ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ፣ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች፣ ከዳውን ሲንድሮም ጋር የሚኖሩ ህፃናት ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የዲቦራ ፋውንዴሽን ቡታጅራ ቅርንጫፍን ጎብኝተዋል።

ይህ ጉብኝት ለቡታጅራ ቅርንጫፋችን ትልቅ ማበረታቻ ነው። የክቡራን እንግዶቻችን መገኘትና ድጋፍ በይበልጥ ተግተን እንድንሰራ፣ አገልግሎቶቻችንን እንድናጠናክር እና ከዳውን ሲንድሮምና ከሌሎች የአእምሮ እድገት ውስንነቶች ጋር ለተወለዱ ህፃናት የተሻሉ እድሎችን ለመፍጠር የበለጠ ተነሳሽነት ሰጥቶናል። ለሰጡን አበረታች ድጋፍ፣ ላሳዩን እምነት እና ከፋውንዴሽናችን ጋር ለሚያደርጉት ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።

President of the Central Ethiopia Region Visits Deborah Foundation Butajira Branch

H.E Dr. Endashaw Tassew, President of the Central Ethiopia Region, together with Mr. Samuel Darge, Head of the Central Ethiopia Regional Health Bureau, members of the Bureau's management team, senior leaders from the East Gurage Zone and Butajira Town, Mr. Tofik Mosa, Manager of Butajira General Hospital, hospital professionals, parents of children living with Down syndrome, and invited guests visited Deborah Foundation Butajira Branch.

This visit is a great source of encouragement for our Butajira Branch. The presence and support of our distinguished guests inspire us to work even harder, strengthen our services, and create greater opportunities for children born with Down syndrome and other intellectual disabilities. We sincerely thank our distinguished guests for their encouragement, the confidence they have shown in our mission, and their continued collaboration in building a more inclusive community.

ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የስደተኞች እና ተመለሾች አገልግሎት (RRS) ጋር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመናል።ይህ የሁለትዮሽ ትብብር በኢትዮጵያ በሚገኙ ስደተኞች፣ ተመለሾች እና ተቀባይ ማህበረሰቦ...
24/07/2026

ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የስደተኞች እና ተመለሾች አገልግሎት (RRS) ጋር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመናል።

ይህ የሁለትዮሽ ትብብር በኢትዮጵያ በሚገኙ ስደተኞች፣ ተመለሾች እና ተቀባይ ማህበረሰቦች ውስጥ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያላቸውን ሰዎች ተቀባይነት ለማጠናከር ያለመ ነው። በጋራ በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የአቅም ግንባታ፣ ስልታዊ የሆኑ የፍላጎት ልየታዎች እና የተሳለጡ የሪፈራል ድጋፍ ስርዓቶችን በመዘርጋት ማንም ወደኋላ እንዳይቀር እንሰራለን!

We signed a Memorandum of Understanding (MoU) with the FDRE Refugee and Returnees Service (RRS).

This bilateral collaboration is a major step toward strengthening intellectual disability inclusion for refugees, returnees, and host communities in Ethiopia. Together, we are committed to driving change through proactive awareness, capacity building, systematic identification, and establishing strong referral support structures to ensure no one is left behind.

አረንጓዴ አሻራ በዲቦራ ፋውንዴሽን ​ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዲቦራ መንደር የተካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በታላቅ ደስታ አከናውነናል! ይህ መርሃ ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ለጀመ...
23/07/2026

አረንጓዴ አሻራ በዲቦራ ፋውንዴሽን

​ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዲቦራ መንደር የተካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በታላቅ ደስታ አከናውነናል! ይህ መርሃ ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ለጀመረችው ታላቅ የሁለንተናዊ አረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የበኩላችንን አወንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከትና ለልጆቻችን ብሩህ ነገን ለመገንባት ያለመ ነው።

​በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት ውድ አጋሮቻችንን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን!

​Growing a Greener Future Together!

July 11, 2026​, we proudly joined hands at Deborah Village for a meaningful tree-planting event as part of Ethiopia’s national Green Legacy initiative! By planting these trees, we are doing our part to nurture our environment, support sustainability, and build a brighter, greener tomorrow for our children.

​Thank you to everyone who stepped up and contributed!

ዛሬ እሁድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ፔዲያትሪክ ኦፕታልሞሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሳዲቅ ታጁ፣ ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓ...
19/07/2026

ዛሬ እሁድ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ፔዲያትሪክ ኦፕታልሞሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሳዲቅ ታጁ፣ ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ከመጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር 100 ለሚሆኑ ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር ለሚኖሩ ሕፃናትና ወጣቶች የዓይን ሕክምና ምርመራ አድርገናል። የዛሬው መርሃ-ግብር ተከታታይ ክትትል እና የቀዶ ጥገና ሕክምናን የሚያካትት የረጅም ጊዜ ሥራችን አካል ነው።

​ዶክተር ሳዲቅ ታጁ እና መላው የሕክምና ቡድኑ ዓላማችን ከስኬት እንዲደርስ እያደረጉት ላለው ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም እያሳዩት ላለው ቁርጠኝነት ያለንን ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን!

Today, Sunday, July 19, 2026, we successfully conducted the 13th round of our Envision Program, providing comprehensive ophthalmology check-ups for over 100 children and youth with intellectual disabilities. This initiative was made possible through a vital collaboration with Dr. Sadik Taju (Pediatric Ophthalmologist), Menelik Referral Hospital, and medical professionals from the Department of Ophthalmology at Addis Ababa University’s College of Health Sciences.

We extend our heartfelt gratitude to Dr. Sadik Taju and the entire medical team for their unwavering dedication and professional support!

Address

Bole Sub-city
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deborah Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Deborah Foundation:

Shortcuts

Share