16/08/2026
የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት (ICS) አመራርና ሠራተኞች ከኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማሕበር ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ የሐገር በቀል ችግኝ ተከሉ።
በመርሃ ግብሩ አመራርና ሠራተኞች 3,000 ችግኞችን በመትከል የአገር በቀል የደን ሀብትን ለማስፋፋትና የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደገለጹት፣ ተቋሙ ይህንን የአረንጓዴ ልማት ተግባር የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት በመደገፍ ከጀመረበት ከስምንት ዓመታት በፊት ጀምሮ በቀጣይነት ሲያከናውን ቆይቷል።
ተቋሙ በቀጣይም የሐገር በቀል ችግኝ ተከላውን በማጠናከር ለሐገሪቱ አረንጓዴ ልማትና ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የችግኝ ተከላውና የተማሪዎች ድጋፍ መርሃ ግብሩ የአካባቢ ጥበቃንና የትውልድ ቀጣይነትን በአንድ ላይ የሚያጎለብት ተግባር ሆኖ ተካሂዷል።