Public Information Noble PIN

Public Information Noble PIN ''Building a better Ethiopia through access to information" "Unlocking the PIN to information access

19/07/2026
19/07/2026

አዲሱ የመረጃ ነጻነት አዋጅ፡ ጋዜጠኞች በፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይሰጥ እንደማይታሰሩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. – በኢትዮጵያ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 1427/2018፣ ለጋዜጠኞችና ለሐሳብ ነጻነት ወሳኝ ጥበቃዎችን ማካተቱ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደገለጹት፣ አዲሱ አዋጅ ማንኛውም ጋዜጠኛ ወይም ዋና አዘጋጅ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሳይሰጥበት፣ በምርመራ ወይም በሌላ ሰበብ ለእስራት መዳረግ እንደማይችል በግልጽ ይደነግጋል።
በቅን ልቦና የሚሰራ ጋዜጠኛ ከሕግ ጥበቃ አለው
ዋና ዕንባ ጠባቂዋ አክለውም፣ ጋዜጠኞች በሕጋዊ መንገድ ያገኙትን መረጃ በቅን ልቦና ለሕዝብ ማሰራጨታቸው በሕግ የሚያስጠይቅ እንደማይሆን አስረድተዋል። "አንድ ጋዜጠኛ ከመንግሥትም ሆነ ከግል ድርጅት በሕጋዊ መንገድ ባገኘው ሰነድ ላይ የተዛባ ወይም የተሳሳተ መረጃ ቢኖር እንኳ፣ ያንን መረጃ ለሕዝብ ያጋራው በቅን ልቦና መሆኑ ከተረጋገጠ፣ በሕግ ተጠያቂ አይሆንም" ሲሉ አብራርተዋል።
በተጨማሪም፣ የተላለፈባቸውን አስተዳደራዊ ወይም ሕጋዊ ውሳኔዎች ጋዜጠኞች ለፍርድ ቤት ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ተመልክቷል።
ሕገ-ወጥ አሠራሮች እና ቅጣቶች
አዲሱ አዋጅ መረጃን በማዛባት፣ በመደበቅ ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ በመጠቀም ሙስናንና ቅሌትን ለመሸፈን የሚሞክሩ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል።
ለከባድ ጥፋቶች፡ መረጃን ሆን ብሎ ማጥፋት፣ መደበቅ፣ ማዛባት ወይም የሐሰት ሰነድ ማዘጋጀት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም እስከ 100 ሺህ ብር፣ ወይም በሁለቱም ሊያስቀጣ ይችላል።
ለመረጃ አቅርቦት መጓተት፡ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ወይም የተሳሳተ መረጃ መስጠት እስከ 1 ዓመት እስራት ወይም ከ 25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ቅጣት ያስቀጣል።

የግል ተቋማትም መረጃ የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል
የቀድሞው አዋጅ በመንግሥት ተቋማት ላይ ብቻ የነበረው የመረጃ አቅርቦት ግዴታ፣ በአዲሱ አዋጅ ወደ ትላልቅ የግል ድርጅቶችና ከመንግሥት ጋር ተያይዞ የሚሰሩ አካላትንም ማካተቱ ተገልጿል።
እያንዳንዱ ተቋም፡
1. መረጃን በኃላፊነት የሚከታተል የመረጃ ኃላፊ መመደብ፣
2. የመረጃ ጥያቄዎችንና ምላሾችን የያዘ ዓመታዊ ሪፖርት ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማቅረብ፣
3. ተቋሙም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያቀርብ የሚገደድ ይሆናል።
ወ/ሮ ስመኝ አዋጁን ሙሉ ለሙሉ ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ መመሪያዎቹ እስኪጸድቁ ድረስ አዋጁን መሠረት በማድረግ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
Public Information Noble(PIN)
ፐብሊክ ኢንፎርሜሽን ኖብል (ፒን) NGO/CSO, Promote the right to access information.
"Information is a key! Information Matters!

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት የሙስና ወንጀል የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት፣ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት በተገልጋዩ ህብረተሰብ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ባለ ግንኙነት የሚፈጸም ተገቢነ...
03/06/2026

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት የሙስና ወንጀል የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት፣

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት በተገልጋዩ ህብረተሰብ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ባለ ግንኙነት የሚፈጸም ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ተገልጋዩ የህብረተሰብ ክፍል በህግ ክርክሮች እና በአስተዳደር አካላት የሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ለማግኘት ወደ ተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፊት ይቀርባሉ፡፡

በዚሁ ሁኔታ አገልግሎት ፈልጎ የቀረበው ተገልጋይ እንደ ጉዳዩ ባህሪ በህግ እና አሰራር በተቀመጠ ምክንያታዊ ጊዜ ውስጥ ለጉዳዩ እልባት አግኝቶ መሸኘት አለበት፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ተገልጋዮችን ተገቢ ላልሆነ እንግልት በመዳረግ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ጉልበታቸውን እንዲያባክኑ በማድረግ፣ ለከፋ ምሬት እና ተስፋ በመቁረጥ በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሻክር ይሆናል፡፡

ያለአግባብ ጉዳይ ማጓተት በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ኃላፊ ወይም ሠራተኛ በኃላፊነቱ በሥራው ምክንያት በቀረበለት ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቅም ለማግኘት ሲል በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለውን ማንኛውንም ሰው ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት በማሰብ ከህግ፣ ከመመሪያ ወይም ከተለመደው አሰራር ውጪ ያለበቂ ምክንያት ጉዳዩን ያልወሰነ፣ ያዘገየ ወይም ባለጉዳይን ያጉላላ እንደሆነ እንደ ጉዳዩ ታይቶ በገንዘብ ወይም በእስራት ይቀጣል፡፡

በአዋጁ እንደተደነገገው ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት የሙስና ወንጀል የሆነበትን መሠረታዊ ምክንያት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የሙስና ወንጀሎች በመሰረታዊነት የሚፈጸሙት የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለአንዱ ወገን በተለያዩ ምክንያቶች በማዳላት ሌላውን ወገን ለመጥቀም በማሰብ ነው።

የዚህ ወንጀል ፈጻሚዎች ጉዳይን አለአግባብ የማጓተት ተግባር የሚፈጽሙት ባለጉዳዩ በመመላለስ ምክንያት ከሚደርስበት እንግልት ለማምለጥ ሲል ገንዘብ እንዲከፍላቸው ተጽእኖ ለማሳደር አልያም ባለጉዳዩ ተማሮ ጉዳዩን መከታተሉን እንዲተወው በማድረግ የባለጉዳዩን መብት ለመረጡት ሌላኛው ሰው በማስተላለፍ በዚህም የሚከፈላቸውን ተገቢ ያልሆነ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ነው ማለት ይቻላል፡፡

የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ የልማት ድርጅቶች እንዲሁም የህዝባዊ ድርጅቶች ተገልጋዮቻቸውን ሲያስተናግዱ አገልግሎት ወይም ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዳይ ያለውን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት በህግ እና በአሠራር ሥርዓት እንዲሁም የተለመዱ አካባቢያዊ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ለተገልጋዮቻቸው በተገቢው ጊዜ ውሳኔ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ያለ በቂ ምክንያት ህግ እና አሰራርን በመጣስ ተገልጋዮችን ለማንገላታት እና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት እንዲሁም አገልግሎት ጠያቂው ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ጉዳይን ያለበቂ ምክንያት ማጓተት በህግ የሚያስጠይቅ እና የሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡

ተገልጋዩ ማህበሰረብ በመንግስትም ይሁን ህዝባዊ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲሄድ በህግ እና አሠራር ስርዓት የተቀመጡ የአሰራር ደረጃዎችን ተረድቶ በዛ ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኝ መጠየቅ እና ይህ በማይሆንበት ጊዜ ጉዳዩን ያለ በቂ ምክንያት የሚያጓትቱ የመንግስት እና ህዝባዊ ድርጅት ሠራተኞች እና ኃላፊዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በመጠቆም ተባባሪ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

05/03/2026

እወቅ
Be informed...✍️

30/12/2025

መረጃ በሚከለክሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ የተቀመጠው
ቅጣት ወደ 150 ሺ ብር ከፍ እንዲል ተጠየቀ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት፣ የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ መረጃ በሚከለክሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያስቀመጠው የቅጣት መጠን ከ20 ሺሕ ወደ 150 ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ትናንት በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄደው ውይይት ላይ ጠየቀ።

ምክር ቤቱ፣ የመንግሥት ሃላፊዎች የሰነድ መረጃ መስጠት ባልቻሉ ጊዜ በቃለ መጠይቅ ተጨማሪ መረጃ እንዲሠጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጁ ውስጥ እንዲካተት ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

ረቂቅ አዋጁ የመንግሥት ሃላፊዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ለመረጃ ጥያቄ ምላሽ እንዲሠጡ ያስገድዳል።

ምክር ቤቱ በበኩሉ፤ ለአስቸኳይ ኹኔታዎች ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተቋማት ሃላፊዎች ለመረጃ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት አለባቸው የሚል አንቀጽ ጭምር ይካተት በማለት አሳስቧል ስትል ዋዜማ ዘግባለች፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
AdissAdmas
Public Information Noble PIN

Access to information
30/12/2025

Access to information

30/12/2025

Tomorrow on Youth Network Ethiopia – Join Us!

መረጃ የማግኘት መብት እና የሕግ ግንዛቤ ‼️
Access to Information & Legal Awareness ‼️

🗓 Date: December 31, 2025

This session will empower young people to understand their right to access information, strengthen legal awareness, and become informed, responsible citizens.

🔗 Join us on Telegram:
https://t.me/YNE123

👥 Invite your friends and networks
📲 Be part of the conversation!





Address

Dropped Pinhttps://maps. App. Goo. Gl/hDT7pUHMWMUkHgFB 7
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Public Information Noble PIN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share