Jemal jemal

Jemal jemal General

ሰላም ወገኖቼ ይህን ጉድ ተመልከቱ ፡፡ከላይ የምታዩትን ፎቶ የወሰድኩት ከኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል የስነ ጥበብ መፅሀፍ ነዉ ፡፡እነዚህ ሰዎች ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም የምላችሁ በምክንያት ነዉ፡፡...
05/04/2026

ሰላም ወገኖቼ ይህን ጉድ ተመልከቱ ፡፡ከላይ የምታዩትን ፎቶ የወሰድኩት ከኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል የስነ ጥበብ መፅሀፍ ነዉ ፡፡እነዚህ ሰዎች ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም የምላችሁ በምክንያት ነዉ፡፡ህፃን ልጅና ወረቀት የያዘዉን አይለቅም ይባላል፡፡ወያኔና ኦ.ህ.ደ.ድ የአማራን ህዝብ እና የኦሮሚያን ህዝብ ለማፋጀት በመለስ ዜናዊ ሀሳብ አመንጭነት የተሰራ የበቀል እና ህዝብን የማጫረስ ፕሮጀከት አካል ነዉ፡፡ይህ ሀዉልት ሲሰራ የኦሮሚያ ክልል የትምህርት እና የጤና ሽፋን የዛሬን አያድርገዉና እጅግ አነስተኛ ነበር ፡፡አስታዉሳለሁ ፡፡ሚኒሊክ አርሲ ላይ ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈፀመበት ጦርነት ስለማካሄዱ ከተስፋየ ገብረአብ በስተቀር በማንኛዉም መፅሀፍ ላይ ተፅፎ አይገኝም፡፡ተስፋዬ ገብረአብም በአማራ ጠልነቱ የሚታወቅ የህወሃት ተከፋይ መሰሪ ነበር ፡፡ከላይ እንደምታዩት ምንጭ ብለዉ ያቀረቡት የራሳቸዉን ሚድያ ነዉ፡፡ሌላ ምንጭ የላቸዉም፡፡ሚኒሊክ ፤የአማራ ህዝብም ይሁን የሚኒሊክ ሰራዊት በዚህ መልኩ ወንጅል ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ሰነድ የለም፡፡ይህ ሀሰተኛ ትርክት ምን ዳፋ እንዳመጣ ከ2010 እስከ አሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፈዉንና አሁንም በወለጋ ዕየተጨፈጨፈ ያለዉን የአማራ ተወላጅ ማየት ይቻላል ፡፡
ለመሆኑ የሚኒሊክን አርሲ መሄድ ወረራ ካላችሁት ፤አሁን ከኦሮሞ የተዉጣጣ ጦር (መከላከያ) አማራ ክልል መገኘትና ጦርነት መክፈቱ ለምን ወረራ አትሉትም፡፡የሚሽኑ ስያሜስ ምን ሊባል ነዉ ? ምንስ ሊያደርግ ነዉ አማራ ክልል የሚዋጋዉ ? በነገራችን ላይ አሁን መከላከያ በሚባለዉ ጦር አማራ ክልል የሚገደለዉ ወጣትና ህፃናት ፤በድሮን የሚጨፈጨፉት ህፃናት እና ቁሳዊ ንብረቶችን አስባችሁት ታዉቃለችሁ ? እኛም ሀዉልት ይሰራልን የሚል የአማራ ትዉልድ እንደሚመጣ አትጠራጠሩ ፤የዚህ ደግሞ እልፈ አእላፍ ማስረጃዎች ያሉት መሆኑን አትዘንጉት፡፡በእርግጥ አማራን መተንኮስ ምን ሊያመጣ እንደሚችል አሁንም ዕያያችሁት ይመስለኛል ፡፡በተጨማሪም ወለጋ ላይ አጣዬ ላይ ወዘተ ያለቀዉን ህዝብም እንዳትረሱት ሙሉ ማስረጃ አለን ፡፡ሁል ጊዜም ዘረኛ አገዛዞች የሚፈፅሙት ግፍ እዳ ከፋይ ህዝቡና ትዉልዱ ነዉ ፡፡ እናዉቃለን ፡፡ወያኔ ፤ብአደንና ኦህደድ በሰሩት ሴራ የተገደለዉ ሚስኪኑ ህዝብ ነዉ ፡፡ በአጠቃላይ የአኖሎ ሀዉልት የምትሉት ነገር የኢትዮጵያን የባለፈዉን ዘመን ታሪክ አይወክልም ፡፡ ለትዉልዱም ከዚህ የሚማረዉ ነገር የለም ፡፡ ቻዉ ፤ቻዉ ፡፡

ሰላም ወገኖቼ ይህን ጉድ ተመልከቱ ፡፡ የምታዩትን ፎቶ የወሰድኩት ከኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል የስነ ጥበብ መፅሀፍ ነዉ ፡፡እነዚህ ሰዎች ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም የምላችሁ በምክንያት ነዉ፡፡ህፃን...
05/04/2026

ሰላም ወገኖቼ ይህን ጉድ ተመልከቱ ፡፡ የምታዩትን ፎቶ የወሰድኩት ከኦሮሚያ ክልል 8ኛ ክፍል የስነ ጥበብ መፅሀፍ ነዉ ፡፡እነዚህ ሰዎች ለኢትዮጵያ አይጠቅሙም የምላችሁ በምክንያት ነዉ፡፡ህፃን ልጅና ወረቀት የያዘዉን አይለቅም ይባላል፡፡ወያኔና ኦ.ህ.ደ.ድ የአማራን ህዝብ እና የኦሮሚያን ህዝብ ለማፋጀት በመለስ ዜናዊ ሀሳብ አመንጭነት የተሰራ የበቀል እና ህዝብን የማጫረስ ፕሮጀከት አካል ነዉ፡፡ይህ ሀዉልት ሲሰራ የኦሮሚያ ክልል የትምህርት እና የጤና ሽፋን የዛሬን አያድርገዉና እጅግ አነስተኛ ነበር ፡፡አስታዉሳለሁ ፡፡ሚኒሊክ አርሲ ላይ ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈፀመበት ጦርነት ስለማካሄዱ ከተስፋየ ገብረአብ በስተቀር በማንኛዉም መፅሀፍ ላይ ተፅፎ አይገኝም፡፡ተስፋዬ ገብረአብም በአማራ ጠልነቱ የሚታወቅ የህወሃት ተከፋይ መሰሪ ነበር ፡፡ከላይ እንደምታዩት ምንጭ ብለዉ ያቀረቡት የራሳቸዉን ሚድያ ነዉ፡፡ሌላ ምንጭ የላቸዉም፡፡ሚኒሊክ ፤የአማራ ህዝብም ይሁን የሚኒሊክ ሰራዊት በዚህ መልኩ ወንጅል ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ሰነድ የለም፡፡ይህ ሀሰተኛ ትርክት ምን ዳፋ እንዳመጣ ከ2010 እስከ አሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፈዉንና አሁንም በወለጋ ዕየተጨፈጨፈ ያለዉን የአማራ ተወላጅ ማየት ይቻላል ፡፡
ለመሆኑ የሚኒሊክን አርሲ መሄድ ወረራ ካላችሁት ፤አሁን ከኦሮሞ የተዉጣጣ ጦር (መከላከያ) አማራ ክልል መገኘትና ጦርነት መክፈቱ ለምን ወረራ አትሉትም፡፡የሚሽኑ ስያሜስ ምን ሊባል ነዉ ? ምንስ ሊያደርግ ነዉ አማራ ክልል የሚዋጋዉ ? በነገራችን ላይ አሁን መከላከያ በሚባለዉ ጦር አማራ ክልል የሚገደለዉ ወጣትና ህፃናት ፤በድሮን የሚጨፈጨፉት ህፃናት እና ቁሳዊ ንብረቶችን አስባችሁት ታዉቃለችሁ ? እኛም ሀዉልት ይሰራልን የሚል የአማራ ትዉልድ እንደሚመጣ አትጠራጠሩ ፤የዚህ ደግሞ እልፈ አእላፍ ማስረጃዎች ያሉት መሆኑን አትዘንጉት፡፡በእርግጥ አማራን መተንኮስ ምን ሊያመጣ እንደሚችል አሁንም ዕያያችሁት ይመስለኛል ፡፡በተጨማሪም ወለጋ ላይ አጣዬ ላይ ወዘተ ያለቀዉን ህዝብም እንዳትረሱት ሙሉ ማስረጃ አለን ፡፡ሁል ጊዜም ዘረኛ አገዛዞች የሚፈፅሙት ግፍ እዳ ከፋይ ህዝቡና ትዉልዱ ነዉ ፡፡ እናዉቃለን ፡፡ወያኔ ፤ብአደንና ኦህደድ በሰሩት ሴራ የተገደለዉ ሚስኪኑ ህዝብ ነዉ ፡፡ በአጠቃላይ የአኖሎ ሀዉልት የምትሉት ነገር የኢትዮጵያን የባለፈዉን ዘመን ታሪክ አይወክልም ፡፡ ለትዉልዱም ከዚህ የሚማረዉ ነገር የለም ፡፡ ቻዉ ፤ቻዉ ፡፡

05/04/2026

የዘዉዱ ሰጥአርጌ ዉሸትና ክሽፈት !የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም !
የአማራ ህዝብ ፈተናዎችና የመዉጫ ብልሀቶች በተሰኘዉ የብርጋዴር ጄኔራል ዘዉዱ ሰጥአርጌ “መፅሀፍ”ላይ የተሰጠ አጭር ሀሳብ ፡
ዘዉዱ ሰጥአርጌ አሁን ያለበት ሁኔታ በተመለከተ በመከላከያ ሰራዊት ዉስጥ የ11ኛ እዝ አዛዥ ነዉ፡፡በሌላ አነጋር በወሎ በተለይ ደግሞ በደቡብ ወሎ አካባቢ ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ(አፋብን)ጋር የሚደረገዉን ጦርነት የሚመራዉ ብልፅግና አፈራሽ ጄኔራል ነዉ፡፡ከዚህ በፊት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ እዝ የ801ኛ ኮር ዋና አዛዥ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡የዚህ ሰዉ የትዉልድ ቦታ በወሎ ክፍለ ሀገር በአማራ ሳይንት ምድር ልዩ ቦታዉ ቤጃ በተሰኘ አካባቢ ነዉ፡፡ከላይ የተጠቀሰዉና በዚህ ሰዉ ተፃፈ ተብሎ በ500 ብር ለገበያ የቀረበዉ መፅኃፍ የህትመት ጥራቱና እርእሱ የሚያማልል ነዉ፡፡ምክንያቱም እዉነትም ለአማራ ህዝብ ፈተናዎችና ስጋቶች መፍትሄ ተገኘ እንደ በሚል ጉጉት ለንባብ የሚያጓጓ ነዉ፡፡ዉስጡን ስናየዉ ግን ከይልቃል ከፋለ ሀሳቦች የማይሻልና እዚህ ግባ የሚባል ቁም ነገር ያልያዘ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡መፅኃፉ አድርባይነት የተንፀባረቀበት ፤የአማራን ህዝብ ፈተናዎችና ስጋቶች የካደ ፤የዉሸታም ካድሬ የደመነፍስ ንግግሮች ናቸዉ፡፡የመፅኀፉ ሀሳቦች ድግግሞሽ የበዛበት እና የተደበላለቀ ከመሆኑም አልፎ ዉሸት የበዛበት እንድሁም በፍርደ ገምድልነት እና በእወደድ ባይነት መንፈስ የተፃፈ መፅሃፍ ነዉ፡፡አድርባይነትና በኦሮሞ አለቆቹ ጋር ለመሞገስ ታማኝነትን ለማሳየት ተብሎ የተፃፈ ነዉ፡፡ደመነፍሳዊነትም የተነፅባረቀበት ነዉ፡፡መፅሃፉ ላይ የታዩ ሃሰቦች በሙሉ ማለት ይቻላል የአማራ ጠላቶች በተለያዩ አጋጣዎች በእቅድ ይሁን ያለእቅድ ፤ያንፀባርቋቸዉ የነበሩ ፀረአማራ ትርክቶች ናቸዉ፡፡እነዚህ ፀረ አማራ ሃሳቦች አማራን አንገት ለማስደፋት የተነደፉ ስልቶች አካል ናቸዉ፡፡በመፅሀፉ የአማራን ህዝብ ከፈተና የሚያዎጣ አንድም ሀሳብና ብልሀት አልታየበትም፡፡ዉል አልቦ ነዉ ፡፡መፅሃፉ በክፉም በደግም ሊነሱ የማይችሉ ብዙ የተዘበራረቁ ሃሳቦችንና የማይጠቅሙ ሃሳቦችን የያዘ ቢሆንም ለአብነት ያህል ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ለማንሳት እወዳለሁ
1. የአማራ ህዝብ ችግሮች ከአማራ ህዝብ እና ከክልሉ ዉስጥ የመነጩ ናቸዉ፤ የሚል ዉሽክትና ዉሸት ሃሳብ በመያዙ
2. ወልቃይትና ራያን ግዛቶች በተመለከተ የአማራ ጥያቄ ህዝቡ አማራ ነዉ ፤የትግራይ ፖለቲከኞች ጥያቄ ደግሞ መሬቱ የአማራ ነዉ ብለዉ ነዉ የሚከራከሩት ብሎ ማቅረቡ ፡፡ ሀሳብም የአማራን ህዝብ የማንትና የግዛት አንድነት ጥያቄዎች በእጅጉ የሚያኮስስና የሚያዋርድ ነዉ ፡፡
3. ኦነጋዉያን የሚለዉንና የኦነጋዊያን አስተሳሰብን ማን እንደሚያራምደዉና በማን እንደሚመራ ሳታዉቅ፤ ሳይገባህ ወይንም ሆነ ብሎ በመካድ መሞከር እና በዚህ ዙሪያ ሃሳብ ለመስጠት መሞከርህ መሰረታዊ ስህተትህ ነዉ፡፡ኦነጋዊያንና የኦሮሞ ፅንፈኝነትን አሁን ቤተ መንግስት ካለዉ ቡድን ለይተህ ለሌላ አካል ለመስጠት መሞከርህ ፤የዚህን ገዥ ቡድን ሀጠያትና ወንጀል ለማቅለል ብሎም ለመካድ የሄድክበትን እርቀት ያሳያል፡፡እንቅጩን ልንገርህ ቤተ መንግስት ካለዉ ኦ.ነ.ግ ሌላ አ.ነ.ግ የለም፡፡የኦነጋዊያን ራእይ የሚያስቀጥሉትም ፤የሚስፈፅሙትም ሚኒሊክ ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት ኦሮሞ አለቆችህ ናቸዉ፡፡ኦነግን ከዚህ ዉጭ ማሰብ ስህተት ነዉ ዘዉድሻ፡፡
ዘዉዱ ሆይ! ጦር እየመራህ የአማራን ገበሬ ከመግደል በተጨማሪ ሌላ ወንጀል ነዉ የሰራሀዉ ፡፡ አማራ ሳይንት ተወልደህ የጠላት መጠቀሚያ በመሆንህ በጣም ያሳዝናል፡፡ለወደፊቱም ሂሳብህንና እዳህን እያባዛህ ነዉ፡፡የአማራ ህዝብ ችግሮች ከአማራ ህዝብ አልመነጩም፡፡የአማራ ህዝብ ችግሮች ከጥንት ጀምሮ የነበረዉና አሁንም ያለዉ የኦሮሞ ኢሊቶች አማራ ጠልና ኢትዮጵያ ጠል ትርክት ነዉ፡፡የኦሮሞ ኢሊቶች(ፖለቲከኞች) ሁሉ አማራ ጠል ናቸዉ የሚል እሳቤ ግን የለኝም፡፡አሁን የአማራ ህዝብ ዉድ ዋጋ እየከፈለ ያለዉ እነዚህ ወገኖች በተለይ የአንተ አለቆች ለአማራ ህዝብ ያላቸዉ ጥላቻና የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ ሀገር ለመጠቅለልና ኦሮሞኛ ተናጋሪ ሀገር ለመመስረት ባላቸዉና ባቀዱት እብሪተኛ እቅዳቸዉ ምክንያት ነዉ፡፡ይህ ደግሞ ሊሳካ አይችልም፡፡አሁን አማራ ክልል ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉ ጦርነትና የትጥቅ ትግል የአንተ አለቆች አማራ ጠል በመሆናቸዉና የአማራን ህፃናት በጅምላ ገድለዉ ፤በጅምላ በመቅበር በአማራ ህዝብ ላይ መዋቅራዊ ዘር ማጥፋ በመፈፀማቸዉ ምክንያት የመጣ ነዉ፡፡ክልሉ ዉስጥ ያለዉ ጦርነትም መነሻዉና ምክንያቱ ይህ ነዉ፡፡መድረሻዉ ግን ሌላ ነዉ፡፡ወታደር ማለት የአንድ ዘረኛ ቡድን ታማኝ አገልጋይና ዘበኛ መሆን ሳይሆን ሀገሩን በችግር ጊዜ ከጭንቅ የሚያወጣ እና ከህዝብ ጎን የሚሰለፍ ማለት እንጅ ለአንድ ዘረኛ ቡድን ወንበር ጠባቂ መሆን ማለት አይመስለኝም፡፡ኦነግ የአማራ ህዝብም የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት ነዉ፡፡ተገንጣይም ነዉ፡፡የኢትዮጵያን ታሪክና ማንነት አይቀበልም፡፡ኢትዮጵያ የአማራ ስሪት ናት ብሎ ያምናል ፡፡አማራ በፈጠራት ሀገር አንኖርም ፤በኦሮሞ ማንነት የተቃኘች ሀገር መመስረት አለብን ብለዉ ነዉ አለቆችህ ያለ እረፍት የሚሰሩት፡፡ይህን አጀንዳ በበላይነት የሚመሩትና የሚያስተባብሩት ብሎም የበላይ ጠባቂዎች እኮ የአንተ አለቆች ናቸዉ፡፡አንተ መንግስት የምትለዉ ቡድን ማለቴ ነዉ፡፡በብልፅግና እና በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ ኦነጋዊነትን አሁን ስልጣን ላይ ካሉት አለቆችህ ለይተህ ለማቅረብ የሞከርከዉ ስሁት ትንታኔ ከንቱ ነዉ፡፡ዉሸትም ነዉ፡፡አሁን ብልፅግና የሚባለዉ ስብስብ እኮ ነባር ማንቶችን የሚያጠፋዉ ፤አማራ ላይ ዘመቻ የከፈተዉ፤ አማራነትንና ኢትዮጵያዊነት ማንነትን የሚፀየፈዉ እኮ በኦሮሞ ባህልና ማንነት የተቃኜች ሌላ ሀገር ለመፍጠር ነዉ፡፡ተግባባን ?ኦቦ ዘዉዱ? ይህ አስተሳብ ነዉ የኦነጋዉያን እሳቤ ማለት፡፡ይህ ቡድን ከመገንጠል ወደ መጠቅለል እሳቤዉ መሰረት ነዉ ሀገር እየወረረ የሚገኘዉ፡፡በዚህ ሂደት አማራ እንቅፋትና ተገዳዳሪ ሀይል ሊሆንብኝ ይችላላ ብሎ እንደሚሰጋ አንተም ታዉቀዋለህ፡፡ወለጋ ያለዉን የኦነግ ታጣቂ አንጃ ኦነግ ከማለት ፈንታ ሸኔ ብሎ አብይ አህመድና ጓዶቹ ስም የሰጡት እኮ የኦነግን ክብር ላለመንካት ነዉ፡፡ኦነጋዊነት ከዚህ በላይ እንድት እና ማን ሊሆን ይችላል፡፡ኦነግ ማነዉ?ኦነግ የት ነዉ ያለዉ ?ስለዚህ ዘዉዳችን የኦነግ ጉዳይ አስፈፃሚ ነህ ፡ ለማለት ያህል ነዉ ፡፡የበለጠ ግልፅ ለማድረግ እናንተ የምትመሩት የሀገር መከላከያ እየተባለ የሚጠራዉ ጦር በመኪና ተጭኖ ወደ ተለያዩ የአማራ ክልል ወረዳዎችና ከተሞች ሲመጣና ሲገባ ኦነግ መጣ፤ የኦሮሞ ጦር መጣ ፤የኦነግ ጦር ገባ ወዘተ የሚባለዉ ለምንድን ይመስልሃል፡፡ ህፃናትና እናቶች ሳይቀሩ ኦነጎቹ መጡ ማለት የተለመደ ነዉ፡፡ቄሮ መጣ ወዘተ ፡፡በተቃራኒዉ ደግሞ የፋኖ ሀይሎች ከተሞችን ሲቆጣጠሩ የዕኛ ልጆች ዛሬ ከተሞችን ተቆጣጠሩ ፤ልጆቻችን መጡ ፤ጀግኖቹ መጡ ወዘተ የሚሉት ንግግሮች በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመዱ አገላለፆች ናቸዉ ፡፡ከዚህ ሁኔታ እኮ አንተ የምትመራዉ ጦር የኦነግን ጦር ነዉ ፡፡ ባንዳዎች የምንላችሁ እኮ ያለ ምክንያት አይደለም ከዚህ ወራሪና ተስፋፊዉ የኦሮሙማ ጦር ተባባሪና ታዛዥ በመሆናችሁ ነዉ ፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሰዉ መፅሃፍ ላይ የተጠቀሱት ሃሳቦች ከአንድ አድር ባይ የብልፅግና ካድሬ ደመነፍሳዊ ንግግሮች የሚሻል መፅሃፍ አይደለም፡፡መፅሃፍም ሊባል አይችልም፡፡ወንድሜ የአማራን ህዝብ ለቅሶ በመቀማትና በደሉን በመሸፋፈን በጦርነት ከሰራሀዉ የጦር ወንጀል በተጨማሪ ሌላ ወንጀል ነዉ የሰራኸዉ፡፡በጣም ያስገረመኝ ደግሞ ወንጀለኛነትህን በመፅሀፍ ሰንደህ በራስህ ላይ ምስክር ለመሆን መዘጋጀትህ ነዉ፡፡የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ይሉሃል ይሄ ነዉ ፡፡ ፡፡ቻዉ፤

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jemal jemal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share