የሠሜን ዕዝ መታሰቢያ ገፅ Northern Command Memorial

የሠሜን ዕዝ መታሰቢያ ገፅ Northern Command Memorial ይህ ገፅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ አባላት የ?

07/06/2025

ዘመቻ አብቹ ምዕራፍ አንድ

እነሆ ከሰአታት በሁዋላ የአብይ አህመድን መንግስት ለመቃወም በኦንላይን ደግሰዋል።

አስገራሚው ነገር ሁሉም 100% አብይን ተቃዋሚ ናቸው 😀
ሁሉም አብይ የሰራውን ሙሉ በሙሉ ያጥላሉ ከመቶ 1% እንኳን ጥሩ የተሰራ ነገር የለም ብለው ነው የሚቃወሙት።

የህ ለዘመናት የቀጠለ የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ጊዜ ነው

ከጓድ ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግስቱ እስከ መለስ ዜናዊ
ከመለስ እስከ ሀይለሪያም
እስካሁን መንግስትን መቃወም በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጉዞ ማለት ምንም ጥሩ ነገርን አለመፈለህ መቶ ፐርሰንት ማጥላላት ነው።

ከምር ይዘገንነኛል ለምንድነው ልጅ አቤል የማትቀላቀለው ያሉኝ ሰወችን ሳስብ ይህ መንፈስ ስለ ተጋባባቸው ነው።

እሽ ይቃወሙ አብይን ያጥላሉ ግን ምንም አንድ እንኳን የተሰራ ጥሩ ነገር የለም ብለው የተለመደውን ይዘው ሲጓዙ እንዴትስ ልቀላቀል ?

በነገራችን ላይ ከተቃዋሚወቹ ውስጥ መለስ ዜናዊ የአብይ ግድብን ሲያስጀምር ለታይታ ነው አገራችን ወደ ጦርነት ሊከታት ነው ሲሉ የነበሩ መለስ ምንም አልሰራም ብለው መቶ ፐርሰንት ሲያጥላሉ የነበሩ ናቸው።

አስተዋይ ወጣት እንዳለም አትዘንጉ እንጅ በአገሪቱ ለተከሰቱ ችግሮች እናንተም ንግግራችሁ ጥላቻችሁ አስተዋፅኦ ነበረው።

ጃዋር እስር ቤትን መጠለያ አደረገ እንጅ ከመግባቱ በፊት የህወሀት ቲዲኤፍ በፌደራል መንግስቱ ቁጥጥር ስር ሊገባ ይገባል የአንድ ክልል ሪጂናልኦቶኖሚ በወታደራዊ ሀይል ሊገነባ አይገባም ሲል ነበር ዛሬ ምንም ጨዋ ሆኖ ቁጭ።

አገሪቱ ውስጥ ለተነሱ ችግሮች እናንተ እንዲያውም ዋና ነበራችሁ።

እኔ መቶ ፐርሰንት ጭፍን ደጋፊ ስህተት እያየም ማይናገር ፅንፈኛ አይመቸኝም

መቶ ፐርሰንት ጥሩ የተሰራን እያጥላላ የሚቃወምም አይመቸኝም።

ዘጠኛ ዘጠኝ ፐርሰንት አብይን አጥላልታችሁ አንድ ፐርሰንት ጥሩ ተሰራ ብትሉኝ አብሬ በቆምኩ

ሁሉንም ነገር ውሸት ስህተት ወዘተ ብላችሁ እንቃወም ያሳፍራል።

በነገራችን ላይ አንዳችሁ ስልጣን ብትይዙ በተመሳሳይ እርስ በርስ መልሳችሁ ታጠላላችሁ።

እንዴ ደጋፊም ተቃዋሚም ሰልጥኑ እንጅ እስከመቸ?

አብይ አህመድ ይሄ ይሄ ችግር ስህተት አለበት ብላችሁ የተቃውሞ አጀንዳችሁን እንስማው ከዛ እንደሰለጠነ ፖለቲከኛ

ቢያስን አንድ ነገር ከመቶ ተቃውሞ ለይታችሁ ይሄን ደግሞ ጥሩ ሰርቶዋል ብላችሁ አንድ ቀን ሳት ብሎዋችሁ ስትናገሩ እንስማ።

ልጅ አቤል መቶ ፐርሰንት ይደግፋል ወይም መቶ ፐርሰንት ይቃወማል ብሎ የሚያስብ ካለ ባናቱ መተከል ይችላል።
አብይ አህመድ ስህተት ስርቶዋል አሁንም ችግር አለ አወ ምን ጥርጥር አለ ብዙ ስህተት አለ ችግር አለ እንደዛውም የሰራቸው ትውልድ ተሻጋሪ ሊደገፉ የሚችሉ ነገሮች አሉ ምን ጥርጥር አለው በሚገባ።

ሚዛን ያለው ፖለቲካ ይዛችሁ ኑ ያኔ ውይይት ይኖረናል ከዛ ውጭ ምንም አታመጡም ምንም አትፈጥሩም የትም አትደርሱም።

@ልጅ አቤል

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሠሜን ዕዝ መታሰቢያ ገፅ Northern Command Memorial posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share