Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Election - CECOE

Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Election - CECOE CECOE is a network of civil society organizations established with the objectives of leading and coordinating all election related activities.

08/06/2026
የህብረት ለምርጫ የመረጃ መሰብሰቢያ ማዕከልን (Data Center) ከጎበኙ ተቋማት መካከል የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር  H.E. Sofie From-Emmesberger  ( European Uni...
04/06/2026

የህብረት ለምርጫ የመረጃ መሰብሰቢያ ማዕከልን (Data Center) ከጎበኙ ተቋማት መካከል የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር H.E. Sofie From-Emmesberger ( European Union in Ethiopia) ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፤ የአለም አቀፍ ተቋማት እና ኤጀንሲዎች ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ  የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ትዝብት ሪፖርቱን አስመልክቶ ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።የመጀ...
03/06/2026

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ትዝብት ሪፖርቱን አስመልክቶ ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ረፖርቱን በድረ ገፃችን ላይ ያገኙታል ። https://cecoe.org/downloads/publications/

የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የትዝብት ረፖርት መሰብሰቢያ ማዕ...
02/06/2026

የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የትዝብት ረፖርት መሰብሰቢያ ማዕከልን ዛሬ ግንቦት 25 2018 ዓ.ም ጎብኘተዋል።
Uhuru Kenyatta - 4th President

ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የተሰጠ አስቸኳይ የሚዲያ ማስተካከያ መግለጫየኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ 2,258 ተቀማጭ...
02/06/2026

ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የተሰጠ አስቸኳይ የሚዲያ ማስተካከያ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ 2,258 ተቀማጭ (Sitting Observers) እና 891 ተንቀሳቃሽ (Mobile Observers) ታዛቢዎችን፣ በአጠቃላይ 3,149 ታዛቢዎችን ማሰማራቱ ይታወቃል።

ህብረቱ በድምፅ መስጫ ቀን ታዛቢዎች ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያ በመግባት እንዲታዘቡ መፈቀድን፣ በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች መክፈቻ ሰዓት የምርጫ አስፈጻሚዎች ተሟልቶ መገኘትን፣ ድምጽ መስጠት በሚጀመርበት ሰዓት (ከጠዋቱ 12 ሰዓት) በጣቢያዎች የተገኙ አስፈጻሚዎች ቁጥርን ፤ የምርጫ አስፈፃሚዎች የፆታ እና የአካል ጉዳተኝነት ስብጥርን፣ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች የተቋቋሙበት ሥፍራን፣ በድምጽ መስጫ ጣቢያ ውስጥ ወይም በ200 ሜትር ርቀት ክልል ውስጥ የቅስቀሳ ምልክቶች እና ቅስቀሳዎች መኖራቸውን፣ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ተደራሽነት እና አመቺነትን፣ ሁሉም የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን ፣ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ከመታሸጋቸው በፊት ባዶ መሆናቸውን ማረጋገጥን በተመለከተ ብቻ እና እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ድረስ ተሰብስበው ማረጋገጥ በቻልናቸው ሪፖርቶችን መሰረት በማድረግ ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርቱን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ለሚዲያ አካላት በጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል።

ሆኖም ግን፣ ህብረቱ ባደረገው የሚዲያ ክትትል በአንዳንድ የሚዲያ ተቋማት ህብረቱ ከሰጠው መግለጫ ይዘትና አውድ ውጭ አዛብተው መዘገባቸውን አረጋግጠናል። ይሁን እንጂ ከህብረቱ ተግባርና ሃላፊነት ውጭ የሆነውን በአጠቃላይ የምርጫውን ውጤት ህብረቱ የገለጸ በማስመሰል መቅረቡ ስህተት መሆኑን እናሳውቃለን።

በተጨማሪም ህብረቱ በሪፖርቱ የቁሳቁስ አጥረት ከአሳሳቢ ሁነቶች ዝርዝር ስር ባልገለፀበት ሁኔታ የቁሳቁስ እጥረት ጉዳይ ‘አሳሳቢ ሁነት (Critical Incidents)’ በሚል በሚዲያ የቀረበው አገላለፅ “ህብረቱ አሳሳቢ ጉዳይ” በሚል መገለፁ ስህተት መሆኑን እንገልፃለን ።

በመጨረሻም እንዲህ አይነት ከአውድ እና ከይዘት ውጭ የትዝብት ረፖርቱን የዘገቡ ተቋማት አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ የሚሰራ መሆኑን ህብረቱ ያሳውቃል። ለበለጠ መረጃ ህብረቱ በዛሬው እለት የሰጠውን መግለጫ በህብረቱ ዌብ ሳይት ላይ ማግኘት ይቻላል። https://cecoe.org/downloads/publications/

ግንቦት 24 ፤ 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ኅብረት ለምርጫ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርት መግለጫ አቀረበ  የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ የመረጃ ማዕከል በድምጽ መስጫ ቀን እስከ ቀኑ 7 ሰ...
01/06/2026

ኅብረት ለምርጫ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርት መግለጫ አቀረበ

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ የመረጃ ማዕከል በድምጽ መስጫ ቀን እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ድረስ ከተቀበላቸው 2,258 ተቀማጭ ታዛቢዎች (Stationary Observers) ባቀረቧቸው ሪፖርቶች ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የእኩለ ቀን ረፖርት መግለጫ አቅርቧል።

የግማሽ ቀን የትዝብት ረፖርት ያቀረቡት የኅብረቱ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሳህለስላሴ አበበ ሲሆኑ የኅብረቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሃይለማሪያም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

ኅብረት ለምርጫ ፣ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገር በቀል የዜጎች ምርጫ ትዝብት (Citizen Election Observation) ለማከናወን፤ 2,258 ተቀማጭ (Sitting Observers) እና 891 ተንቀሳቃሽ (Mobile Observers) ታዛቢዎችን፣ በአጠቃላይ 3,149 ታዛቢዎችን አሰማርቷል።

የኅብረቱ ታዛቢዎች ስምሪት፤ ከትግራይ ክልል፣ በአማራ ክልል ከሚገኙ ስምንት የምርጫ ክልሎች፣ እንዲሁም አከራካሪ ከሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ውጭ ባሉ የምርጫ ክልሎችን የተከናወነ ነው።

የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርቱ መሰረት ያደረገው የኅብረቱ ታዛቢዎች በተሰማሩባቸው 2,258 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ኅብረቱ ካሰማራቸው ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎች የሰበሰባቸው መረጃዎች አሳሳቢ ሁነቶች ላይ የተደረጉ ሪፖርቶች ብቻ ነው።

ሙሉ ረፖርቱን ለማንበብ ድረ ገፃችንን ዪጎብኙ
https://cecoe.org/

The East and Horn of Africa Election Observation Network (E-HORN) ልኡክ ቡድን በህብረት ለምርጫ የምርጫ ትዝብት መረጃ መሰብሰቢያ ማዓከልን በመጎብኘት ላ...
01/06/2026

The East and Horn of Africa Election Observation Network (E-HORN) ልኡክ ቡድን በህብረት ለምርጫ የምርጫ ትዝብት መረጃ መሰብሰቢያ ማዓከልን በመጎብኘት ላይ ናቸው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፣ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ  ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት  ፕሬዝደ...
01/06/2026

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፣ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት አቶ አህመድ ሁሴን የህብረት ለምርጫ የትዝብት መረጃ መዓከልን ጎብኘትዋል ።

ህብረት ለምርጫ የድምፅ ምስጫ ቀን የትዝብት ረፖርት መቀበል ጀምሯል
01/06/2026

ህብረት ለምርጫ የድምፅ ምስጫ ቀን የትዝብት ረፖርት መቀበል ጀምሯል

ነገ ግንቦት 24 2018 ዓ.ም የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነው። ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅዎን መስጠት አይርሱ ።
31/05/2026

ነገ ግንቦት 24 2018 ዓ.ም የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ነው።

ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፅዎን መስጠት አይርሱ ።

Address

Heritage Building, 3rd Floor Cameroon Street Across From The Embassy Of Tanzania, Beside DoubleTree Hotel
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Coalition of Ethiopian Civil Society Organizations for Election - CECOE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share