06/10/2026
ዛሬ፣ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም.፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን (አመፋ) እና EcoVita Training and Consultancy በመካከላቸው የትብብር ማዕቀፍ ለመፍጠር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል። ይህ ትብብር የአመፋን የድርጅታዊ፣ የቴክኒክ እና የአሠራር አቅም ለማጠናከር ያተኮረ ነው።
በዚህ ትብብር ሁለቱ ድርጅቶች የድርጅት አቅም ግምገማና የሥርዓት ማጠናከር፣ ሥልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ፣ የሀብት ማሰባሰብና የፕሮፖዛል ዝግጅት፣ የለጋሽና የአጋር ዝግጁነት እና የክትትልና ትምህርት በጋራ ይሰራሉ።
ይህ ስምምነት በቀጣይነት ለመማር፣ የድርጅታዊ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና ዘላቂ የድርጅት እድገትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
በቀጣይ ጊዜያት ፍሬያማ ትብብር፣ የጋራ ትምህርትና ልምድ ልውውጥ በማጠናከር፣ አመፋ ለሚያገለግላቸው ማህበረሰቦች የበለጠና ዘላቂ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችሉ ጠንካራ የድርጅት ሥርዓቶችን በጋራ ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ነው።
~ ~ ~
Today, 6 October 2026, the Dr. Ambachew Mekonnen Foundation (AMF) and EcoVita Training and Consultancy signed a Memorandum of Understanding (MoU) to work together in strengthening AMF’s organizational and technical capacity.
Through this partnership, the two organizations will collaborate on organizational assessment and systems strengthening, capacity building and technical support, resource mobilization and proposal development, donor & partnership readiness, and monitoring & learning
The partnership reflects AMF’s commitment to continuous learning, stronger institutional systems, and sustainable organizational development as the Foundation grows its programmes and partnerships.
We look forward to a productive collaboration, shared learning, and stronger systems that will help AMF deliver greater and more sustainable impact for the communities we serve.