Bethel E Geletu Foundation

Bethel E Geletu Foundation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bethel E Geletu Foundation, Addis Ababa.

Envisions to see Empowered Media & Youth that would cause socio economic transformation through skills training, evidence generating researches and consultancies.

Captain's Amsale Guallu።።።።።።።።።።።።።።።።-🎯 (in 2010) Ethiopian Airlines first female pilot-🎯 Flying (flipped) Bombardier ...
09/02/2026

Captain's Amsale Guallu
።።።።።።።።።።።።።።።።
-🎯 (in 2010) Ethiopian Airlines first female pilot

-🎯 Flying (flipped) Bombardier Q400 from Addis Ababa to Gondar, achieving great success in the history of Ethiopian aviation.

🎯 The first female pilot in Boeing 767, 777, and 787.

🎯 Led all female crew in 2017 from Addis Ababa to Lagos, Nigeria & Buenos Aires (2018) .

🎯 Amsale is the only woman who led and pilot the group led by women only.

🎯Started work in Ethiopian Airlines in 2000 and is still serving till today.

Amsale Gulu is a great example for young women in Africa..................................
💥Captain Amsale Gualu:

የወዳጄ ጋዜጠኛ ዘሪሁን የሕይወት ታሪክ ...*****************ተወዳጅ ሚዲያ እንዳሰናዳው
06/02/2026

የወዳጄ ጋዜጠኛ ዘሪሁን የሕይወት ታሪክ ...
*****************
ተወዳጅ ሚዲያ እንዳሰናዳው

አባት 'ሕግ' ነው! -አባትነትም:- ፍቅሩ ከአፋዊ ይልቅ በግብር የሚኖርበት ነው!... ልጆቻችሁም ጓደኞቻችሁ አያደሉም!   ===================አባትነት ለቤት ሕግ መሆን ነው፤ በአ...
06/02/2026

አባት 'ሕግ' ነው! -አባትነትም:- ፍቅሩ ከአፋዊ ይልቅ በግብር የሚኖርበት ነው!... ልጆቻችሁም ጓደኞቻችሁ አያደሉም!
===================
አባትነት ለቤት ሕግ መሆን ነው፤ በአባዊ ሥርአት በእኛም የእድገት ልምድ ልጆች ሲያጠፉ"ቆይ ለአባትህ ባልነግር!" እንባል ነበር።

እኔም በአባትነቴ ልጆች ሲያጠፉ ጮርቃነታቸው ስሱ ስሜት ውስጥ ይከተኝና ሥርአትና ደንብን አውቀው እንዲያድጉ ካለው ኃላፊነቴ ጋር ግን ይፋጠጡብኛል።

ይህን አመዛዝኖ የማስተናገድ ጭንቅ የሚያውቀው ያውቀዋል።
ይህ ሕግነት ታዲያ ልጆች ጅ እያቴአድገው ከአባታቸው ጋር ያለው ግንኙነት ቀለልና ፈታ ያለ እንዳይሆን ሳያደርገው አይቀርም።

እናቶቻችን ግን ፍቅራቸውን በቃላት ለመግለፅ አይቸገሩም፤ ሀብታም እና ኝ ይይዝልሃልብርድረስ ፍ ። የእናቴን ወዳለሁ ብዙ ነው፤ የአባት ግን በቁጥቡ ነው ... ለምን?

ልጅ ሳለን የአባቶቻችንን መውደድ በቃላት የሰማንበት እድል እጅግ ጠባብ ነው። እኛም ስለአባቶቻችን ፍቅር ወይ አባት ስንሆን አሊያም ረፍዶ ሲያልፉ ነው የምናውቀው። እኔም አባትከ ሆንኩ በኋላ ነው በጥልቀት የገባኝ።

እናቶቹ ፍቅራቸውን በበሽበሽ ቃላት ስለሚያጅቡትም ታድለዋል፤የአባት ፍቅር ስታዲየም ላይ ግን ቲፎዞው ይሳሳል። ለዚያውም ከቲፎዞው ብዙው ረፍዶ የገባው ሳይሆን አይቀርም።

እስኪ ምን ያህሎቻችሁ ናችሁ አባቶቻችሁ በ"I Love You" እወድሀለሁ ቃላት ያንበሸበሿችሁ?

አባቶቻችን በአብዛኛው "ልባቸውን ኮሌታቸው ላይ የሚለብሱት አይነት" አይደሉም።

አንዳንዴ ድምጽ አውጥተው ይህን እንዴት እንደሚሉት ግራ የሚጋቡ ወይም ስሜቱን በቃላት አውጥቶ መግለፅ ቂልነት አድርገውም ይቆጥሩታል ብዬ አስባለሁ ይላል ጸሃፊው።

እኔም ነፍስኄር አባቴን ሳስታውስ ቃል አውጥቶ "እወድሀለው" እሸት ያለበትን ቀን መኖሩ ትዝ አይለኝም፤ ግን በድርጊት - የስስት አስተያየቱ፤ እናቴ ስትቆጣኝ ከውስጥ በመነጨ ስሜት እናቴንጠርቶ 'አሰገድ እለፊው ልጅም አይደል' የሚለው የፍቅር ተማፅኖው፥ ምሳ ላደርስለት ከስራው ቦታ ወንጂ ሆስፒታል ስደርስ የመውደድ ልክ እቅፉ፥ ረዥም ሌሊት ቁጭ ብዬ ሳጠና ፀጉሬን ደባብሶ 'ሊነጋ እኮ ነው እሸት - በቃ ተኛ!' የሚለው የልብ ስስቱ አይዘነጉኝም።

አባቴመትቶኝ አያውቅም፤ አጠገቡ ጠርቶ ያስቀምጠኝና አንዳች የቁጣ ስሜት በሌለበት ስህተቴን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ታሪክ ተረጋግቶ ይነግረኝና በተመስጦ ሳዳምጠው ቆይቼ የሚያነቃኝ "ተረዳኸው ልልህ የፈለግሁትን!" የሚለው ትሁት የነገር ማሰሪያ ጥያቄው ነው።

እነኚህ ውስጥ ሁሉ "ፍቅር በገቢር" አለበት፤ እና የምን ቃላትን ለንፋስ ማስጣት ነው ያስብላል።

በተለይ ፍርድና ቅጣት ኃላፊነቱ በእናታችን በኩል ስለሚፈፀም የፍትሕ ጉዳይ ክትትል የአባታችን ሆኖ በተለይ የምወድለት ከዱላ እኛን የመከላከያ ዘዴው ነው:-
"ጠዋት ልጅን መቆጣትና መምታት የት/ቤት ውሎውን ያደነዝዘዋል"፤ የምሽት ቁጣና ዱላ ደግሞ "ልጅን "ያቀዣል" ይላል።

ሌላው ደግሞ ጥፋት አጥፍቼ በመስኮት አምልጬ ወጣና አባቴ ከስራ ሲመለስ "እናቴን ይቅርታ "ልላት እፈልጋለሁ" ብዬው አብሬው እገባለሁ፤ ያኔ እናቴ "ቆይ! ዋጋህን ታገኛታለህ" ካለችኝ፤ እናቴን በትህትና "እባክሽ ልጆቹን ቂም መያዝ እንዳይለምዱ እለፊያቸው!" የሚለው ለእኔ ምርጥ የማሪያም መንገድ ነበር።

እነኚህ የስስት ከለላዎች ውስጥ ሁሉ ከ "I Love You" ቃላት የተሻገሩ በግብር የተገለፁ መውደዶች ከልቤ ታትመዋል።

የአባት ፍቅር በድምጽና ቃላት የነገሰ አይደለም (not loud)። ይልቅ ግብራዊው የመውደድ ልክ ልብን የሚያሳርፍ፥ የሕይወታች ጋሻ፥ ከዕለት ዕለት የሕይወት ምዕራፋችን ጋር የተጋመደ ለብርታታችንም ክንድ የሚሆን ነው።

አሁን አባት ሆኜ ሳየው፥ ያኔ እናቴ በነቢብም በገቢርም መውደዷን በቅጡ አውቄ አድጌያለሁ። የአባቴ መንገድ ለካ ያስተማረኝ የአባቶች መንገድ አለ።

ያም "እውነተኛ ፍቅር ሁልጊዜ በቃላት በድምጽ አይስተጋባም"። አንዳንዴ የዋዛ በሚመስሉ ጥቃቅን ገቢሮች፥ ግን በለሆሳስ ቻል አድርገን ባለፍናቸው መስዋዕትነቶች፤ ግን ለአፍታም ሸብረክ ባላልንባቸው ፅኑ መኖርና መገኘቶች (presence) ውስጥ ይገለጻል።

እኔ ዛሬም የማደርገው እንደ አባት - ያኔ አባቴ አንድ ሁለቴ ሌሊት ከተኛንበት መጥቶ ተገላልጠን ከሆነ አልብሶን እና ትንፋሻችንን አፍንጫችን ስር የሚያደርገውን እኔም ቀጥዬዋለሁ።

አባቶቹ ከልጆች ጀርባ ስለመኖራቸው ብዙ ታውቆና ተለይቶ ባልሆነ ሁኔታ ስለልጆቻቸው ደህንነትና እድገት በስሱና በፀጥታ ውስጥ እንደጥላ መኖራቸው አሌ አይባልም።

እናም ዛሬ ዝምተኛው ነፍስኄ አባቴን በወናፍ ቃል ሳይሆን በገዘፈ ገቢራዊ ድርጊት በጥልቅ ፍም ፍቅሩ ገርቶና ቃኝቶ ለልጆቼ ጥሩ የአባትነት አብነት ሆኖኛልና አባትነት በጩኸት የማይገን መስዋዕትነቱም በለሆሳስ የሚከወን የድል አክሊል የማይሻ የውዴታ ግዴታ ጅግንና መሆኑን አይቻለሁ።

✨ ፍቅር ሁል ጊዜ በቃላት ግለፁኝ አይልም፤ ይልቁን በይዘቴ ልክ በተግባር ኑሩኝ ባይ ነው።
(Points added: # lifestyle)

************
"ልጆቻችሁ ጓደኞቻችሁ አይደሉም"
===============
በመራር አስተያየት እንዳይቆጠር - ይህ ደረቅ ሀቅ ነው።
It's not a Harsh Statement, but it's Truth.

ልጆችዎ በምርጥ ጓደኝነት ሊያስብዎ የሚችሉበት ዝንባሌ እንደሚኖር አይገምቱ።

ልጆች ለሚያከናውኗቸው ለውሎ አመሻሻቸው ሁሉ ወላጅ አብሯቸው እንዲወስን እንደሚሹ አትጠብቁ።

በስህተቶቻቸውም ጭምር ስቀው ማለፍ እና እግር በእግር እየተከተለ ካላረምኩ ከሚላቸው አውድ ርቀው እና ከቁጥጥር ዘና የሚያደርግ ሁኔታን ይፈልጋሉ።

በቃ እርስዎ እንደ ወላጅ ከጓደኝነት ይልቅ ልጆች የሚሹት በወላጅነት ኃላፊነት አጥር ውስጥ እንዲወሰኑ ነው።

ልጆች ሊቀበሉት ባይጥማቸውም ወላጆች የሚያስቀምጡት አይሞከሬ የደንብ ቀይ መስመር ድንበሮች አሉ።

ልጆች ብዙ ባይመቿቸውም ወላጆች ልጆችን ተጠያቂ የሚያደርጉባቸው የማይደራደሯቸው ጉዳዮች አሉ።

አንዳንዱን ነገር ግድ የለም እስኪ ይሁን ብለው ማለፍ ሲችሉ ወላጆች አይሆንም አይደረግም "No" ይላሉ።

ወላጆች ለልጆቻቸው ጓደኛ የመሆን እድላቸው የሚሳሳው በተከታዮቹ ጥቂት ምክንያቶች ሳቢያ ነው።

- ጓደኝነት በአቻዎች መካከል ነው፥
- በጓደኞች መካከል አንዱ የሌላውን ባህሪ የማረቅና የማረም ኃላፊነት ግድ አይሆንበትም፥
- ማህበራዊ እሴትን የማስጠበቅ፥ ለልጆች መጪ የነገ ሕይወት አጋዥ ከሕይወት ልምድ የሚቀዳ ተሞክሮን የማጋራት ድርሻ ግድ አይደለም ሲባል በጓደኝነት 'Must to do list' ውስጥ የለም ማለት ነው።

ይሁንና ከላይ የተጠቀሱት የልጆች መጪ ሕይወትን የመቅረጽ ድርሻ ግን የወላጆች ግዴታ ነው፤ እነኚህ የወላጆች የተቀደሰ አይታለፌ የከባድ ሚዛን ድርሻ ናቸው።

እናም ልጆች ዓይናቸውን ሲያንቀዋልሉ፥ በሮቻቸውን ወርውረው ሲዘጉ፥ ሲያለቅሱ ጭምር አይይ እንዲህ አይደረግም! እንዲህ አትሁኑ! የምትለዋ ተግሳፅ ከወላጆች ይጠበቃል።

በቃ ይህን አይነት የመዋቅራዊ ግንኙነት ስዕል ነው ወላጆች ስለወላጆቻቸው ሚና ያላቸው እሳቤ።

ልጆች የልብ መሻታቸው በፍቅር የሚያርማቸውን ወላጅ ሚናው ሳይደበላለቅ ማግኘት ነው።

ያ ወላጅ በፍቅር ተመራጭ የሕይወት አቅጣጫ እንዲያሳያቸው ይሻሉ።

እና ዓለም ሁሉ ከሳሪ ናቸው ተስፋም የላቸው ሲላቸው ልጆቹን በፍቅር አይዟችሁ ብሎ መጪውን ጊዜ በስኬት ትሻገራላችሁ ብሎ ስለመቻላቸው - እንዲችሉም በአስቻይነት አብሮ የሚቆም ወላጅን ነው የሚፈልጉት።

እናም እነኚህ ልጆች አድገው ትልቅ ሰው ሲሆኑ - በጠራ እይታ የእድገታቸውን ሂደት በምልሰት (in flashback) ሲቃኙ - እውነታውን በቅጡ ይገነዘባሉ። ወላጆች አታድርጉ! አይሆንም! አይቻልም! አይሞከርም! ያሏቸው ጉዳዮች ሁሉ ስለፍቅር ተብሎ እንደሆነ ልጆቹ ሲያድጉ ይረዳሉ (Children later on understand as those NOs emanate from love & parental protection).

እነኚያ የወላጆች ደንቦች ለካ እኛን ከክፉ እንደ ጋሻ የሚከላከሉ እንዲሁም እንድናከብራቸው የተቀመጡ የሥነ ሥርአት መመሪያዎችም ለእኛ የምግባር አቅጣጫ አመልካቻችን ነበር ለካ ብለው ልጆቹ ቆይቶም ይገነዘቡታል።

እናም ያኔ ልጆቹ - 'እናት እና አባት' ብቻ እንዲሆኑላቸው የፈለጓቸው ወላጆቻቸው ለካ እውነተኛ ጓደኞቻቸው በፍቅር ያሞቋቸውና እንደ ጋሻም የከለሏቸው እውነተኛ ጓደኞቻቸው እነሱ እንደነበሩ ቆይቶም ቢሆን ይገነዘባሉ።

እናም ወላጆች ለልጆቻቸው ጓደኞችም ናቸው ለካ! ግን በጊዜ ልዩነት። ሀሳብ አስተያየቶች እያነሳን ብንመክርበትስ! ፤ ልምዶቻችንን ጭምር እያከልን ተሞክሮ ብንጋራስ!

(Source:

In Loving Memory of Zerihun Girma : Ethiopian Hospitality & Tourism Journalist, INDUSTRY GURU, Strategist, Master Planne...
06/02/2026

In Loving Memory of Zerihun Girma :
Ethiopian Hospitality & Tourism Journalist, INDUSTRY GURU, Strategist, Master Planner, NATIONWIDE EXPLORER, and National Visionary >>>>>>>>>>

Ethiopia mourns the passing of Zerihun Girma, one of the nation’s most dedicated and influential voices in HOSPITALITY, TOURISM, and MEDIA—a distinguished journalist, INDUSTRY GURU, Strategist, Master Planner, and NATIONWIDE EXPLORER whose life was defined by SERVICE, INTEGRITY, HUMILITY, and LOVE FOR COUNTRY.

Born on August 18, 1983 (Nehasse 12, 1975 E.C.) in Gumayde, to Ato Girma Sahlu and Woizero Adunya Alemu, Zerihun’s journey reflected DISCIPLINE, CURIOSITY, and PURPOSE. He completed his primary education in Gumayde and secondary education in Konso and Arba Minch. A graduate of Hawassa Teachers’ Training College (Chemistry), he began his career as a CHEMISTRY TEACHER in the Gurage Zone, earning deep respect from students and colleagues.

In 2009 (2001 E.C.), driven by a passion for national storytelling, he joined the field of JOURNALISM in Addis Ababa. Over more than 17 YEARS, he became one of Ethiopia’s LEADING Hospitality and Tourism Journalists, working with major radio stations including Zami 90.7 FM, Debub FM 100.9, and Ethio FM 107.8. As a true NATIONWIDE EXPLORER, he traveled extensively across ETHIOPIA, documenting destinations, cultures, and communities, and bringing the nation’s rich heritage closer to the public through RADIO, TELEVISION, and SOCIAL MEDIA.

Widely respected as an INDUSTRY GURU, Zerihun was an expert in TOURISM POLICY, HOSPITALITY INVESTMENT, PUBLIC RELATIONS, and MEDIA CONTENT DEVELOPMENT. He held TWO Bachelor’s Degrees and was actively pursuing an MBA PROGRAM, reflecting a lifelong commitment to LEARNING and LEADERSHIP.

He was a KEY PLANNER and STRATEGIC ADVISOR for major national and regional platforms, including the MICE East Africa Forum, the Hotel Show Africa International Hospitality and Tourism Investment Tradeshow, and other MAJOR NATIONAL EVENTS, contributing significantly to Ethiopia’s MICE, INVESTMENT, and DESTINATION DEVELOPMENT AGENDA.

His landmark media works include “Wub Hager” (Ethio Tourism & Hospitality TV and ESAT TV), which played a vital role in TOURISM AWARENESS and DESTINATION PROMOTION. He was also developing “Guzoye / My Travel” and “MICE Addis”, programs dedicated to TRAVEL STORYTELLING and MICE DEVELOPMENT. As a respected TRAINER, he was especially known for URBAN TOURISM JOURNALISM capacity-building.

Zerihun received OVER A DOZEN SECTOR-BASED AWARDS for STRATEGIC PLANNING, INCENTIVE PROGRAMS, and INDUSTRY IMPACT, establishing him as one of the MOST INFLUENTIAL and TRUSTED VOICES in Ethiopia’s hospitality and tourism ecosystem.

Beyond professional achievements, Zerihun Girma was admired for his HUMILITY, KINDNESS, and RESPECT FOR PEOPLE. A devoted HUSBAND and FATHER of TWO (SON and DAUGHTER), he loved traveling across ETHIOPIA with his family and instilling PATRIOTISM and CULTURAL PRIDE in his children. He is survived by his wife, THREE BROTHERS, and THREE SISTERS.

Zerihun Girma passed away at the age of 42. His funeral service was held on February 6, 2026 (Tir 29, 2018 E.C.) at Arba Minch Medhane Alem Church.

Though his voice is now silent, his LEGACY LIVES ON—in the PLATFORMS he BUILT, the PROFESSIONALS he MENTORED, and the NATIONAL VISION he CHAMPIONED.
May his soul rest in ETERNAL PEACE.

May his family find STRENGTH and COMFORT.
Zerihun Girma will FOREVER remain in our HEARTS and HISTORY.
We Love and Respect You Forever

By :
Kumneger Teketel WG
OZZIE Business & Hospitality Group

ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ግርማው አበበ (ዶ/ር) በተመድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በሳይንሳዊ አማካሪዎች አባልነት ተሾሙ  =====================የተባ...
06/02/2026

ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ግርማው አበበ (ዶ/ር) በተመድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በሳይንሳዊ አማካሪዎች አባልነት ተሾሙ
=====================
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለመጀመሪያ ባቋቋመው "ገለልተኛ ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሳይንሳዊ ፓነል" ውስጥ ኢትዮጵያዊው የዘርፉ ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ተካተዋል።

ይህ ሹመት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የኤአይ (AI) አስተዳደርና ፖሊሲ ቀረጻ ላይ ያላትን ውክልና የሚያረጋግጥ ታሪካዊ እርምጃ ስለመሆኑ ነው የተገለጸው።

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እ.ኤ.አ የካቲት 3 ቀን 2026 ለጠቅላላ ጉባኤው ባቀረቡት ጥቆማ መሰረት፤ ከዓለም ዙሪያ የተመረጡ 40 ታዋቂ ባለሙያዎች ለሦስት ዓመታት በፓነሉ ውስጥ ያገለግላሉ ተብሏል።

በዚህም ፓነል ውስጥ ዶ/ር ግርማው ከካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ሜክሲኮ፣ ሴኔጋል፣ ግብፅ እና ፊንላንድ ከመጡ ቀዳሚ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን በጋራ እንደሚስሩ ተነግሯል።

ፓነሉ የተቋቋመው እ.ኤ.አ በ2024 በተካሄደው የ"Summit of the Future" ጉባኤ ላይ በጸደቀው፤ "Global Digital Compact" መሰረት ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚመጡ ዕድሎችን፣ ስጋቶችንና ማህበራዊ ተፅዕኖዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በመገምገም ለዓለም አቀፍ ፖሊሲዎች ግብዓት ማቅረብ ነው።

ዶ/ር ግርማው አበበ በአሁኑ ወቅት በማይክሮሶፍት "AI for Good" የምርምር ማዕከል ዋና ሳይንቲስትና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ ቀደም ሲል በIBM Research እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ተመራማሪነት ሰርተዋል።

በተጨማሪም ከሀርቫርድ እና ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ኤአይ (AI) በጤናው ዘርፍ በተለይም ውስን ግብዓት ባለባቸው አካባቢዎች በሽታን ለመለየት እንዲውል ከፍተኛ ምርምር አድርገዋል።

( )

"ጥምቀት የትህትና፡ የፍቅር እና የአብሮነት ምሳሌ ነው"================ብርሃነ ጥምቀቱ ሃይማኖታዊ ትርጓሜው ባልተናነሰ ለማህበራዊ እና ባህላዊ እሴት መጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑ ነ...
02/02/2026

"ጥምቀት የትህትና፡ የፍቅር እና የአብሮነት ምሳሌ ነው"
================
ብርሃነ ጥምቀቱ ሃይማኖታዊ ትርጓሜው ባልተናነሰ ለማህበራዊ እና ባህላዊ እሴት መጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑ ነው በጃን ሜዳው ደማቅ የሃይማኖታዊው ሥርአት የተነገረው።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የበዓለ ጥምቀቱ ሃይማኖታዊ እና የባህላዊ ሕብረ ቀለማዊ አውድ እንዲህ ይመስላል።

ከበዓሉ ረድኤት በረከት የምናገኛበት ያድርግልን!
ታቦታቱን ከመንበራቸው፡ ካህናቱን ከደብራቸው አይለይብን!

"ከጎዳና ያነሳኸኝ፡ ከልመና ያወጣኸኝ፡ ወድቄ ሳለ ያከበርከኝ" - አሉ አንዲት እናት ማስተር አብነት ከበደን። ምስኪናንን እንዳሰብህ ምህረቱን ይላክልህ! ወንድሜ ጨርሶ ይማርህ!=========...
02/02/2026

"ከጎዳና ያነሳኸኝ፡ ከልመና ያወጣኸኝ፡ ወድቄ ሳለ ያከበርከኝ" - አሉ አንዲት እናት ማስተር አብነት ከበደን። ምስኪናንን እንዳሰብህ ምህረቱን ይላክልህ! ወንድሜ ጨርሶ ይማርህ!
=========================
እኚህና አረጋዊት እናት በጥቃቃና የጉሊት ንግድ ራሳቸውን በዘለቄታው እንዲያቋቁሙ ከሌሎች አጋዦች የተላከውን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የሞራል ብርታትም ያደረገላቸው እናት ናቸው እምባ እየተናነቃቸው የተናገሩት።

አብነት እንደ ስሙ አብነትነቷ የተዘነጉ ሰዎችን ከልቡ እቅፍ አድርጎ አይዟችሁ የሚልበት የሰው የውሃ ልክነት ምግባሩ እጅግ ያስደምመኛል። ራሱን ጥሎ ረስቶ የተቸገሩትን ከልብ ቸርነት ለመደገፍ፡ ሀገራዊ አደጋ ባጋጠመ ቁጥራ የዕለት ፍጆታ የሚሆን ቁሳቁስ ተሸክሞ በማድረስ፡ ካዘኑት ጋር አብሮ አልቅሶ በአይዟችሁ አፅናንቶ ለተገፉ ወገኖች መኖር መታደል ነው።

ቀነ ለጨለመባቸውና ለተዘነጉ በርካቶች አለሁላችሁ እንዳልክ መድህን ዓለም ክርስቶስ አለሁ ይበልህ!

ማስተር አብነት ዛሬ ላይ ሕመም አድክሞት በሕክምና ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም በጉብዝናው የስፓርተኝነት ዘመኑ ካደገበት የከምባታ ጠንባሮ ዞንና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንስቶ በመላ ኢትዮጵያ በሞተር ሳይክል ላይ የሚያሳየው ትንግርታዊ የአትሌቲካዊ ትርኢት አስደማሚ ነበር።

እንዲህ ተደረገልኝ ብለህ የምትመሰክርበትንና በአደባባይ ለምስጋና እንዳትመጣ የእግዚያብሔር ቅዷስ ፈቃዱ ይሁን!

እቴጌ ምንትዋብን የሚዘክር ባለታሪክ ቀመስ ዘውግ የፊልም ሥራ ሊጀመር የመግባቢያ ስምምነት መርሐ ግብር ተከናወነ።በጎንደሩ በተፈረመው ስነ ስርአት ላይ እንደተገለጸው ፊልሙ በደራሲ እና ዳይሬክ...
30/01/2026

እቴጌ ምንትዋብን የሚዘክር ባለታሪክ ቀመስ ዘውግ የፊልም ሥራ ሊጀመር የመግባቢያ ስምምነት መርሐ ግብር ተከናወነ።

በጎንደሩ በተፈረመው ስነ ስርአት ላይ እንደተገለጸው ፊልሙ በደራሲ እና ዳይሬክተር ማህሙድ ዳውድ የሚዘጋጅ ነው።

የፊልሙ ዋነኛ ዓላማ ትውልዱ ራሱን እንዲመስል መሠረት የሚጥል መኾኑ ተጠቁሟል። ፊልሙን በሁለት ዓመት ውስጥ ለመጨረስ መታሰቡም ተመላክቷል።

ምንትዋብን ወክላ በፊልሙ ላይ የምትተውነው ተዋናይት ሜላት ነብዩ ስትኾን የእቴጌ ምንትዋብን ታሪክ ተላብሳ ለመሥራት ከሦሥት ዓመታት በላይ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሳለች።

የፊልሙ ሥራ መጀመሩን የገለጸችው ተዋናይት ሜላት በቅርብ ጊዜያት ተጠናቅቆ ለዕይታ እንደሚበቃም ገልጻለች።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው እቴጌ ምንትዋብ ለአሁኑ ትውልድ አርዓያ መኾናቸውን ማሳየት የሁሉም ኀላፊነት ሊኾን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፊልሙ ሥራ እስኪጠናቀቅም የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ታሪክ አዋቂ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለባለሙያዎቹ እገዛ እንዲያደርጉም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጠይቀዋል።

የፊልሙ ደራሲ እና ዳይሬክተር ማህሙድ ዳውድ የጎንደር ታሪክ ተነግሮ የማያልቅ እና ለትውልድ የሚተላለፍ ሃብት መኾኑን ጠቅሶ የእቴጌ ምንትዋብን ታሪክ በፊልም ለመሥራት መመረጣቸው ትልቅ ክብር መኾኑን ተናግሯል።

(ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ)

ዕድሜህን እርሳው! በተለይ በሕይወት ልታሳካው የምትሻው ግብ ካለ፡ከዳር ለምታደርሰው ስኬት አሁናም ድረስ ወጣት ነህ!
27/01/2026

ዕድሜህን እርሳው!
በተለይ በሕይወት ልታሳካው የምትሻው ግብ ካለ፡
ከዳር ለምታደርሰው ስኬት አሁናም ድረስ ወጣት ነህ!

"የእግዚአብሔር ሰው ሲመጣ ዝናቡ ይመጣል" - አሉ አሪዎች -አቡነ ዕንባቆምን ድርቅ በመታው ቀያቸው ሲቀበሉ።አባታችን ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ! እረፍተ ነፍስ ይሁንልዎ!==============...
27/01/2026

"የእግዚአብሔር ሰው ሲመጣ ዝናቡ ይመጣል" - አሉ አሪዎች -አቡነ ዕንባቆምን ድርቅ በመታው ቀያቸው ሲቀበሉ።
አባታችን ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ! እረፍተ ነፍስ ይሁንልዎ!
==========================
ይህን የተናገሩት የአሪ ማህበረሰብ አንድ አረጋዊ መሆናቸው ይወሳል። ጊዜው አቡነ ዕንባቆም የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩበት ዘመን ነው።

አሪዎች በሚኖሩበት አካባቢ ዝናብ ከጠፋ አመታት ተቆጠረ። ዝናብ ሲጠፋ የሀገራችን ኑሮ ምን ዓይነት የከፋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገባ መዘርዘር አያሻም።

ያኔ በአካባቢው ለስብከተ ወንጌል ይሯሯጡ ለነበሩ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት እኚህ አረጋዊ በዚያ ጭንቅ ወቅት መፍትሔው ምን እንደሚሆን ከቀደምት አባቶቻቸው ሲነገር የሰሙትን ይነግሯቸዋል።

ለካ ቀደም ባሉት ዘመን ዝናብ በጠፋ ጊዜ ወደ ሕዝቡ እየሔዱ ይጸልዩ ዝናቡም ከመሸገበት ፈጥኖ ይመጣ ኖሯል።
ዜናውን ለአቡኑ ያደርሳሉ። አቡነ ዕንባቆም ጊዜ አላባከኑም። ቦታው መኪና አይገባበትም - ጭልጥ ያለ ገጠር። ከፊሉን በሞተር ሳይክል ቀሪውን ደግሞ በእግር እያቆራረጡ ገሰገሱ።

ከቦታው ሲደርሱ "የእግዚአብሔር ሰው መጣ" እያሉ የሀገሬው ሕዝብ ተሰበሰበ። በተርጓሚዎች አማካኝነት ተነጋገሩና ጸሎተ ምሕላ ደረሰ። እንደተጠናቀቀ ሰማዩ የተቀደደ ያህሌ ዝናቡን ዠቅ አድርጎ ለቀቀው። ይሄኔ ልዩ ደስታ ኾነ -ለመጠመቅም ያንገራገረ አልነበረም።

ይህ የሰተማው ጂንካ ለአገልግሎት በተሄደበት ጊዜ ነው። አቡነ ዕንባቆም ማረፋቸውን ስሰማ ትዝ አለኝ ብሎ አጋርቷል አንድ ወንድማችን። ... በረከታቸው ይደርብን!

Proud to spotlight these Passionate Women who Redefine communications landscape in Ethiopia.=====================From in...
24/01/2026

Proud to spotlight these Passionate Women who Redefine communications landscape in Ethiopia.
=====================
From industry pioneers to strategic powerhouses, these leaders are setting new benchmarks for excellence and driving brand narratives at the highest levels.

Recognised among the top women shaping the PR industry in Ethiopia, these a are at the forefront of innovation and strategic growth. Join to celebrate:

•⁠ ⁠Rahel Zewdu Kebede, Communications Specialist, USAID Ethiopia

•⁠ ⁠Samrawit Girma, Non-Alc Category Brand Manager, The HEINEKEN Company.

•⁠ ⁠Yoadan Tilahun, Founder & CEO, Flawless Events

•⁠ ⁠Wynne M., Head Of Communication, African Union Commission

•⁠ ⁠Hanna Atnafu, Manager, Corporate Communications, Ethiopian Airlines

•⁠ ⁠Billene Seyoum W. , Press Secretary, Office of The PM

•⁠ ⁠Ethiopis Tadesse, DTM, PMP , Communications Specialist

•⁠ ⁠Elshaday Gebeyehu, Communications Officer at the World Food Programme Ethiopia

•⁠ ⁠Rahwa Gebremeskel, Corporate Communications Specialist

•⁠ ⁠Rahel Assefa, VP Marketting, Ethiopian Airlines

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bethel E Geletu Foundation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share