Ethiopian Media Women Association - EMWA

Ethiopian Media Women Association - EMWA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Media Women Association - EMWA, Non-Governmental Organization (NGO), Arada Sub-city, Wereda 1, Kebele 05, House No. 601, Ethiopia, P. O. Box: 6473 Tel. : (251-11) 1116852/62, email/ethiopianmwa@gmail. com 2, Addis Ababa.

Ethiopian Media Women Association (EMWA) is non-partisan, non-for-profit association established by likeminded female journalists and media professionals to promote women's issue in and through the media.

11/04/2026
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ምክትል የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆነችው ማያ ምስክር የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ለላቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያዘጋጀው...
18/03/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ምክትል የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆነችው ማያ ምስክር የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ለላቁ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያዘጋጀውን ሽልማት አገኘች። ማያ “ሲፍተር” በሚል የኤሌክትሮኒክ መጽሔቷ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሽፋን እንዲያገኙ ላደረገችው አስተዋጽዖ ሽልማቱን ተበርክቶላታል። ሽልማቱን ከተቀበለች በኋላ ማያ “ይህ ሽልማት የተነሳሁለት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ትኩረት እንዲያገኙ የማድረግ ዓላማ ትክክል እንደነበረና ጠንክሬ ልቀጥልበት እንደሚገባ አስገንዝቦኛል” ብላለች።
ማያ እንኳን ደስ አለሽ!

Ethiopian Human Rights Defenders Center recognized Maya Misikir, Deputy Board Member of the Ethiopian Media Women Association, for amplifying human rights issues through “Sifter” – a webbased newsletter.
She was honored for her contribution through her electronic magazine “Sifter”, which has helped bring wider coverage to human rights issues.
After receiving the award for outstanding human rights advocates Maya said, “This award has reminded me that my goal of bringing attention to human rights issues was the right one, and it has encouraged me to continue with even greater determination.”
Her recognition is not only a personal achievement but also a powerful validation of the role women in media play in amplifying human rights issues.
Congratulations Maya!!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር (ኢትመባሴማ) ከግራስሩት ሶከር የዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ኤለና ኮሄን  ጋር ውይይት አደረገ። ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት በጋራ የተጀመ...
26/02/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር (ኢትመባሴማ) ከግራስሩት ሶከር የዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ኤለና ኮሄን ጋር ውይይት አደረገ። ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት በጋራ የተጀመረውን የወጣት ወንዶችና ሴቶች የአእምሮ ጤና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ፕሮጅክት ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር።
ውይይቱ የወጣት ወንዶችና ሴቶች አእምሮ ጤና አጠባበቅ ጉዳይ ከሬዲዮ ፕሮግራም ወደ መደበኛ የመገናኛ ብዙኃን አሠራርና ፖሊሲ ውስጥ በማስገባት ይህ ጉዳይ የዘወትር የማኅበረሰባችን አጀንዳ የሚሆንባቸው ሥልቶች ላይ አተኩሯል። ለዚህ ዓላማ መሳካት የተገኙ ውጤቶችንና ልምዶችን በተገቢው መንገድ መሰነድ፣ ማስፋፋትና አጋሮችን ማብዛት ወሳኝ ጉዳዮች ተደርገው ተለይተዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና ግራስሩት ሶከር ከአዳማ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ፣ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ከመቀሌ FM ጋር በመተባበር የወጣት ወንድና ሴቶችን የአእምሮ ጤና አጠባበቅ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የሬድዮ ፕሮግራሞችን እያሰራጩ ነው።

23/02/2026

ሴቶች ማለፍ የሚችሏቸው የአመራርነት ማነቆዎች

: ለሴቶች የአመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ለመድረስ መንገዱ በፈተና የተሞላ፣ በየጊዜው አዳዲስ ችግሮች የሚገጥሙበት ቢሆንም፣ ይህንን ተቋቁሞ ከአመራርነት ደረጃ መድረስ ይቻላል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጀም ሆነ በአገር አቀፍ የሴት አመራሮች ቁጥር አነስተኛ በሆነበት፣ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች ተገማች ቢሆኑም፣ ሴቶች የገጠማቸውን ችግሮች እንደ ዕድል በመጠቀምና መፍትሔ በማበጀት አመራርነት ላይ ደርሰው ለውጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡

ፈተናዎችን እንደ ዕድል የተጠቀሙ ሴቶችም፣ ባሉበት ኃላፊነት ተጨባጭ ለውጦችን ሲያመጡ ይስተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያም ቁጥራቸው ጉልህና ሕዝብ በሚያውቃቸው መልኩ ጎልተው የወጡ ባይሆንም በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማኅበራዊ ዘርፍ በአመራርነት በመምጣት ለተቋማቸው ለውጥ ያስመዘገቡ አሉ፡፡
ከማኅበረሰቡ፣ ከሥራ አጋሮቻቸው ብሎም ከቤተሰብ የሚገጥሟቸውን ጫና ተቋቁመው አመራርነት ደረጃ በመድረስና አርዓያ በመሆን በዙሪያቸው ያሉ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ጉልህ ሚና የሚጫወቱም አሉ፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና የኢትዮጵያ ሴት ማኅበራት ቅንጅት በጋራ ያዘጋጁት የሴቶች አመራርነት ማነቆዎችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውም፣ ሴቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች እያለፉ አመራርነት ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ልምድ ለመለዋወጥ ነው።

በውይይቱ ላይ መነሻ ሐሳብ ያቀረበችው ጋዜጠኛና የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ዓባይነሽ ብሩ፣ በኢትዮጵያ በፖለቲካ ተሳትፎ በተለይ ከ2018 ዓ.ም. ወዲህ ሴቶች የተሻለ ቦታ አግኝተው የ...

🔗 ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/151987/

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ↠ bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር ↠ bit.ly/35qeNwV
ሊንክድኢን ↠ bit.ly/3S0k6uB
ኢንስታግራም ↠ bit.ly/44Iiuxb
ቴሌግራም ↠ bit.ly/3Qb4N1M
ዩቲዩብ ↠ bit.ly/3p0jUQY
ቲክቶክ ↠ bit.ly/3Ruxsyv
ትሬድስ ↠ bit.ly/466VBCG

🧾 የስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com
📢 የጨረታ ማስታወቂያዎች ↠ ReporterTenders.com

📩 ለዜና ጥቆማ እና መረጃ፡ [email protected]

✍️ ነጻ ፕሬስ፣ ነጻ ሐሳብ፣ ነጻ መንፈስ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከቢቢሲ ሚዲያ አክሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡና በአዲስ አበባ ለሚኖሩ አባል ሴት ጋዜጠኞች የዲጅታል አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ...
20/02/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ከቢቢሲ ሚዲያ አክሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡና በአዲስ አበባ ለሚኖሩ አባል ሴት ጋዜጠኞች የዲጅታል አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢቢሲ ሚዲያ አክሽን ፕሮጀክት መሪ ጽዮን ሞላ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያ ለዲጅታል መገናኛ ብዙኃን የቀረበ በመሆኑ ሴት ባለሞያዎች ራሳቸውን በዘርፉ በማሳደግ ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። “ለሴቶች የዲጅታል ሚዲያ ተሳትፏቸውን ማሳደግና ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን እንዲከላከሉ የሚያስችል ስልጠና መስጠት ወሳኝ ተግባር” መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት ትርፌ እምሻው ማኅበሩ በተመሣሣይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለሦስትኛ ጊዜ ስልጠና መስጠቱን አስታውሰው ሰልጣኞች ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ሥራ በመለወጥ ሥልጠናውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳሰበዋል።
መሠል ስልጠናዎች አባላት በሥራቸው ምክንያት የሚደርሱባቸውን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል እንዲሁም ብቁና ተወዳዳሪ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎችን ለማፍራት እንዲሁም በዲጅታል ሚዲያ ተጠቅመው ውጤታማ ሥራ መሥራት የሚችሉበትን አቅም እንዲፈጥሩ የማድረግ ዓላማ ያነገበ መሆኑን አስረድተዋል።

ማኀበራችን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች፣ ባለቤትና ሥራ አስፈጻሚ በነበሩት በአቶ አማን ፍስሀ ጽዮን ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን ይገልጻል። አቶ አማን የራሱ ቀለም ያለው መገናኛ ብዙኃን በመመስረት...
11/02/2026

ማኀበራችን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች፣ ባለቤትና ሥራ አስፈጻሚ በነበሩት በአቶ አማን ፍስሀ ጽዮን ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን ይገልጻል። አቶ አማን የራሱ ቀለም ያለው መገናኛ ብዙኃን በመመስረት ለጋዜጠኝነት ሞያ ላበረከቱት አስተዋጽዖ አክብሮታችንን እንገልጻለን።
አቶ አማን የማኅበራችን ህልውና አደጋ ላይ በወደቀበት ጊዜ የበኩላቸውን ድጋፍ በማድረግ ማህበሩ እንዲቀጥል ታለቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ማህበራችነን በዋና ሥራ አስፈጻሚ አማን ፍስሀ ጽዮን ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን ይገልጻል። ለጣብያው ሠራተኞች፣ ባልደረቦቻቸው፣ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና የኢትዮጵያ ሴት ማኅበራት ቅንጅት በጋራ ያዘጋጁት የሴቶች አመራርነት ማነቆዎችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባዔ ተካሄደ። በውይይቱ...
11/02/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበርና የኢትዮጵያ ሴት ማኅበራት ቅንጅት በጋራ ያዘጋጁት የሴቶች አመራርነት ማነቆዎችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባዔ ተካሄደ። በውይይቱ ላይ ሴቶች ወደ አመራርነት እንዳይመጡ የሚያደርጓቸው ማነቆዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ሐሳብ የቀረበ ሲሆን ፓናል ውይይትም ተካሂዷል።
ተወያዮች የተቋማት መሪዎች ለሴት ሐላፊዎች ሙሉ ሐላፊነት ለመስጠት መቸገር፣ የሴቶችን ፍላጎቶች መሠረት ያላደረጉ የሥራ ከባቢዎች፣ የአሠራር፣ የምዘናና የምደባ ሥርዓት መኖር እንዲሁም የልምድና ክህሎቶች መለዋወጫ መድረኮች ውሱንነት የሚሉት በማንቆነት የተነሱ ዐበይት ጉዳዮች ናቸው።
በውይይቱ ላይ ተቋማት ሴቶች ወደ አመራር መጥተው ወጤታማ የሚሆኑባቸውን የሥራ ከባቢዎች እንዲሁም የሴቶችን ፍላጎቶች መሠረት ያላደረጉ የአሠራር፣ የምዘናና የምደባ ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባቸው ተገልጿል። ሴቶችም ውጤታማ መሪዎች ለመሆን የሚያደረጓቸውን ሥልቶች መጠቀም ይገባቸዋል ተብሏል። ለዚህም የታቀደበት የጊዜ አጠቃቀም ልምምድ ማዳበር፣ ራስን ለማበልጸግ የሚረዱ ጥምረቶችን መቀላቀል፣ ለሴቶችም ለወንዶችም ምቹ የሆኑ የሥራ ከባቢዎች እንዲኖሩ መሥራት፣ ራስን በሁሉም መስክ ማሳደግያ ሥልቶችን መቀየስ እንዲሁም የአመራር ኃላፊነትን እንደ ሸክም ሳይሆን እንደ ዕድል ማየት፣ የርስ መደጋገፍያና መማማርያ መድረኮችን ማደራጀት አስፈላጊ ሥልቶች ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ናቸው።
በውይይቱ ላይ ከሴት መር ድርጅቶች፣ በሴቶች ጉዳዮች ላይ ከሚሠሩና ከትምህርትና ሥልጠና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙኃን የተጋበዙ ባለሞያዎች ላይ ተሳትፈዋል።

CALL FOR EXPERT TRAINERS
09/01/2026

CALL FOR EXPERT TRAINERS

Address

Arada Sub-city, Wereda 1, Kebele 05, House No. 601, Ethiopia, P. O. Box: 6473 Tel. : (251-11) 1116852/62, Email/ethiopianmwa@gmail. Com 2
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+2511116852

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Media Women Association - EMWA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Media Women Association - EMWA:

Share