Thomando

Thomando Striving To Build Positivity All Over The World!

 -አመክንዮ (Logic & Mindset)👉በቀን ስንት ሰዓት ስልካችን ላይ መረጃዎችን በማንበብ እናሳልፋለን? ለጤና፣ ለገንዘብ አያያዝ፣ ለቴክኖሎጂና ለስኬት የሚረዱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጽሁ...
12/04/2026

-አመክንዮ (Logic & Mindset)
👉በቀን ስንት ሰዓት ስልካችን ላይ መረጃዎችን በማንበብ እናሳልፋለን? ለጤና፣ ለገንዘብ አያያዝ፣ ለቴክኖሎጂና ለስኬት የሚረዱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጽሁፎችን እናነባለን።
ግን ጥያቄው እዚህ ጋር ነው፤ ባነበብነው ልክ ህይወታችን ላይ ለምን ለውጥ አይታይም?"
👉ምናልባት
#የመረጃ መጥለቅለቅ (Information Overload)፦ አእምሯችን መረጃን ከማከማቸት ባለፈ የማውጠንጠኛና የመተግበሪያ ጊዜ እያጣ ይሆን?
#የማወቅ ስሜት እንጂ #ዕውቀት አለመኖሩ፦ አንድን ነገር ስላነበብነው ብቻ ያወቅነው ይመስለናል፤ እውነተኛ ዕውቀት ግን ከተግባር ነው የሚመነጨው።
#የማሳወቂያዎች (Notifications) ረብሻ፦ አንዱን ጠቃሚ ነገር አንብበን ሳንጨርስ ሌላ መረጃ ይደርሰናል፤ ይህም ትኩረታችን እንዲበታተን ያደርጋል።
#ከጥልቅ ንባብ ወደ አጉራሽ ንባብ፦ መጽሐፍትን በጥልቀት ከማንበብ ይልቅ አጫጭር ጽሁፎችንና ቪዲዮዎችን ብቻ መመልከት ጥልቀት የሌለው ትውልድ እየፈጠረ ይሆን?

 👉​በአንድ ወቅት፣ ሁለት እንቁራሪቶች ምግብ ፍለጋ ሲዘሉ ሳያውቁት በአንድ ግዙፍ የወተት ገንዳ ውስጥ ዘለው ገቡ። ገንዳው ጥልቅ፣ ግድግዳው ደግሞ በጣም የሚያንሸራትት ነበር።​ሁለቱም እንቁራ...
14/01/2026


👉​በአንድ ወቅት፣ ሁለት እንቁራሪቶች ምግብ ፍለጋ ሲዘሉ ሳያውቁት በአንድ ግዙፍ የወተት ገንዳ ውስጥ ዘለው ገቡ። ገንዳው ጥልቅ፣ ግድግዳው ደግሞ በጣም የሚያንሸራትት ነበር።
​ሁለቱም እንቁራሪቶች ለመውጣት ደጋግመው ዘለሉ፤ ነገር ግን ግድግዳው ስለሚያንሸራትት ተመልሰው ወተቱ ውስጥ ይወድቃሉ። ለሰዓታት ሲታገሉ ቆዩ።
👉​የመጀመሪያው እንቁራሪት በጣም ደከመው። በአሉታዊ አመለካከት ተሞልቶ እንዲህ አለ፦ "ይህ ከንቱ ድካም ነው። መውጫ የለም፣ ግድግዳው ይንሸራትታል፣ ማንም ሊረዳን አይመጣም። ደክሞ መሞት ምን ያደርጋል?" አለና መዋኘቱን አቆመ። ወዲያውም በወተቱ ውስጥ ሰጥሞ ቀረ።
👉​ሁለተኛው እንቁራሪት ግን አመለካከቱ የተለየ ነበር። "አሁን ባላውቀውም አንድ መውጫ መንገድ መኖሩ አይቀርም፤ እስከ መጨረሻው እስትንፋሴ ድረስ ግን እግሮቼን አላቆምም" በማለት በሙሉ ኃይሉ መዋኘቱንና መታገሉን ቀጠለ።
👉​ለብዙ ሰዓታት እግሮቹን ሲያወዛውዝና ሲመታ ቆየ። በሚገርም ሁኔታ፣ የእንቁራሪቱ እግሮች ወተቱን ደጋግመው ሲመቱት፣ ወተቱ ተመታና ወደ "ቅቤነት" ተለወጠ። ወተቱ ወፍሮ ቅቤ ሲሆን፣ እንቁራሪቱ በቅቤው ላይ ተረግጦ መቆም ቻለ። ከዚያም በቅቤው ላይ ቆሞ በመዝለል ከገንዳው ወጥቶ ሕይወቱን አተረፈ።
​"ድካምህ ቅቤ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፤ ብቻ መዋኘቱን አታቁም!"

Listen to the inner light; It will guide you.Listen to the inner Peace;  It will feed you.Listen to the inner Love;It wi...
13/01/2026

Listen to the inner light; It will guide you.
Listen to the inner Peace; It will feed you.
Listen to the inner Love;It will transform you.

02/01/2026

#ድንቅ ልማድ

አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ ትንሽ ቆይቶ በቀላሉ የማይበጠስ ሀያል ገመድ ይሆናል።

አየህ አሪፍ ልማድን ስትጀምረው እንደ ክሩ ስስ ነው፤ ለመበጠስ ቅርብ ነው፤ ስትደጋግመው ግን አንተ ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይፈጥራል።

ሌላ ምሳሌ የትኛውም ሱስ ከትንሹ ነው የሚጀምረው ለምሳሌ የሲጋራ ሱስ ያለባቸው ሰዎች አይተህ ከሆነ ማጨስ ሲጀምሩ 1 ወይም 2 ፓኮ በማጨስ አይደለም የጀመሩት ከባኮ ውስጥ አንዷን በማውጣት ዛሬ አንዷን ነገም ይደግማል እያለ የሆነ ጊዜ ላይ በአነዴ ፓኮ ሲጨርስ ታገኘዋለህ።

ግድ የለህም ወዳጄ በጠዋት መነሳቱን፣ ማንበቡን፣ ስፖርት መስራቱን፣ ቋንቋ መለማመዱን በቃ የጀመርከውን አሪፍ ልማድ ሳትሰለች ትንሽ ደጋግመው፤ ከዛ ምን አይነት ሰው እንሚያደርግህ ታየዋለህ!

የተባረከ ቀን ተመኘን🙏

31/12/2025

"Before you judge someone about their anger. Ask them about their pain".

27/12/2025

👇
☞ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡

☞ ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡

☞ ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል።

☞ ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።
❤መልካም ቀን❤

26/12/2025

!

🚶‍♀️ስትራመድ— ደስ ይበልህ!

☀️ጸሐዩአን ስታይ— ደስ ይበልህ!

🎧መዝሙር ስትሰማ— ደስ ይበልህ!

🤸‍♀️ስትንጠራራ— ደስ ይበልህ!

🙊ከሚወዱህ ጋር ስታወራ— ደስ ይበልህ!

🧎ስትጸልይ— ደስ ይበልህ!

ይህን ማድረግ ያልቻሉ ብዙ አሉና። ተመስገን በል!

26/12/2025



✍️አንዳንድ ሰዎች ለምን እንደማይማሩ ሲጠየቁ፣ “ትምህርት ቤት መማር ብዙ ዋጋ ያስከፍላል” ይላሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ልክ ነው መማር ያስከፍላል - ገንዘብን፣ ጊዜን፣ እንቅልፍን፣ ጉልበትን . . . ያስከፍላል! ነገር ግን መማር ከሚያስከፍለው ይልቅ አለመማር ያስከፍላል፡፡ መማር አሁን ያስከፍልና ነገ ይከፍላል፤ አሁን ያደክምና ነገ ያሳርፋል፡፡ አለመማር ግን፣ “አሁን ዘና በል” በማለት ነጻ ይለቀንና እድሜ ልካችንን እያስከፈለና እየገዘገዘን ያከርመናል፡፡

✍️ከላይ የተጠቀሰው የመደበኛ ትምህርት ሂደት እውነታ መደበኛ ባልሆነው የየእለት የሕይወት ትምህርትም አንጻር ያው ነው፡፡ ለነገው ሕይወታችን ጥበብን፣ ልምድንና የሕይወት ተሞክሮ ተግባራዊ እውቀትን የምናገኝበት ብቸኛ መንገድ ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር ከምንሰራቸው ስህተቶች የተነሳ ነው፡፡ በሌላ አባባል ሲገለጽ፣ ስህተት ማለት ለነገ የሕይወት ስኬት ዛሬ የምንከፍለው የትምህርት ቤት ክፍያ ነው፡፡

✍️“በሕይወታችን ሁለት ፍላጎቶች ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ አንደኛው ሁል ጊዜ መማር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሁል ጊዜ ሳይሳሳቱ ትክክል መሆን” (Errol Gerson)፡፡ እነዚህን ሁለቱንም ነገሮች ግን በአንድ ላይ ማስኬድ አንችልም፡፡

✍️ሁል ጊዜ ትክክል መሆን ከፈለግን አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እናቆማለን፡፡ ያን ጊዜ ሕይወት ይቆማል - ትልቁና የመጨረሻው ስህተት!፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ከሞከርን መሳሳታችን አይቀርም - ታላቁና ውጤታማው ስኬት መንገድ!
ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን የመሞከርን መንገድ የመረጥን ጊዜ ሕይወት በብዙ ልምድ፣ ልምምድ፣ ጥበብና እውቀት ታሸበርቃለች፡፡

✍️ዛሬ አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር የምንከፍለው ዋጋ ለነገው ሕይወታችን ስኬታማነት የሚከፈል ስለሆነ ማለት ነው፡፡

24/12/2025

የሚያቆምህ ነገር የለም!

✍️ለፈጣሪህ የችግርህን ታላቅነት አትንገረው፤ በተቃራኒው ለችግርህ የፈጣሪን ታላቅነት ንገረው!
👍ያኔ ችግርህን ከላይ ወደታች ማየት ትጀምራለህ።

✍️የሚያስገርም ለውጥ የምትፈልግ ከሆነ አይንህ ከገጠመህ ችግር ትልቀት ላይ አንሳውና የፈጣሪን ታላቅነት አስብ፤ ከዛ አንተን መቼም እንደማይተውህ::
❤ውብ ቀን ተመኘሁላቹ❤

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Thomando posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Thomando:

Share