WIM Ethiopia

WIM Ethiopia WIM Ethiopia has a vision of striving for just Environment where all Women and Girls enjoy their Fullest right and Potentials.

በውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትብብር በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በሌ ሀዋሳ ከተማ በሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ አተኩሮ የተካሄደው የ ሴቶች እ...
03/06/2024

በውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትብብር በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በሌ ሀዋሳ ከተማ በሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ አተኩሮ የተካሄደው የ ሴቶች እና ወጣቶች የክርክር እና የውይይት መድረክ በስከት ተጠናቋል። በመድረኩ ላይ የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስምኦን ሳፓን ጨምሮ የወላይታ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ የትምህርት ጽ/ቤት ፣ እንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት፣ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኀላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የስቭክ መምህር ተገኝተው ስለ ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን በሚመለከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ የክርክር እና የውይይት መድረክ ላይ በሁለት ጎራ ተከፍለው ክርክር ያደረጉ ስምንት ተሳታፊዎች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት ደቂቃዎች ተሰጥቷቸው ባቀረቡት የክርክርና የውይይት ሀሳብ በሴቶች ላይ ይደርሱ የነበሩ ጫናዎችን በሚመለከት ሴቶች በቂ ዕድል ያለማግኘታቸው በልማትና መልካም አስተዳደር ላይ የፈጠረውን ክፍተት፣ ሴቶች ወደ ውሳኔ ሰጪነት እንዳይመጡ ያደረጋቸው የማህበረሰቡ የተሳሳተ ግንዛቤ እና በአጠቃላይ ከአባባል ጀምሮ በለተ ዕለት ሕይወት ውስጥ ስተገበሩ የቆዩ የተዛነፉ አመለካከቶች በስፋት ተነስተው በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዚህም የውይይቱና የክርክር መድረኩ ላይ የታደሙ ተሳታፍዎች ሴቶች ከዚህ ቀደም ይደርስባቸው ከነበሩ ጫናዎች ተላቀው ከወንዶች እኩል ማህበራዊ ፣ እኮኖሚያዊ እና ፖሌቲካዊ ተሳታፍነታቸው እና ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በቂጡ እንዲያውቁ እና እንዲጠቀሙበት ብሎም የውሳኔ ሰጭነት አቅማቸው እንዲያድግ የሚያግዝ መሰል መድረክ በመዘጋጀቱ ደስተኞች መሆናቸውን እና ይህንኑ መድረክ ያመቻቹ አካላትን ውመን ኢን ማይስ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አመስግነዋል።

08/03/2024

Happy International Women's Day to all the amazing women in my life! Today, let's celebrate our strength, resilience, and achievements. 🌟💪👩‍🎓👩‍⚕️👩‍🔬👩‍🏫👩‍💼👩‍🔧👩‍🚀👩‍🎨👩‍✈️👩‍🚒👩‍⚖️👩‍🦽👩‍🦯🧕👸👩‍🌾👩‍🍳👩‍🏭👩‍💻👩‍💻👩‍🎤👩‍🎤👩‍🚀👩‍🚀👩‍🚒👩‍🚒🧝‍♀️🧝‍♀️🧚‍♀️🧚‍♀️🧜‍♀️🧜‍♀️🧞‍♀️🧞‍♀️👩‍❤️‍💋‍👩👩‍❤️‍👩👩‍❤️‍👩

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተዘጋጀ  ሀገር አቀፍ  የሥነ -ዜጋና የመራጮች ትምህርት ሥልጠና መድረክ ሲሆን እጅግ በጣም የተማማርንበት እና ልምድ የተለዋወጥንበት ፍሬያማ ቆይታ ነበር። ይ...
13/02/2024

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የሥነ -ዜጋና የመራጮች ትምህርት ሥልጠና መድረክ ሲሆን እጅግ በጣም የተማማርንበት እና ልምድ የተለዋወጥንበት ፍሬያማ ቆይታ ነበር። ይበልጥ ተጠናክሮ እንደምቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።
እናመሠግናለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ለሚሰጡ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ስልጠና እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጠ::የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋና መ...
12/02/2024

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ለሚሰጡ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ስልጠና እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጠ::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል በምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚሠሩ 40 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ከ ጥር 29 እስከ ጥር 30 ቀን 2016ዓ.ም. ድረስ ለሁለት ቀናት የቆየ የስልጠና መድረክ አዘጋጀ። መድረኩ በምርጫ ቦርድ አመራር አባል ዶ/ር አበራ ደገፋ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸው የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን በቋሚነት የመስጠትን ጠቀሜታ ካብራሩ በኋላ ይህ እንዲሳካ ከቦርዱ ባልተናነሰ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ዋነኛ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል።

ስልጠናው የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት ይዘትን ባካተተውና በቦርዱ በተዘጋጀው ማስተማሪያ እና የአሰልጣኞች መምሪያ (ማኑዋል) ላይ በተመለከተው መሰረት ዴሞክራሲ እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፥ የሕዝብ ውክልና ተቋማት በኢትዮጵያ፥ የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥት እና የመንግሥት አወቃቀር፥ ስልጣን እና ተግባር፥ መንግሥት እና የፖለቲካ ሥርዓት በኢትዮጵያ፥ ምርጫ-የምርጫ ሕግጋት እና የምርጫ ሒደቶች በኢትዮጵያ፥ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የዜጎች መብቶች እና ኃላፊነቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የሲቪል ማህረሰብ ተቋማቱ ትምህርት ከመስጠታቸው በፊት እንዴት የፍላጎት ምዘና (የዳሰሳ ጥናት) ማድረግ እንዳለባቸው፥ ለየትኛው የማህበረሰብ ክፍል በምን መልኩ መልዕክት መተላለፍ እንዳለበት፥ እንዲሁም የባለ ድርሻ ኣካላት አመራረጥን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጥቷል።

የስነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርትን ለማሳካት የበጎ አድራጎት/የፈቃደኝነት ሥራ ያለው ሚና በቦርዱ የስነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት የሥራ ክፍል የተብራራ ሲሆን ተሳታፊዎች በቀጣይ በአካባቢያቸው የሚገኙትን ወጣቶችን እንዴት በበጎ ፈቃደኝነት ማሳተፍ እንደሚችሉ እና ወደፊትም በምርጫ ሂደቱ በተለያየ ደረጃ የሚያገለግሉ ወጣቶችን በምን መልኩ ማብቃት እንደሚቻል አጠር ያለ ማብራሪያ እና የሌሎች አገራት ልምድ በተመለከተ በስልጠናው ወቅት ቀርቧል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ቦርዱ በተናጠል እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በጋራ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት እና ለወደፊት የታቀዱ ሥራዎችን እንዲሁም የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን የሚሰጡ አካላት ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶችን በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል።

በስልጠናው ወቅት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ግንዛቤ ለማስፋት የቦርዱ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ከስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል። በዚህ መሰረት፡ የቦርዱ የሕግ ሥራ ክፍል በምርጫ ሕጉ ማዕቀፍ እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊነት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳዮች ሥራ ክፍል በኩል ደግሞ ፓርቲዎች በመራጮች ትምህርት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በተመለከተ እንዲሁም በፖለቲካ ፓርቲዎች በተፈረመው ሰነድ እና በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የሚከናወን መሆኑን እና ለዚህም የሚውል ለፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግስት የሚሰጥ በጀት መኖሩን አስረድተዋል። ለወደፊቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በቅርበት በመስራት የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት ያለምንም መድሎ በገለልተኝነት ለህብረተሰቡ የሚሰጥበትን ዘዴ መተለም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የስርዓተ ጾታና አካታችነት ትምህርት ሥራ ክፍል በበኩሉ የሲቪል ማህበራቱ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊስተናገዱ የሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ማለትም ሴቶችን፥ የአካል ጉዳተኞችን፥ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በምን መልኩ በስነ-ዜጋ እና መራጮች ትምህርት አሰጣጥ ውስጥ ማካተት እንዳለባቸው አብራርተዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮችም ከስርዓተ ጾታና አካታችነት ትምህርት ሥራ ክፍል የቀረበውን ማብራሪያ እንደ መነሻ በመውሰድ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የሰው ሀይል፣ የቁሳቁስ፣ የማስተማሪያ ዘዴዎችና እና ሌሎች ግብአቶችን ምንነትና እና የግብአቶቹን አቅርቦት በተመለከተ ውይይት እና የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

በቦርዱ የኮሙኒኬሽን ሥራ ክፍል ደግሞ መሰረታዊ የተግባቦት ክህሎቶችን በሚገባ መረዳት የስነ-ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ከማስተላለፋችን በፊት ማዳበር የሚገባን ጉዳይ መሆኑን ካስረዱ በኋላ ይህንም ማሳካት የሚቻለው መልዕክቱን ለማሰተላለፍ የተመረጠውን ማህበረሰብ ከመረዳት እንደሚጀምር ገለጻ አድርገዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዝሃነት በሚንጸባረቅበት ማህበረሰብ ውስጥ የተለያዩ የተግባቦት ዘዴዎችን በመጠቀም የሚተላለፈው መልዕክት የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ለተሳታፊዎቹ የግንዘቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡ በቦርዱ የስልጠና ሥራ ክፍልም ስልጠና የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን ለማስረፅ ያለውን አስተዋጽዖ በተመለከተ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

በሌላ መልኩም በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ከኢትዯጵያ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጥምረት በኩል በሰብአዊ መብትና የምርጫ ተያያዥነት እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት ኃላፊነትን አስመልክቶ አጠር ያለ ገለጻ አድርገዋል።ይህም ማብራሪያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ምን እንደሆነና እንዴት እንደሚወጡት ጭምር ከዳሰሳ ጥናትና ከልምድ የተገኘ ተሞክሮን አጋርቷል፡፡

ከተሳታፊዎች ጋር በተደረገው ዉይይትም የስልጠናው ተሳታፊዎቹ በስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት በቂ ግንዛቤ የጨበጡ መሆናቸው የተስተዋለ ሲሆን በስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት አሰጣጥ ዙሪያ ትምህርቱ ለማን ተደራሽ መሆን እንዳለበትና እንዴት ሳይንሳዊ፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ ዘዴ መሰጠት እንዳለበት በቂ ክህሎት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት አሰጣጡ ዙሪያ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን እና ዋና ዋና ተግዳሮቶችን በማንሳት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በሌላም በኩል የመራጮች ትምህርት ማስተማሪያ ማንዋል ላይ መሻሻል አለባቸው ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል። የቦርዱ ሊቀመንበር ክብርት ወ/ሮ ሜላትወርቅ ለተዘጋጀው መድረክ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን ካመሰገኑ በኋላ የስነ-ዜጋና መራጮች ትምህርትን በዘላቂነት መስጠት ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ለዚህም ስኬት የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ዋነኛ ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አፅንዖት በመስጠት የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል። በመጨረሻም የቦርዱን መስፈርት ያሟሉ 40 የሲቪል ማህበራት ከክብርት ሊቀ መንበሯ የፍቃድ ምስክር ወረቀት ተቀብለው መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

We’re pleased to announce to our esteemed partners that women in MICE Ethiopia has received a certificate of accreditati...
09/02/2024

We’re pleased to announce to our esteemed partners that women in MICE Ethiopia has received a certificate of accreditation from the National Election Board of Ethiopia to provide voters education.
# Women in MICE Ethiopia # Women participation

19/01/2024

Women in MICE Ethiopia (WIM Ethiopia) is board led, non – profit making, non – religious, non-political and non – governmental women’s organization with special interest in empowerment of girls and women to contribute in transforming the society in positively and impacting a positive change. WIM Ethiopia is mainly involved in empowering Ethiopian women and girls, aiming for their personal, career, and economic success through empowerment and by mobilizing women’s participation in securing occupation, promotion of their products and services to the public, through training and skills development activities through coaching and mentorship.

WIM Ethiopia is officially registered Civic Organization and accorded legal personality with registration number 6362 from Federal Democratic Republic of Ethiopia Authority for Civil Society Organizations.

WIM Ethiopia has a vision of striving for just Environment where all Women and Girls enjoy their Fullest right and Potentials. With an inarching mission of promoting women and girls empowerment at all levels to develop their natural abilities to their fullest potential; equip women and girls with skills and knowledge to excel as leaders of their workplaces and communities in spheres of the economic, social, political and legal empowerment; and strengthen synergy among different human & women rights advocating organizations towards gender Equality and an enhanced level of engagement of women in Ethiopia.

17/07/2023

Welcome to my new page

Address

Africa Avenue
Addis Ababa
4462

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WIM Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share