Nasir Yasin Foundation - NYF

Nasir Yasin Foundation - NYF መልካምነትዎን ያጋሩ! Share your kindness!

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽንናስር ያሲን ፋውንዴሽን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አራት ወረዳዎች ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ለረመዳን ማፍጠሪያ የሚሆኑ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።...
19/03/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አራት ወረዳዎች ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ለረመዳን ማፍጠሪያ የሚሆኑ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ለዚህም የምስጋናና የምስክር ወረቀት የሁሉንም ወረዳዎች በመወከል ከወረዳ 01 አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ግዛቸው ሶበቃ ተቀብለናል። በቀጣይ በትብብር በምንሰራባቸው ጉዳዮች ውይይት አድርገናል። ናስር ያሲን ፋውንዴሽን ለተሰጠው እውቅና ምስጋናውን ያቀርባል።

ፋውንዴሽኑ በረመዳን ወር በተለያዩ አካባቢዎች ሲያቀርባቸው ለነበሩ ድጋፎች በገንዘብ፣ በእውቀት እንዲሁም በጊዜያችሁ ስትደግፉና ስታበረቱን ለነበራችሁ አባላትና ደጋፊዎቻችን በሙሉ ታላቅ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ያቀርባል።

አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን እያልን መልካም የኢድ አል-ፈጥር በዓል እንዲሆንላችሁ በፋውንዴሽናችን ስም እንመኛለን!

ኢድ ሙባረክ!

🔶 Donate @
💰 Commercial Bank of Ethiopia
1000449031907
💰 Awash Bank
01308690216200
💰Bank of Abyssinia
89068924

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:
page:
https://www.facebook.com/NYF2022
Email: [email protected]
📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በዘንድሮ የረመዳን ወር ከፋውንዴሽኑ አባላትና ደጋፊዎች የተሰበሰበ የዘካ ገንዘብ በቡራዩ ከተማ ወረዳ 01 በጠሬ መንደር ለሚገኙ ተፈናቃይ ...
18/03/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በዘንድሮ የረመዳን ወር ከፋውንዴሽኑ አባላትና ደጋፊዎች የተሰበሰበ የዘካ ገንዘብ በቡራዩ ከተማ ወረዳ 01 በጠሬ መንደር ለሚገኙ ተፈናቃይ ቤተሰቦች በዛሬው እለት አከፋፍሏል።

በመንደሩ ከ40 በላይ ተፈናቃይ ቤተሰቦች የተለያየ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ፋውንዴሽኑ እነዚህ ልዩ ድጋፍና እገዛን የሚሹ ቤተሰቦችን በመዘየር በድርጅቱ በኩል የተሰበሰበ የዘካ ገንዘብ አከፋፍሏል።

🔶 Donate @
💰 Commercial Bank of Ethiopia
1000449031907
💰 Awash Bank
01308690216200
💰Bank of Abyssinia
89068924

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:
page:
https://www.facebook.com/NYF2022
Email: [email protected]

📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽንየካቲት 2018✅ የረመዳን ኢፍጣር ሰደቃ ፕሮግራም በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ተጠቃሚ  ቤተሰቦችጋ ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም።🔶 Donate @  💰 Commer...
09/03/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን

የካቲት 2018

✅ የረመዳን ኢፍጣር ሰደቃ ፕሮግራም በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ተጠቃሚ ቤተሰቦችጋ ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም።

🔶 Donate @
💰 Commercial Bank of Ethiopia
1000449031907
💰 Awash Bank
01308690216200
💰Bank of Abyssinia
89068924

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:
page:
https://www.facebook.com/NYF2022
Email: [email protected]
📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን! የካቲት 2018 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን 1447ተኛ የረመዳን ፆም አስመልክቶ ከግማሽ ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ልዩ ልዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በአዳ...
05/03/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!

የካቲት 2018

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን 1447ተኛ የረመዳን ፆም አስመልክቶ ከግማሽ ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ልዩ ልዩ የምግብ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በአዳማ ከተማ አደረገ።

ፋውንዴሽኑ ድጋፉን በአዳማ ከተማ ቁባ መስጅድ አካባቢ ለሚገኙ 150 የአቅም ውስንነት ላለባቸው ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት አከፋፍሏል።

ፋውንዴሽኑ ባለፈው ሳምንት ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተመሳሳይ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ ማድረጉ ይታወሳል።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን የድጋፍ ስርጭቱን ለመሩና ላስተባበሩ የአዳማ ቁባ መስጅድ ኮሚቴዎች እንዲሁም ሰደቃቸውን በፋውንዴሽኑ በኩል ለለገሱ አባላትና ደጋፊዎች ታላቅ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ያቀርባል!

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:

📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

24/02/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ወገኖች የረመዳንን ፆም አስመልክቶ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ባደረገበት ዕለት ክቡር አቶ ሳኒ ረዲ ያስተላለፉት መልዕክት።

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:

📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን! ናስር ያሲን ፋውንዴሽን ለረመዳን ኢፍጣር የሚሆን የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።ናስር ያሲን ፋውንዴሽን 1447ተኛ የረመዳን ፆም አስመልክቶ ከአንድ ሚልየን ብር በ...
23/02/2026

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን ለረመዳን ኢፍጣር የሚሆን የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን 1447ተኛ የረመዳን ፆም አስመልክቶ ከአንድ ሚልየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ቤተሰቦች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ፋውንዴሽኑ ከምስረታው ጀምሮ ለረመዳን ማፍጠሪያ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ዘንድሮ ለስድስተኛ ዙር ሲሆን ድጋፉንም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖች በልዩ ሁኔታ ተደራሽ አድርጓል።

ድጋፉን ክቡር አቶ ሳኒ ረዲ እንዲሁም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የፋውንዴሽን የቦርድ አመራሮች በተገኙበት አስረክቧል።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን የድጋፍ ስርጭቱን ለመሩና ላስተባበሩ የወረዳ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሰደቃቸውን በፋውንዴሽኑ በኩል ለለገሱ አባሎችና ደጋፊዎች ታላቅ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ያቀርባል!

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:

📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

የሀዘን መግለጫየቀድሞው የስልጤ ዞን አስተዳዳሪና በአሁኑ ሰዓት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አሊ ከድር በዛሬው እለት ማለትም ሚያዚያ 20/2017 ኦሮሚያ ክልል...
28/04/2025

የሀዘን መግለጫ

የቀድሞው የስልጤ ዞን አስተዳዳሪና በአሁኑ ሰዓት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አሊ ከድር በዛሬው እለት ማለትም ሚያዚያ 20/2017 ኦሮሚያ ክልል ሞጆ የፍጥነት መንገድ ላይ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።

የናስር ያሲን ፋውንዴሽን ቤተሰብና አባላት በመሪያችንና በወንድማችን ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለወንድማችን ጀነት ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!የካቲት 29/ 2017ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የረመዳንን ፆም አስመልክቶ ከአንድ ሚልየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአቅም...
09/03/2025

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!

የካቲት 29/ 2017

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የረመዳንን ፆም አስመልክቶ ከአንድ ሚልየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአቅም ውስንነት ላለባቸው 250 ቤተሰቦች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ፋውንዴሽኑ ከምስረታው ጀምሮ ለረመዳን አስቤዛ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ዘንድሮ ለሶስተኛ ዙር ነው።

ፋውንዴሽኑ ቋሚ አባሎችና ደጋፊዎችን በማስተባበር ባሰባሰበው ገንዘብ ምግብ ነክ አስቤዛዎችን እንደ ዱቄት፣ ሩዝ፣ የገብስ ቂንጬ፣ ዘይትና ስኳር በመግዛት ለ250 ቤተሰብ አከፋፍሏል።

በዚህም ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ወገኖች በልዩ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል።

ፋውንዴሽኑ በተመሳሳይ በዕለቱ ለቂልጦ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ለህፃናት ተኝቶ መታከሚያ ክፍል የሚውሉ 10 አልጋዎች ከሙሉ ፍራሽ፣ ትራስ፣ ብርድልብስና አንሶላ አጠቃላይ ግምታቸው 350,000 ብር የሚሆኑ መገልገያዎችን አበርክቷል !

ድጋፋን የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ ፣ የስልጤ ዞን አፈጉባኤ ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ሀላፊ አቶ ሀይረዲን ሀቢብ እና ሌሎች የዞንና የወረዳ ሀላፊዎች እንዲሁም የፋውንዴሽኑ የቦርድ አመራርና አባላት በተገኙበት አስረክቧል።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን የድጋፍ ስርጭቱን ለመሩና ላስተባበሩ የመንግስት ኃላፊዎች እንዲሁም ሰደቃቸውን በፋውንዴሽኑ በኩል ለለገሱ አባሎችና ደጋፊዎች ታላቅ ምስጋና ከአክብሮት ጋር ያቀርባል!

🔶 ናስር ያሲን ፋውንዴሽን!
🔸 መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:

📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽንናስር ያሲን ፋውንዴሽን በስልጤ ዞን በጎርፍ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!በስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ  ከቤ...
11/10/2024

✅ ናስር ያሲን ፋውንዴሽን

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን በስልጤ ዞን በጎርፍ ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!

በስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ በቀረበው ጥሪ መሠረት ፋውንዴሽናችን የበቆሎ ዱቄትና የመኝታ ፍራሽ ድጋፍ አድርጓል።

ፋውንዴሽናችን ለተጎጂ ወገኖቻችን ያደረገው የዓይነት ድጋፍ ዋጋ ግምት ከ300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በላይ የሚገመት ነው።

ፋውንዴሽናችን የቁሳቁስ ድጋፋን ዞኑን ወክለው የተገኙት የስልጤ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር አለሙ እንዲሁም የሁለቱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በዞኑ የቀይ መስቀል ኃላፉ በአቶ ሙሀባ ሁሴን አማካኝነት ርክክቡን ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ በቋሚነት ለሚደረግ ድጋፍ ፋውንዴሽናችን የበኩልን አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ናስር ያሲን ፋውንዴሽን
መልካምነትዎን ያጋሩ!

Telegram:
Email: [email protected]
📱+251-9-01593359
📱+251-9-01598859

Address

Addis Ababa

Opening Hours

08:00 - 00:00

Telephone

+251901593359

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nasir Yasin Foundation - NYF posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Nasir Yasin Foundation - NYF:

Share