Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር

Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ  ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር, Charitable organisation, Entoto Street, Near to Qusquam Mariam Church, Addis Ababa.

የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር
የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር በቁስቋም ሰፈር እና አካባቢው በተወለዱ እና/ወይም ያደጉ በጎ አሳቢ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ማህበር ሲሆን አላማውንም በቁስቋም ሰፈር እና አካባቢው የሚኖሩ ደጋፊና ረጂ የሌላቸው አቅመ ደካማዎችን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን፣ አካል ጉዳተኛ ወገኖችን፣ ወንዶችን እንዲሁም ስራ አጥ ወጣቶችን ያለ ማናቸውም የዘር፣ የቀለም፣ የሀይማኖትና የፆታ ልዩነት በእኩል አይን መርዳትና ማገዝ አድርጎ የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡

የማህበሩ ዓላማዎች
የማህበሩ ዋነኛ ዓላማ በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የሚኖሩ ጧሪ አጋዥ የሌላቸው አቅመ ደካማ አረጋውያንና አዛውንቶችን ደጋፊ የሌላ

ቸው ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኖች እንዲሁም ስራ አጥ ወጣቶችን ለመደገፍና በሂደትም በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሰረተ ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎችም፡-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚኖሩ በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የተወለዱ ወይም ያደጉ እንዲሁም አላማውን የሚደግፉ ሰዎችን በማስተባበር በአቅም ማነስ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ህፃናትና ሴቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ፣
2. ወጣቶች ስራ እንዲፈጥሩ፤ እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲወገዱ ግንዛቤ መፍጠር
3. በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የሚገኙ አቅመ ደካማና ረዳት የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን (ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወንዶች፣ ወጣቶች) በጊዜያዊነት ወይም በዘላቂነት ለመርዳት እንዲሁም ለማቋቋም
4. በኤች አይ ቪ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናትን በመደገፍ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ማድረግ
ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን አላማዎች በማስፈፀም በአካባቢያችን ብሎም በክተማችን ለሚኖሩና ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት፤
5. በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የህፃናትና እናቶች ጤና አጠባበቅ፣ የቤተሰብ ምጣኔና የቅድመ በሽታ መከላከል ስራዎች መስራት፣
6. በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢ ት/ት ያቋረጡ ልጆችን መርዳት፣ እንዲሁም በየዩኒቨርሲቲዎች ላሉ ድጋፍ ለሚሹ የአካባቢው ተወላጆች የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ማድረግ፣
7. በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የሚገኙ ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ የአቅም ግንባታ ስራዎች መስራት፣
8. በእንጦጦ ቁስቋም እና አካባቢው የሚገኙ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችን የሃገር ውስጥና የውጪ የት/ት ዕድል እንዲያገኙ ማመቻቸትና ችግር ለገጠማቸው ድጋፍ ማድረግ፣

08/01/2026

ማህበራችን የጌታችንና መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በእንጦጦ አካባቢ ነዋሪ ለሆኑ 60 ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው የ3000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል:: በዚህ በጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሳተፋችሁን የማህበራችን አባላት በተረጂ ቤተሰቦች ስም እናመሰግናለን፡፡

የሄርናን ሳንድዊች --------በኮሎምቢያ በሜደልሊን ማንሪኬ በሚባል ሰፈር ሁልጊዜ ማታ ልክ 3 ሰዓት ላይ  በፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀለሉ ሳንድዊቾች ዛፍ ላይ ይቀመጣሉ።ሳንድዊቹን ማን እንደ...
02/01/2026

የሄርናን ሳንድዊች
--------
በኮሎምቢያ በሜደልሊን ማንሪኬ በሚባል ሰፈር ሁልጊዜ ማታ ልክ 3 ሰዓት ላይ በፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀለሉ ሳንድዊቾች ዛፍ ላይ ይቀመጣሉ።

ሳንድዊቹን ማን እንደሚያስቀምጥ ወይም እንደሚተዋቸው ማንም አያውቅም ።

በአካባቢው ያሉ በጎዳና ላይ የሚኖሩ ምንዱባን ሳንድዊቾቹን በጉጉት ይጠብቃሉ። 3፡15 ላይ ምንም ሳይቀር ተወስደው ያልቃሉ።

ለስድስት ተከታታይ ዓመታት ለአንዲት ቀን እንኳን ሳንድዊቾቹ በዛፉ ላይ መቀመጣቸው ቀርተው አያውቁም ።

ከስድስት አመት በኋላ አንድ ቀን በድንገት ሳንድዊቾቹ በዛፉ ላይ መቀመጥ አቆሙ።

"ሳንድዊች ሰው ምን ሆነ?" ብለው ድሃዎቹ የጎዳና ሰዎች ጠየቁ።

የሳንድዊቹ ሰውን በጎዳና የሚኖሩ ሰዎች በፍለጋ ማን እንደሆነ አወቁት ።
--------------
ሄርናን ይባላል።

አዛውንቱ ሄርናን ዕድሜው 19 ዓመት የነበረ ልጁን አጥቷል፤ ልጁ ከሱስ ጋር በጎዳና ላይ ነበር የሚኖረው ። ሄርናን ልጁን ለብዙ ዓመታት ፈልጎት ነበር። ነገር ግን ሊያገኘውና ሊያድነው አልቻለም። በመጨረሻም እንደሞተ ሰማ ፣በጣምም አዘነ!

ሄርናን "ልጄን አንድ ሰው ምግብ ቢሰጠው ኖሮ… ምናልባት ዛሬም በሕይወት ይኖር ነበር"።ይላል። በዚህ ምክንያት ልጁን በቀበረ ማግስት ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ሳንድዊች ማታ ማታ በዛፍ ላይ ማስቀመጥ ጀመረ።

ችግረኞቹን ካወቃቸው ለማን እንደሚሰጥ እመርጣለሁ በማለት ሳንድዊቹን ተደብቆ ነበር በዛፍ ላይ የሚያስቀምጠው።

በግንበኛ ሙያ የሚተዳደረው ሄርናን ለስድስት ዓመታት 17,520 ሳንድዊቾችን እራሱ አዘጋጅቶ በዛፉ ላይ አስቀምጦ ነበር። ሄርናን በድንገት ከሞተ በኋላ ሳንድዊቾቹ ከዛፉ ላይ ሲጠፉ "የሳንድዊች ሰው ምን ሆነ?" ተባለ።

ሄርናን ከሞተ ከአመታት በኋላ በዚያ አካባቢ በጎዳና ላይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ አንዲህ ብለው ነበር :-

"እነዚያን ሳንድዊቾች ለአራት ዓመታት በልቼ ነበር ህይወቴን አዳኑኝ!"

"አንዳንድ ቀናት የምበላው የእሱን አንድ ሳንድዊች ብቻ ነበር።"

"ዛሬ ቤት እና ስራ አለኝ ፣ ትዳር እና ልጆች አሉኝ ። እነዚያ ሳንድዊቾች ባይኖሩ ይህ አይሆንም ነበር!"

"እነዚያ ጣፋጭ ሳንድዊቾች በህይወት አቆዩኝ.......።"
-----------
©️አዳነ ካሳሁን

ውድ የማህበራችን አባላት ሆይ: ዛሬ በምታዋጡት መዋጮ እናንተ በቅርበት የማታውቋቸው በርካታ ታዳጊዎች ይደገፋሉ። በስውር የምትሰጡትንም እግዚአብሔር ያያል: በግልፅም ይከፍላችኋል። በጤና ቆይታችሁ የድሆች አምባ/ተስፋ ለመሆን ያብቃችሁ🙏🏽መልካም የልደት በአል 🙏🏽

30/12/2025

Entoto Qusquam Charity Association extends warm wishes to all its supporters and beneficiaries for a happy 2026.

😭 የሐዘን መግለጫ😭በደቡብ አፍሪካ ለረዥም ዓመታት የኖረው ወንድማችን እና የማህበራችን አባል አቶ ዘውዱ ደበበ ባደረበት ሕመም ምክንያት በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ሲከታተል ...
15/12/2025

😭 የሐዘን መግለጫ😭

በደቡብ አፍሪካ ለረዥም ዓመታት የኖረው ወንድማችን እና የማህበራችን አባል አቶ ዘውዱ ደበበ ባደረበት ሕመም ምክንያት በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ሲከታተል ቆይቶ በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በፀበል እንዲሁም በህክምና ተቋማት ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በመጨረሻም በ05-04-2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል። አቶ ዘውዱ ደበበ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነበረ።

የአቶ ዘውዱ አበበ የቀብር ስነ ስርዐት በዛሬው ቀን (ታህሳስ 06 - 2018 ዓ/ም) በእንጦጦ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 8:30 ላይ ይፈፀሚል።

ማህበራችን ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹ እና ጓደኞቹ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥልን ይመኛል ።

እግዚአብሔር አምላክ ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋር በቀኙ ያሳርፍልን🙏 ነፍስ ይማር።

Address

Entoto Street, Near To Qusquam Mariam Church
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Entoto Qusquam Charity Association የእንጦጦ ቁስቋም በጎ አድራጎት ማህበር:

Share