Besiraw Mesele

Call Directions Website Contact the organization

Besiraw Mesele ሀገርህን ውደድ፣ምንም ደኻ ብትሆንም በኢትዮጵያ አትጨክን

08/08/2026
22/02/2026
22/02/2026

"ሰብአዊነትና አንድነት፦ ከድል አደባባይ ወደ ምግብ ሉዓላዊነት!" 🇪🇹

መልካም እሁድ ለሁላችሁም!

እኛ ኢትዮጵያውያን ለዓለም የታየ የጥቁር ሕዝቦች ኩራትና የድል ተምሳሌቶች ነን። ይህ ድል ደግሞ በባዶ ሜዳ የመጣ ሳይሆን በታላቅ "ሰብአዊነት"፣ በመደጋገፍና በአንድነት የተገነባ ነው። አባቶቻችንና እናቶቻችን በአድዋ ተራራዎች ላይ ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በአንድ ልብ ስለቆሙ የማይበገረውን የጠላት ኃይል ድል አድርገው ለነፃነት አብቅተውናል።

ዛሬም ያው የአድዋ መንፈስ፣ ያው የመተባበርና የመረዳዳት ባህላችን ከፊታችን ለተደቀነው የድህነትና የተረጅነት ፈተና ዋነኛው መፍትሔ ነው።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ትልቁ ዓላማ አደጋን መከላከል ብቻ አይደለም፤ የዜጎቻችንን ሕይወት በዘላቂነት መታደግ ጭምር እንጂ! ሰብአዊነት ማለት ወገናችን ሲራብ ማየት ሳይሆን፣ በጋራ በመቆም የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ እና የምግብ ሉዓላዊነታችንን በተግባር ማሳየት ነው።

ካሰብንበትና ከተባበርን የማንወጣው አቀበት የለም!

በትጋት ከሰራን ከተረጅነት እንላቀቃለን!

በራስ አቅም መቆም የሰብአዊነት ሁሉ መጀመሪያ ነው!

አንድ ሆነን አድዋ ላይ እንዳሸነፍን፣ ዛሬም በልማትና በምግብ ራሳችንን ችለን እናሸንፋለን!

ይህ እሁድ የወገን ፍቅር የሚታይበት፣ ሰብአዊነት የሚጎላበትና ለሀገራችን ብልጽግና ዳግም ቃል የምንገባበት ይሁንልን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Besiraw Mesele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Besiraw Mesele:

Shortcuts

Share