18/08/2026
🌱 5Day — የነገን ትውልድ ዛሬ መገንባት
አንድን ልጅ ማስተማር አንድን ሰው ማዳን ብቻ አይደለም፤ የሚመጣውን ትውልድ መንካት ነው። 🌱
https://t.me/cefethiopia
ይህን እውነት በተግባር እየኖረ ያለው 5Day ፕሮግራም በርካታ ልጆችን በወንጌል እያገኘ የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረና ልጆችን በእምነት እያጠናከረ ይገኛል። 🙏📖
5Day ወንጌልን ለልጆች በማድረስ ብቻ አይቆምም ብዙ ልጆችን በወንጌል እያስታጠቀ የነገ ትውልድ የሚሆኑ ልጆችን ዛሬ እያዘጋጀ ይገኛል። 🌍🔥
https://t.me/cefethiopia
ዛሬ በልጆች ላይ የምንዘራው የወንጌል ዘር ነገ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በትውልድ ውስጥ ፍሬ ያፈራል።በቀጣይም (Children-riche-Children Program) CRC ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ ማድረግ ትልቁ ተግባራችን ነው (ለዚህም የሚያስፈልጉ መፅሐፍትና ማቴሪያሎች በቂ ዝግጅት ተደርጎባቸዋል) 📚
እነዚህን ወሳኝ #ተግባራት በቀጣይም ከቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በጋራ እንተጋለን። 🔍 https://t.me/cefethiopia
በተቀደሰው አገልግሎታችን ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን!
Telegram | https://t.me/cefethiopia
💯 💯 💯
Child Evangelism Fellowship
እያንዳንዱን ልጆች | በእያንዳንዱ ቀን | በሁሉም ቦታ