ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር Mizan Peace And Development Association

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር Mizan Peace And Development Association

ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር Mizan Peace And Development Association Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር Mizan Peace And Development Association, Non-Governmental Organization (NGO), Addis Ababa.

ሰ ላ ም : ጤ ና : ይ ስ ጥ ል ን
ስለ ሚዛን ማህበር ጥቂት እንበላችሁ…
……………………………………………………
� ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር ለማህበረሰባቸው
አዎንታዊ አስተዋፅኦ ለማበርከት ዓላማ በሰነቁ ጥቂት ወጣቶች
አነሳሽነት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ከኢፌዲሪ ሲቪል
ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ፍቃድ አግኝቶ ጥቅምት 2012
የተመሰረተ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት
ሲሆን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት የሚሰራ በጎ
አድራጎት ማህበር ነው፡፡

� ከማህበሩ ዓላማዎች መካከል…
•••••••••••••
※ ሀገራዊ አንድነትና ሰላም የሃገሪቷን ሰላም፣ የህዝቦቿን አብሮነትና
መከባበር በሚያሳድጉ

ና የሃገር ፍቅርን በሚያጎለብቱ እንዲሁም
ግጭትና አለመግባባቶችን በሚፈቱ ሃገር በቀል እሴቶችና ታሪኮች
ዙሪያ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ ፣ የምክክር መድረኮችን
ማዘጋጀት፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዲንሸራሸሩ ማድረግ።

※ አካባቢ ጥበቃ
ህብረተሰቡን ያሳተፈ የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ስራዎችን
በማከናወን ስለአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በመፍጠር የሃገሪቱን
የአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረገውን
ትግል መደገፍ።

※ ወላጅ አልባ ህጻናት
ለጊዚያዊ ችግሮች ማስተንፈሻ ድጋፍ ከመፈለግ በተጨማሪ
ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ድጋፎች ማፈላለግ
በተጨማሪ የተለያዩ በዓላትን በጋራ በማሳለፍና በመሳሰሉት
ተግባራት ከችግረኛ ቤተሰቦችና ወላጅ አጥ ህፃናት ጎን በመሆን
የአብሮነት መንፈስን ማጎልበት።

※ ሀገር በቀል
በሃገር በቀል እውቀቶች ለማስጠበቅና ለመቆየት የሚረዱ፣
ስነ ጥበባዊ ዘርፎች፣ ታሪኮች፣ ባህሎች፣ እምነቶችና እሴቶች
ዙርያ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድና ማበረታታት እንዲሁም
ምክረ ሃሳቦችን ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማቅረብ።

※ የህጻናት፣ ሴቶችና ወጣቶች
የህፃናት፣የሴቶች፣ የወጣቶችና በአጠቃላይ የዜጎች
ሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ መታገል።

※ ማህበረሰባዊ ዲጂታላይዜሽን
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በማስተዋወቅና ተግባራዊ
በማድረግ ፤እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት
የአርሶ አደሩንና የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት እና የቴክኖሎጂ
አጠቃቀምን ማሳደግ።

※ ት/ት እና ጤና ተቋማት
የትምህርትና ጤና ተቋማትን መገንባት፣ አቅም ማጎልበትና
የጤናና ት/ት አገልግሎቶችን መስጠት።

※ ወጣት አመራር
የወጣቶችና ሴቶችን ማህበረዊ፤ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
ተሳትፎ እንዲሁም የአመራር አቅም የሚያጎለብቱ የአቅም
ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት።

� ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ ምን ምን
ስራዎችን አከናውኗል ?
••••••••••
� የተለያዩ መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪያዎች አዘጋጅቷል።
የማህበሩን የሰው ኃይል ቁጥር አደራጅቷል የማህበሩ ቋሚና
ደጋፊ አባለት የማፍራት ስራ ሰርቷል።

� የማህበሩ ቢሮዎችን በሰው ኃይልና በቁሳቁስ እንዲሁም
በቴክኖሎጂ የማደራጀት ስራ ሰርቷል ለማህበሩ ስራ ለማሳካት
የተለያየ ፈንድ የማፈላለግ ስራ ሰርቷል።

� ማህበሩን ለማስተዋወቅ የሚረዱ የተለያዩ መድረኮች
የማዘጋጀትና የዌቭ ሳይት የማጎልበት ስራ ሰርቷል።

� የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ጥራትና ሽፋን ለማሻሻል
ከሙስሊም ዩኤስ ኤድ ጋር በመተባበር በጉራጌ ዞን ከ6 ሚልየን
ብር በላይ በሆነ ወጪ መማሪያ ክፍሎችን በመስገንባት የመማሪያ
ቁሳቁሶችን አሟልቶ አገልግሎት እንዲሰጡ አስችሏል።

� ከ6 ዙር በላይ በተለያዩ አርዕስቶች በታዋቂ ምሀራን በተለያዩ
አርዕስቶች ስልጠናዎች ለወጣቶች፤ ለመንግስት ሰራተኞች፤
ለነጋዴዎች ለስራ እድል ፈላጊዎች ለ182 አከባቢ ሰልጣኞች
ስልጠና የመስጠት ስራ ሰርቷል።

� በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ
ምክንያቶች ችግር ለደረሰባው የማህበረሰቡ አካለት የተለያየ
ድጋፎችን ተደራሽ አድርጓል።

� በባሰ ችግር ውስጥ ለሚገኑ ቤተሰብ ለሚገኙ ለ100 የአጸደ
ህጻናት ተማሪዎች የቁርስና ማሳ ከአንድ ሚልየን ብር በላይ ወጪ
በመሸፈን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።

� በጉራጌ ዞን አንድ የጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ የጥናት ስራ
አሰርቶ ከ3.5 ሚልየን ብር ወጪ የቁፋሮ ስራ አስጀምሯል።

� ለ15 ስራ ፈላጊ ወጣቶች ለቋሚ የስራ እድል ተጠቃሚ
እንዲሆኑ ለማስቻል በወልቂጤ ከተማ በህዝብ-1 እና ታክሲ-1
የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲወስዱ ከሰማኒያ ሺብር በላይ
ወጪ አድርጎ ለስልጠና አስመዝግቧል።

� የማህበሩ ቀጣይ እቅዶች ?
•የተለያዩ የትምህርት፤ የጤና ፤የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት
ማስፋፊያ ግንባታዎችን ማከናወን።

፠ የግሪን ኤሪያ ማልሚያ ቦታዎችን ከሚመለከተው የመንግስት
አካል በመረከብ የአረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን መደገፍ።

፠ የከተማ ጽዳትና ውበት የሚከናወኑ ተግባሮች በባለቤትነት
ማከናወንና መደገፍ ለአቅመ ደካሞች ፤ለአረጋዊያን ፤ወላጆቻቸውን
ላጡ ህጻናት የተለያዩ ድጋፎችን መድረግና መደገፍ።

፠ ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ የማጣቀሻ መጽሃፎች
ድጋፍ ማፈላለግና መደገፍ።

� የማህበሩ መገኛ የት ነው ?
• በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ
• ንብ ባንክ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109, ወልቂጤ, ኢትዮጵያ
� ስልክ +251 11 884 7157
�ኢሜይል… [email protected]
� official website : www.Mizan.org.et
________________________
“ ለማህበራዊ ለውጥ እንተጋለን ”
ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚዛን የሰላምና ልማት ማህበር Mizan Peace And Development Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share