Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ

Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ Plogging-Ethiopia advocates and promotes picking up plastic litter while jogging/ walking.

Big thanks to Getahun Seifufor all your support! Congrats for being a top fan on a streak 🔥!
14/03/2026

Big thanks to Getahun Seifu

for all your support! Congrats for being a top fan on a streak 🔥!

03/02/2026
𝐄𝐧𝐭𝐨𝐭𝐨 𝐏𝐚𝐫𝐤, 𝐓𝐨𝐝𝐚𝐲 - 𝐰𝐡𝐞𝐫𝐞 𝐛𝐞𝐚𝐮𝐭𝐲 𝐜𝐥𝐨𝐜𝐤𝐞𝐝 𝐢𝐧 𝐞𝐚𝐫𝐥𝐲 𝐚𝐧𝐝 𝐬𝐭𝐚𝐲𝐞𝐝 𝐥𝐚𝐭𝐞.🌿 A Sunday dressed in sunshine.🌿 Air so fresh it felt...
14/12/2025

𝐄𝐧𝐭𝐨𝐭𝐨 𝐏𝐚𝐫𝐤, 𝐓𝐨𝐝𝐚𝐲 - 𝐰𝐡𝐞𝐫𝐞 𝐛𝐞𝐚𝐮𝐭𝐲 𝐜𝐥𝐨𝐜𝐤𝐞𝐝 𝐢𝐧 𝐞𝐚𝐫𝐥𝐲 𝐚𝐧𝐝 𝐬𝐭𝐚𝐲𝐞𝐝 𝐥𝐚𝐭𝐞.

🌿 A Sunday dressed in sunshine.

🌿 Air so fresh it felt like a deep breath for the soul.

🌿 A park in full bloom, standing tall and proud.

🌿 Young, radiant minds from the “ 21 days Days” program - preparing not just for jobs, but for purpose.

🌿 A rich, honest conversation on what work culture truly means (hint: it’s more than a paycheck).

🌿 And above all… a beautiful, stubborn hope that refuses to be littered away

𝟏𝟕 𝐯𝐨𝐥𝐮𝐧𝐭𝐞𝐞𝐫𝐬. 𝟏𝟎 𝐤𝐢𝐥𝐨𝐦𝐞𝐭𝐞𝐫𝐬. 𝟏𝟔 𝐤𝐢𝐥𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦𝐬 𝐨𝐟 𝐩𝐥𝐚𝐬𝐭𝐢𝐜 𝐜𝐨𝐥𝐥𝐞𝐜𝐭𝐞𝐝.

Small numbers, big footsteps.
The future showed up today - and it brought gloves.

#ንብትውልድ
Daniel Digafie. Robel Feyissa Ankush Thakur

የነገው የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የግማሽ ቀን ውሏችን በብዙዎችን ዘንድ እጅግ ተጠባቂ ሆኗል :: ነገ ጠዋት በማዕከሉ ግቢ ውስጥ ቀድመው ለሚገኙ 50 ሰዎች በኢትዮዽያ የመጀመሪያው ዕፅዋት ማዕከ...
16/08/2025

የነገው የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የግማሽ ቀን ውሏችን በብዙዎችን ዘንድ እጅግ ተጠባቂ ሆኗል ::

ነገ ጠዋት በማዕከሉ ግቢ ውስጥ ቀድመው ለሚገኙ 50 ሰዎች በኢትዮዽያ የመጀመሪያው ዕፅዋት ማዕከል ውስጥ ለቦታው ተስማሚ የሆኑ የተመረጡ የሀገር በቀል የዛፍ ችግኞችን የመትከል ዕድል ያገኛሉ::

ይህ አጋጣሚ በፍፁም እንዳያመልጣችሁ::

የእርስዎን እና የወዳጅዎን ቦታ ከወዲሁ ያስይዙ!

መገናኛ ቦታ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በር ላይ ከጠዋቱ 1:30

Gullele botanic Garden Main Gate
https://maps.app.goo.gl/v6xRhyLEKuzjYdgb9

📞 ለተጨማሪ መረጃ በማንኛውም ሰዓት ይደውሉልን!
+251942545470 ወይንም በቴሌግራም አድራሻዎቻችን ያግኙን!
#ንብትውልድ

መስከረም ላይ በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አደይ አበቦች ታጅበን "እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ"  ብለን የከፈትነው የ plogging + hiking እንቅስቃሴ በጀት ዓመት በዚህ ሳምንት እሁድ ደ...
11/08/2025

መስከረም ላይ በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አደይ አበቦች ታጅበን "እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ" ብለን የከፈትነው የ plogging + hiking እንቅስቃሴ በጀት ዓመት በዚህ ሳምንት እሁድ ደግሞ "ሆያ ሆዬ" ብለን ልንዘጋው ዝግጅታችንን ጨርሰናል::

ቀን:- 🗓️ ነሀሴ 11 2017 ዓ.ም (እሁድ)
ቦታ:- ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል
Gullele botanic Garden Main Gate
https://maps.app.goo.gl/v6xRhyLEKuzjYdgb9

ከእናንተ የሚጠበቀው የፊታችን እሁድ (ነሀሴ 11 2017 ዓ.ም ) በግል የትራንስፖርት አማራጭ ከጠዋቱ 1:30 በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዋና በር ላይ ከወዳጅ ፣ ቤተሰብ ፣ ጋደኛ ጋር መገኘት ብቻ ነው::

ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነው የጉዞ ፕሮግራም ከ #ፕሎጊንግኢትዮጵያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ፣ በጉዟችን በዕፅዋት ማዕከሉ ውስጥ በቸልተኝነት የተጣሉ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን እናፀዳለን።

ልጆች ሆያ ሆዬ ይጨፍራሉ ፤ አዋቂዎችም ይሸልማሉ:: እርስዎ ከየትኛው ወገን ኖት?

👉 ፕሎጊንግ/plogging የእግር ጉዞ እያደረጉ ወይም ዱብዱብ እያሉ (jogging ) እግረ መንገድ ለአካባቢ ብክለት የሆኑ ቆሻሻዎችን የማንሳት አስደሳች ልምምድ ነው።

በዕለቱ ከ 7-10 ኪሎ ሜትር የሚፈጅ መንገድ በግማሽ ቀን ውስጥ በእግራችን እንጓዛለን ።

ከዚህ ቀደም ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን የመጎብኘት ዕድል ያላገኛቹ ውድ ቤተሰቦቻችን ይህ አጋጣሚ በፍፁም እንዳያመልጣችሁ እናሳስባለን!!

ማስታወሻ

📍ጉዞው የተዘጋጀው በነፃ ሲሆን። ከጉዞ በፊት የሚጠየቅ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ አይኖርም። ሆኖም ግን በዕለቱ የፓርክ መግቢያ እና የአስጎብኚ ክፍያዎችን ለመሸፈን በአንድ ተጓዥ ከ 100 (አንድ መቶ ብር) ያልበለጠ መዋጮ ብቻ ይጠየቃል ።

🥖አማራጭ የክፍያ መንገድ 👉 ለሌሎች ተጓዦችም ጭምር የሚተርፍ ሙልሙል ዳቦ ይዞ መገኘት 🙏

👉ተጓዦች ለግማሽ ቀን ውሏቸው የሚሆን ውሃ በኮዳ እንዲሁም ቀለል ያለ ምግብ (snacks) በቦርሳቸው እንዲይዙ እንመክራለን።

ያለንበት ወቅት ዝናባማ እንደመሆኑ መጠን ከወቅቱ አየር ጋር ሊሄድ የሚችል አለባበስ ይመረጣል።

✅ ለጉዞ ምቹ የሆነ ጫማ ይዘጋጅ (ከዚህ ቀደም በእግር ጉዞ የተሞከረ ይሁን ፣ እርጥበታማ ወይንም ጭቃማ መንገድ ላይ የማያንሸራትት )

👉 ለድንገተኛ ዝናብ የሚሆን የዝናብ ልብስ ወይንም ዣንጥላ ይያዝ።

👉 በድጋሚ ይህ ጉዞ ሁሉም ተጓዥ የራሱን የትራንስፖርት አማራጭ በመጠቀም የሚገናኝበት የጉዞ ፕሮግራም መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን::

መኪና በዕፅዋት ማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለምንም የደህንነት ስጋት ማቆም ይቻላል።

📞 ቦታ ለማስያዝ እንዲሁም ለተጨማሪ መረጃዎች እነዚህን የስልክ አድራሻዎች ብቻ ይጠቀሙ!!
+251942545470

እንዲሁም comment ላይ ''አለሁ'' በማለት አስቀድሞ ቦታ ማስያዝ ይቻላል።

07/08/2025

አይሆንም ያሉት ሲደርስ፥ አይድረስ!Firew Kefyalew ከቀኑ 11፡45 ሰዓት ቢሆን ነው።  ቅዳሜ ቀን ነው   ስልኬን ጆሮዬ ላይ ለጥፌ ከ8 ዓመት በፊት የተመረቁ ተማሪዎቼን ገለፃ በፍፁም...
14/06/2025

አይሆንም ያሉት ሲደርስ፥ አይድረስ!
Firew Kefyalew

ከቀኑ 11፡45 ሰዓት ቢሆን ነው።

ቅዳሜ ቀን ነው

ስልኬን ጆሮዬ ላይ ለጥፌ ከ8 ዓመት በፊት የተመረቁ ተማሪዎቼን ገለፃ በፍፁም ተመስጦ እሰማለሁ። ተቀጣጥረን በበይነ መረብ መሰባሰባችን ነው። የዛሬ 8 ዓመት በማስተርስ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ትምህርቱ ምን ያህል እንደጠቀማቸው ስለሚያወሩ ቀልቤ ሁሉ እነሱ ዘንድ ነው።

ከአሜሪካ፥ ህንድ፥ ኔፓል፥ ጋና፥ ኢትዮጵያ፥ ዑጋንዳ፥ ሶማልያ ወዘተ ተሰባስበናል።

ለ 45 ደቂቃዎች በእግሬ እየተጓዝኩ ይህንኑ የቀድሞ ተማሪዎችን ገለፃ እሰማለሁ። ቁጭ ብዬ እንዳልሰማቸው የሚመች ቦታ አላገኘሁም። ከሆስፒታል የታመመ ሰው ከጠየቅሁ በኋላ በዚያው ወጥቼ በእግሬ እየተጓዝኩ መስማት ቀጠልኩ።

መንገዱ ሰው ብቻ ነው፥ አውራ ጎዳናውም በመኪና ተጨናንቋል። አዲስ የተሰራውን የእግረኛ መንገድ ይዤ፥ ሰው እንዳይገጨኝ እየተጠነቀቅሁ፥ እግሬን እየጎተትኩ እጓዛለሁ። የፊት ገፄን ላየው በእርጋታ አንዳች የፍቅር ወሬ የምሰማ ሳያስመስለኝ አይቀርም።

ከተማሪዎቼ ጋር በጣም ልዩ ትዝታ አለኝ። የማስተርስ ትምህርታቸውን ከህንድ ጀምረው፥ ማኅተማ ጋንዲ በኖረበት ግቢ እንደሱ እየኖሩ ተምረው፥ ከዚያም በዑጋንዳና ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከማኅበረሰቦች እየተማሩ፥ በመጨረሻም ፊሊፒንስ የማይረሳ ጊዜ አሳልፈን ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል። ምረቃቸው ፊሊፒንስ ነበር።

በስልኬ የሚመጣውን ወግ እየኮመኮምኩ፥ የቦሌን ድልድይ ወደኋላዬ ትቼ አዲስ በተሰራውና ወደጎሮ በሚዘልቀው መንገድ እየሄድኩ ነው። በዚህ መንገድ በየቀኑ የእግር ጉዞ ስለማደርግ ሰፈሬ የሆነ ያህል ይሰማኛል።

ወደ አየር ማረፊያ ጣቢያው ከሚያስገባው ሁለተኛ በር መታጠፊያ አለፍ ብዬ አንድ መቶ ሜትር የሚሆን እንኳ ሳልሄድ የማገኘውን፥ ሁልጊዜም ለምን መንገዱ እንዲህ አምሮ ተሰርቶ ቸል እንደተባለ የሚገርመኝን የፍሳሽ ማስወገጃ ድልድይ አለፍኩት። በድልድዩ ሥር ሽታው የሚሰነፍጥ፥ ለዓይንም የሚቀፍ ቆሻሻ ወይ ረግቶ አሊያም ሲወርድ ይታያል። አልፎ አልፎ ወንዶች ጠጋ ብለው ወደፍሳሹ ሲሸኑም ታዝቤ አውቃለሁ።

ይህንን ቀፋፊ ድልድይ አለፍ ብዬ አንድ 10 ሜትር የሚሆን እንደተጓዝኩ እጅግ በፈጠነና ለማሰብ ጊዜ በማይሰጥ ቅፅበት እያዳመጥኩበት የነበረው ስልኬ ከግራ እጄ ላይ ተሞጨለፈ!

መጀመሪያ አጓጉል የጓደኛ ቀልድ መሰለኝ … ቀጥሎ እየተዘረፍኩ እንደሆነ ተገለጠልኝ።

መንገዱ በቅዳሜ ከሰዓት እግረኞች ተጨናንቋል። ትንሽ ቀደም ብዬ ጥንድ ፖሊሶች ጋር ዓይን ለዓይን ስንገጣጠምም አስታውሳለሁ። አካባቢው ምንም ለሥጋት የሚጋብዝ ነገር የለውም።

አንድ ቀጠንና ዘለግ ያለ ወጣት ስልኬን ከእጄ ነጥቆ ሲንደፋደፍ ሮጦ ለማምለጥ እየሞከረ ስለመሰለኝ በልቤ የንቀት ሳቅ ሳቅሁበት … “አሁን በዚህ አሯሯጥህ የምታመልጠኝ ይመስልሃል?” ዓይነት። እንደማያመልጠኝ በጣም ርግጠኛ ነበርኩ።

ያዘው! ሌባ! ያዘው! ሌባ! ጮኽኩና ተፈተለኩ…

ግን ወዲያው ዳዴ ጀምሮ እንደሚውተረተር ህፃን እግረኛ መንገዱ ላይ በ ፊት ለፊቴ አጓጉል ወደቅሁ። እንደዚህ ተንዘራግቼ የወደቅሁበት ጊዜ ትዝ አይለኝም፤ እንደምንም ተንገዳግጄ የምቆም አለበለዚያም በግማሽ መሬት ነክቼ የምመልስ ዓይነት ሰው ነበርኩ። አሁን ግን ወደቅሁ፤ ተስፋ ና ድጋፍ እንደሌለው ሰው፥ አቅም እንደሌለው ድኩም ወደቅሁ!

አሁን ሳስበው ሳልጠለፍ አልቀረሁም፤ መጀመሪያ ግን አንሸራቶኝ መስሎኝ ነበር። ሁለት ነበሯ! አንደኛው ነጥቆ ሲሮጥ፥ ሁለተኛው በሾኬ እንዲመታ ሳይመዳደቡ አልቀሩም።

ይሄ ሁሉ ሆኖ ከወደቅሁበት ሊያነሳኝ የሞከረ የለም። በእንዲህ ያለው ክፉ አጋጣሚ ሀዘናቸውን ለመግለፅም ሆነ ለማፅናናት የማይቦዝኑት የእናት ደመነፍስ ያላቸው ባዳዎችም የሉም። አንድ ሽበት የወረረው ጎልማሳ በጠራራ ፀሐይ ንብረቱን ሲዘረፍ፥ ያም አላንስ ብሎ በአስጊ ሁኔታ ሲወድቅ እንዴት “እኔን!” የሚል ይጠፋል? ሁሉም ቆም ብሎ አይቶ ወደጉዳዩ ይጓዛል፤ እንጂ በድንጋጤ ወይም በሐዘን የሚያዩኝ አዛኝ ዓይኖች ባማትር የሉም!

በአደግኩበት አካባቢ “እኔን!” እና “አይዞህ!” ማንም የማይሰስታችው የመጀመሪያ ዕርዳታዎች ናቸው።

ከወደቅሁበት ተንስቼ ለመከተል አንድ ሁለት እርምጃ እንደተራመድኩ ሁለቱ ነጣቂዎች እዚያ ቀፋፊ ድልድይ ሥር ወዳለው ቱቦ ተወርወረው ሲገቡ አየኋቸው። አንድ ልጅ’ግር ፖሊስ ተከትሎ ገባ …

አሁን ያ ስነጠቅም ሆነ ስወድቅ ለመርዳት ያልተጋ ተመልካች ያችን ድልድይ ከላይ ከታችም ወረራት። እኔም ወደቱቦው አፍ ከሰው እየተጋፋሁና እያነከስኩ ደረስኩ። ጉልበቶቼ፥ መዳፌ፥ ትከሻዬ፥ ቀፈቴ ያልተቀጠቀጠ የለም። ትንሽ ደምም ይፈሰኛል። የለበስኩት ጂንስ ሱሪ ጉልበቱ ላይ በምላጭ እንደተሸነተረ ዓይነት ወደጎን ተቀዷል፣ ስወድቅ ከእግረኛው መንገድ ጋር ምን ያህል በኃይል እንደተላተምኩ ያሳያል።

ፖሊሱ ነጣቂዎችን ተከትሎ በቱቦው በጣም እውስጥ ድረስ ገብቷል።

… ይዞታል፥ አይለቀውም

… መሳሪያ ስላልያዘና እነሱ ሁለት ስለሆኑ ይጎዱታል

… ኤሄሄ ይሄኔ እናጅሬ በሌላ አቅጣጫ ወጥተዋል

… አሁን ይሄ ሰውዬ ሲሰረቅ (እኔን ነው) 3 ኛው ነው፥ ማንም አይዛቸውም።

መጯጯሁ እየቀነሰ ሲመጣ ፖሊሱ እንዳልሆነለት አወቅሁ። ሰውም አይዞህ ና እያለ እንዲወጣ ፖሊሱን ማደፋፈር ያዘ… በሰው ድጋፍ ተጎትቶ ወጣ። መላ ሰውነቱ፣ ፊቱ ሳይቀር በዚያ በካይ ቆሻሻ ተለውሷል። ሙሉ በሙሉ ራሱን ያውቃል ማለት አይቻልም።

አሁን ስልኬን ረሳሁት። የወጣቱ ፖሊስ ነገር ያሳስበኝ ያዘ፤ በእኔ ጦስ ምንም እንዳይደርስበት ፀለይኩ። ሁኔታው ያስፈራል …

በዚህ ሁሉ መሃከል እኔን በጥያቄ የሚያዋክበኝ ሰው ብዙ ነው። ምናልባት የስቪል ልብስ የለበሱ ፖሊሶች እንደሆኑ እያልኩ እመልሳለሁ….

… የት ጋ ነው?

… ምን ዓይነት ስልክ ነው?

… ምን ስታደርግ ወሰዱብህ?

… ስንት ናቸው?

… ፖሊሱ ለምን ተከትሏቸው ገባ?

… ሴቷ ፖሊስ ለምን አብራ አልገባችም?

… እነዚህ ላይ ተከታትሎ አንድ ካርታ እላያቸው ላይ መጨረስ ነበር (በስማ’ብ!)

አንድ የሬድዮ መገናኛ የያዘ ፖሊስ ደርሶ ወደ ቦሌ ድልድይ አቅጣጫ የሚሄድ ሚኒባስ አስቆመና ከሴቷ ፖሊስና ሌላ ከየት እንደመጣ ያለየሁት ፖሊስ ጋር ወደ ሐኪም ቤት እንድንሄድ አዘዘ። ትዕዛዙ እኔ ላይ የበረታ ይመስላል፤ መቅረትም ብፈልግ የሚያስቀረኝ ዓይነት አይደለም።

የሚኒባሱ ሾፌር ፖሊስ ስለጫነ የልብ ልብ ተሰሞቶት እንደሆነ አላውቅም ይከንፋል፤ ሌላ ጊዜ ፍጥነት የሚያስበረግገኝ ሰውዬ አሁን ወድጄዋለሁ፤ የተጎዳው ፖሊስ በቶሎ ሕክማን እንዲያገኝ ፈልጌያለሁ።

ሚኒባሱ ወደሰፈሬ አቅጣጫ ሲከንፍ ሆስፒታል እየሄድን መስሎኝ ነበር፤ ግን የለም ጤና ጣቢያ ነው የሚሄደው ተባለ። እባካችሁ ሆስፒታል እንውሰደውና ዕርዳታ ያግኝ ብልም፥ የእኔን ሩብ እንኳ ያልተጨነቀው ወንዱ ፖሊስ ወደ ጤና ጣቢያ እንዲነዳ ሾፌሩን ኮስተር ብሎ አዘዘው። ሴቷ ፖሊስ ማልቀስ ከጀመረች ቆይታለች፣ ቡቡ ዓይነት ናት።

ጤና ጣቢያው ከትንሽ ተፍተፍና ትርምስ በኋላ ወደ ሆስፒታል ሪፈር ፃፈለትና እነሱ ሲሄዱ እኔ ቃሌን እንድሰጥ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰድኩ። መርማሪው ከመሸ ደረሰና ጧት መጥቼ ቃሌን እንድሰጥ ነግሮ አሰናበተኝ።

በኋላ እንደሰማሁት የተጎዳው ፖሊስ መጀመሪያ ወደተላከበት ሆስፒታል ዕርዳታ ሊያገኝ ባለመቻሉ፥ በመጨረሻ ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ተወስዷል። ጤና ጣቢያው በቀጥታ ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ሪፈር መፃፍ እንደማይችልም ሰማሁ።

ግራ የገባኝ ነገር የህዝብን ደህንነት ሊጠብቅ ወጥቶ ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት የፖሊስ አባል ለምን በአቅራቢያው በሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ዕርዳታ የማግኘት መብት እንደማይኖረው ነው። ፖሊሱ ከቀናት በኋላ ተሽሎት ወጥቶ፥ ከአጭር ዕረፍት በኋላ ወደመደበኛ ሥራው ተመልሷል።

ከቀናት በኋላ በአራት ሰዓታት የቱቦ ለቱቦ ክትትል የተያዙ ስልክ ነጥቀው የሸሹ ሦስት ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ሰማሁ።

የእኔው ነጣቂ ከእነሱ አንዱ ይሆን?

ስልኬ ግን አሁንም የሌባ ተቀባይ እጅ እስከ አሁን የገባ አይመስልም። ከገባ የመገኘት ዕድሉ ሰፊ ነው፤ልምድ አለኝ።

የስልኬን መዘረፍ የሰማ ሰው ሁሉ የሚነግረኝ ተመሳሳይ ታሪክ ዘግናኝ ነው። ከተማው ለእንቅስቃሴ የሚያስፈራ ይመስላል። መቸስ በራስ ሲደርስ አይደል የሚታወቅ!

ጎበዝ እየተጠነቀቃችሁ፤ ቢቻል በአደባባይ ብቻችሁን ሆናችሁ አስጎምዢ ስልካችሁን አትጠቀሙ። ጊዜው ከፍቷል!

ሌላ የእርካታ ምንጭ የሆነን ሰንበት!42 ሆነን፣ እስከ 16 ኪሜ የሚደርስ የእግር ጉዞ በማድረግ ከ 30 ኪግ በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ የሰበሰብንበት፣ ለስልጠና ኩሪፍቱ የነበሩ ወጣቶችን (Int...
09/02/2025

ሌላ የእርካታ ምንጭ የሆነን ሰንበት!

42 ሆነን፣ እስከ 16 ኪሜ የሚደርስ የእግር ጉዞ በማድረግ ከ 30 ኪግ በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ የሰበሰብንበት፣ ለስልጠና ኩሪፍቱ የነበሩ ወጣቶችን (Interactors) አግኝተን ሃሳባችንን ያካፈልንበት የዛሬው እሑድ ሸጋ ነበር።
፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧፨፧

(በቅንፍ ደግሞ እንዲህ አለቃቅሳለሁ። ምነው ቢሉ ደሞ ከሽሮ ጋር በተፋጠጠኩበት በዚህ አስተዛዛቢ ጊዜ ሀሌታ ሀሌታ ጮማ ከብርንዶ ያማረጠችበትን ቪዲዮ ለቀቀችዋ! ፌር አይደለም!😂😂😂)

#ንብትውልድ

Big shout our to my new rising fans! Amdework Tibebu
07/02/2025

Big shout our to my new rising fans! Amdework Tibebu

Shout out to our newest followers! Excited to have you onboard! Amdework Tibebu, Maza Maza #ንብትውልድ
29/01/2025

Shout out to our newest followers! Excited to have you onboard! Amdework Tibebu, Maza Maza

#ንብትውልድ

05/01/2025

ሃገርም እንደሰው...

ላለፉት 2 ወራት ከኢትዮጰያ ውጭ ስቆይ ከልብ ይናፍቀኝ የነበረው በየሳምንቱ በአብዛኛው በእንጦጦ ፓርክ የማደርገው ሳምንታዊ የፕሎጊንግ እንቅስቃሴ ነበር።

በነበርኩበት ሃገር ያደርግኋቸው ሁለት የፕሎጊንግ እንቅስቃሴዎች ይህንን ናፍቆቴን የሚያሰታግሱ አልነበሩም። የራሳቸው ልዩ ጣዕም ግን ነበራቸው።

የእንጦጦው (እና ሌሎችም የሃገራችን አካባቢዎች) እንቅስቃሴ ሁልጊዜም ልዩ ነው።

እና ዛሬ በጧት በፍርስራሽ ተሹለኩልኬ፣ አቧራ እቀዘፍኩ፣ በተስኪያን ሳሚ ግራና ቀኜን ያጀበኝ ያህል እየተሰማኝ ደረስኩ።

ሁሌም ጧት 2 ሰዓት ላይ የምንገናኝበት በቁሰቋም አልፎ የሚገኘው የፓርኩ መግቢያ በር አካባቢ ተለውጦ እንደ እንግዳ ሊያደርገኝ ዳዳው።

ኮንሶን እግዜር ይስጠው!

ንቦቹ ኮንሶዎች የአስገራሚ ጥበባቸውን እፍታ መግቢያው በር አካባቢ በማሳየት ይጀምሩና ወደውስጥ ይዘልቃሉ።

ይህን ሁላ ምነዜ ሰሩት?!!!

እንደውነቱ የዓለም ድንቅ የሆነ ጥበባቸው ከታላቋ ሃገር መዲና ለመድረስ የፈጀው ጊዜ ይቆረቁራል።

(እግረመንድ) የኮንሶን ጥበብ ወደ "ዓዲ-ሳባ" እንዲዘልቅ ያሳሰቡትንም ያዘለቁትንም ማመስገን ይገባል!

(በነካ እጃቸው የትግራይን ድንቅ የሕድሞ ጥበብ፣ የሲዳማውንና የጋሞውን የቤት አሰራር ወዘተ እንዲያስቡት እመኛለሁ።)

እና የናፈቀችኝ እንጦጦ አምራ ጠበቀችኝ ነው'ምላችሁ።

11 ፕሎገሮች በዛሬው የበዓል ዋዜማ እንቅስቃሴ ከ10 ኪሜ የዘለቀ ርቀት በመሸፈን 12 ኪግ የፕላስቲክ ቆሻሻ ሰብስበናል።

የገና ስጦታም ተለዋውጠናል።

የሳምንት ሰው ይበለን!

#ንብትውልድ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ:

Share