አፋልጉኝ Afalgugn - reunite missing persons return lost and found items

አፋልጉኝ Afalgugn - reunite missing persons return lost and found items የጠፉ ሰዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ፤ ጠፍቶ የተገኘ ዕቃ ለባለቤቱ ?

አፋልጉኝ የጠፉ ሰዎች ለመፈለግ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት የተቋቋመ የበጎ-ፈቃደኞች ኔትወርክ ነው። አፋልጉኝ የአፋልጉኝ ፍለጋ ቀላል እንዲሆን በማሰብ ሙሉ ትኩረቱን የጠፉ ሰዎች ላይ ያደረገ www.afalgugn.com የተባለ ዌብሳይት ገንብቷል። መረጃ በፍጥነት እና በቀላሉ ለመለዋወጥ በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ከዌብሳይታችን ጋር የተሳሰረ አካውንት ፣ ገጽ ፣ ግሩፕ እና ቻናል አለው።

ፌስቡክ እና መሰል ፕላትፎርሞች የተሰሩበት አላማ ሌላ ስለሆነ የጠፋ ሰው ለማፈላለጊያነት ለመጠቀም ውስንነቶች አሉባቸው። ለምሳሌ:- የዛሬ 3ወር ሼር ያደረግነው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ዛሬ ለማየት ብንፈልግ አመቺ ካለመሆኑም በላይ ለሚከተሉን

ጓደኞቻችን ብቻ ለአንድ ጊዜ ታይቶ ከእይታ ይጠፋል ፤ ብዙ ሰዎች የተለያየ እና ተደራሽ ያልሆኑ ገጾች ስለሚጠቀሙ መረጃው የተበታተነ ይሆናል ፤ ስለ ጠፉ ሰዎች የተደራጀ መረጃ አይኖርም ፤ ሰዎች ትኩረታቸውን ሰብስበው ለመወያየት አያመችም ፤ የአፋልጉኝ ዌብሳይት እነዚህንና እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል።

ከሁሉም በላይ በአካል እና በኦንላይን ለማገዝ ከተለያዩ ቦታዎች የተመረጡ የበጎ ፈቃደኞች ኔትወርክ አለው። ከእርሶ የሚጠበቀው በኦንላይን ፣ በአካል ወይም በሁለቱም በጎ-ፈቃደኛ ሆኖ በመሳተፍ ማገዝ ነው።

ለምን www.afalgugn.com እና የበጎ-ፈቃደኛ ኔትወርክ አስፈለገ?
ዋና ዋና ምክንያቶች:-
1ኛ) የጠፋ ሰው መፈለግ እጅግ ከባድ እና አድካሚ በመሆኑ
2ኛ) የጠፋ ሰው መፈለግ ከሰዓታት አንዳንዴ እስከ ዓመታት ሊወስድ የሚችል በመሆኑ
3ኛ) በግለሰብ ወይም ቤተሰብ ደረጃ ብቻ የጠፋ ሰው ፈልጎ ማግኘት አዳጋች በመሆኑ
4ኛ) በዘመቻ እና በተጠና መልኩ በአካል ሰዎችን መፈለግ አስፈላጊ በመሆኑ
5ኛ) ፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች አጋዥ እንጂ የጠፉ ሰዎችን ለመፈለግ ተብሎ የተሰራ ድህረ-ገጽ የማይተኩ በመሆኑ
6ኛ) የጠፋ ሰው ለመፈለግ በአንድ ቦታ የተደራጀ ፣ መረጃ ለማስገባት እና ለማየት ቀላል የሆነ ፣ ተደራሽነት ያለው እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ ዌብሳይት አስፈላጊ በመሆኑ
7ኛ) ስለ ጠፋ ግለሰብ የሚለቀቅ መረጃ የተሟላ ፣ ትክክለኛነቱ እና ወቅታዊነቱ የተረጋገጠ መሆን ስላለበት
8ኛ) በየትኛውም ቦታ እና ዲቫይስ ፣ በተመቸን ሰዓት ለመጠቀም አመቺ የሆነ እና ከሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ጋር የተሳሰረ አሰራር አስፈላጊ በመሆኑ

Address

AA
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አፋልጉኝ Afalgugn - reunite missing persons return lost and found items posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to አፋልጉኝ Afalgugn - reunite missing persons return lost and found items:

Share