Hope Walks-Ethiopia

Hope Walks-Ethiopia It is the official page of Hope Walks Ethiopia which aims to reduce disability secondary to idiopathic clubfoot in Ethiopia by creating awareness.

በአፋር ክልል የነበረንን ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል። በቆይታችን ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ህክምና አስጀምረናል፣ በተለያዩ የጤና ተቋማት በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እ...
24/09/2026

በአፋር ክልል የነበረንን ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል። በቆይታችን ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ህክምና አስጀምረናል፣ በተለያዩ የጤና ተቋማት በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር ልየታ እና ህጻናትን ሲያገኙ ወዴት መላክ እንዳለባቸው ግንዛቤ ሰተናል፣ በተጨማሪም ሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና ለማህበረሰቡም ስለ ዞረ እግር አስተምረን ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ሲያገኙ ነጻ ህክምና ወደ ሚሰጥባቸው ተቋማት እንዲያመጧቸው አስተምረን ሳምንታችንን አጠናቀናል።

ህጻናትን በጊዜ ወደ ህክምና በማምጣት ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት እንታደጋቸው!!! 👣

 👣
22/09/2026

👣

የአፋር ክልል ቆይታችን እንደቀጠለ ነው። ከዞረ እግር(clubfoot) ጋር የተወለዱ ልጆች እየተለዩ ህክምና እየጀመሩ ነው፣ በተለያዩ ገበያዎች በመገኘት ግንዛቤም እያስጨበጥን ነው። ከዛም በተ...
21/09/2026

የአፋር ክልል ቆይታችን እንደቀጠለ ነው። ከዞረ እግር(clubfoot) ጋር የተወለዱ ልጆች እየተለዩ ህክምና እየጀመሩ ነው፣ በተለያዩ ገበያዎች በመገኘት ግንዛቤም እያስጨበጥን ነው። ከዛም በተጨማሪ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች እና ህጻናት ላይ ለሚሰሩ ማህበራት፣ ለሃይማኖት አባቶች እና ለልምድ አዋላጆች ስለዞረ እግር ግንዛቤ እየሰጠን እንገኛለን።

እናንተም የምታውቋቸው ህጻናቶች ካሉ በጊዜ ወደ ህክምና እንዲመጡ በማድረግ ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት ታደጏቸው!!! 👣

በትላንትናው እለት ወደ አፋር ክልል በመጓዝ የዘመቻ ስራችንን ጀምረናል። ዘመቻው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን እንደተለመደው በተለያዩ የጤና ተቋማት ውስጥ በመገኘት ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ...
18/09/2026

በትላንትናው እለት ወደ አፋር ክልል በመጓዝ የዘመቻ ስራችንን ጀምረናል። ዘመቻው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን እንደተለመደው በተለያዩ የጤና ተቋማት ውስጥ በመገኘት ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ልየታ እና ህክምና ማስጀመር። እንዲሁም ጎን ለጎን ለህክምና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር ልየታ እና ማስተሳሰር ስልጠና መስጠት፣ ሴቶች እና ህጻናት ላይ ለሚሰሩ ማህበራት፣ ለሃይማኖት አባቶች እና ማህበረሰቡ በሚሰበሰብበት ቦታዎች በመገኘት ስለ ዞረ እግር ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በመስራት እንሰነብታለን።

እናንተም የምታውቋቸው ህጻናቶች ካሉ በጊዜ ወደ ህክምና እንዲመጡ በማድረግ ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት ታደጏቸው!!! 👣

የዞረ እግር (clubfoot) በህክምና ይድናል!! ህክምናውም ነፃ ነው!የዞረ እግር (clubfoot) ሕክምና ሂደት ሁለት ዋና ደረጃዎች አሉት፦🔹 1ኛ የማስተካከያ ደረጃይህም በጄሶ (casti...
16/09/2026

የዞረ እግር (clubfoot) በህክምና ይድናል!! ህክምናውም ነፃ ነው!

የዞረ እግር (clubfoot) ሕክምና ሂደት ሁለት ዋና ደረጃዎች አሉት፦

🔹 1ኛ የማስተካከያ ደረጃ
ይህም በጄሶ (casting) የዞረውን እግር ቀስ በቀስ ማስተካከል። ብዙውን ጊዜ ህክምናው ከ 6-8 ሳምንታት ሊቆይ ይችላል። ከዚያ በኋላ አነስተኛ ቀዶ ጥገና (tenotomy) ይደረጋል።

🔹 2ኛ የማቆያ ደረጃ
ህጻናቱ እግሩ የተስተካከለበትን ቦታ እንዲጠብቅ የሚያግዝ ጫማ (brace) ይለብሳል። ጫማው(brace) የተስተካከለውን እግር በትክክለኛ አቀማመጥ እንዲቆይ ይረዳል።

ህጻናት ህክምናውን ቶሎ ሲጀምሩ በቀላሉ ከእኩዮቻቸው ጋር መጫወት እና መቦረቅ ይችላሉ!!!

11/09/2026
ሆፕ ዋክስ ከክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢንሺዬቲቭ(CHAI) ጋር በመተባበር በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ኢትዮ- ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኘውን የቆልማማ እግር(clubfoot) ህክምና ክፍል በማደስ እ...
08/09/2026

ሆፕ ዋክስ ከክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢንሺዬቲቭ(CHAI) ጋር በመተባበር በድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ኢትዮ- ፈረንሳይ ውስጥ የሚገኘውን የቆልማማ እግር(clubfoot) ህክምና ክፍል በማደስ እና በማስዋብ በተጨማሪም የልጆች የመጫወቻ ክፍልን አዘጋጅቶ በዛሬው እለት አስመርቋል። በምርቃት ስነስርቱ ላይ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ፣ የሆፕ ዋክስ እና ክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢንሺዬቲቭ አመራሮች፣የሆስፒታሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ህክምናውን በማግኘት ላይ ያሉ ህጻናት እና ወላጆችም ተገኝተዋል።
የልጆች መጫወቻ ክፍሉ ህጻናቱ የቆልማማ እግር(clubfoot) ህክምናውንም እያገኙ የሚያርፉበት እንዲሁም ህመማቸውን እረስተው መልካም ጊዜ የሚያሳልፉበት ክፍል ነው!!

ቆልማማ እግር(club foot) በህክምና ይድናል!!!!

ላለፉት አምስት ቀናት በሲዳማ ክልል የነበረንን ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል። በቆይታችን በተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር ግንዛቤ ማስጨበጥ፣...
05/09/2026

ላለፉት አምስት ቀናት በሲዳማ ክልል የነበረንን ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል። በቆይታችን በተለያዩ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ልየታ እና ህክምና ማስጀመር። በተጨማሪም ሴቶች, ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እና ለማህበረሰቡም ስለ ዞረ እግር አስተምረን እና ህጻናት ከዞረ እግር ጋር ሲወለዱ በሲዳማ ክልል ውስጥ ባሉ ነጻ ህክምና ወደ ሚሰጥባቸው ተቋማት እንዲያመጧቸው አስተምረን ሳምንታችንን አጠናቀናል።
ህጻናትን በጊዜ ወደ ህክምና በማምጣት ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት እንታደጋቸው።

በዛሬው እለት የተለያዩ ተቋማት ውስጥ በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር እና ህጻናትን ሲያገኙ ወዴት መላክ እንዳለባቸው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ስንከውን ዉለናል። ከዛም በተጨማሪ በ...
03/09/2026

በዛሬው እለት የተለያዩ ተቋማት ውስጥ በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች ስለ ዞረ እግር እና ህጻናትን ሲያገኙ ወዴት መላክ እንዳለባቸው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ስንከውን ዉለናል። ከዛም በተጨማሪ በጤና ጣቢያዎች ላገኘናቸው ወላጆች ስለ ዞረ እግር የግንዛቤ ማስጨበጥን እንዲሁም የሴቶች, ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ውሰጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች። በስተመጨረሻም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚገኙበት ገበያ ውሰጥ ግንዛቤ በማስጨበጥ ቀናችንን አጠናቀናል።

ህጻናትን በጊዜ ወደ ህክምና በማምጣት ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት እንታደጋቸው!!

በሲዳማ ክልል ያለን ቆይታ እንደቀጠለ ነው። ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ልጆችን ህክምና እያስጀመርን, በተለያዩ የጤና ተቋማት ውሰጥ በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች የዞረ እግር ቅድመ ልየታ እና ማ...
02/09/2026

በሲዳማ ክልል ያለን ቆይታ እንደቀጠለ ነው። ከዞረ እግር ጋር የተወለዱ ልጆችን ህክምና እያስጀመርን, በተለያዩ የጤና ተቋማት ውሰጥ በመገኘት ለጤና ባለሙያዎች የዞረ እግር ቅድመ ልየታ እና ማስተሳሰር ስልጠናን መስጠት, እንዲሁም ልጆችን ለማስከተብ ለሚመጡ እናቶች እና ለማህበረሰቡ ስለ ዞረ እግር ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራችንን እንደቀጠልን ነው።
እናንተም የምታውቋቸው ህጻናቶች ካሉ በጊዜ ወደ ህክምና እንዲመጡ በማድረግ ከዘላቂ አካል ጉዳተኝነት ታደጏቸው!!!

Address

Roosvelt Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hope Walks-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Hope Walks-Ethiopia:

Shortcuts

Share