Enpursha motivation

Enpursha motivation This page is enpursha motivationa. Enpursha is konso word which means i am gonna change.

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች በቅርቡ ባሰወቅናችሁ መሰረት ዛሬ የዝግጅታችንን መጀመሪያ እንግዳ ከሆነችው ባለታሪክ ወ/ሮ ጥሩነሽ ተስፋዬ ጋር ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። ስለሆነም ከስር ባስ...
01/05/2026

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች በቅርቡ ባሰወቅናችሁ መሰረት ዛሬ የዝግጅታችንን መጀመሪያ እንግዳ ከሆነችው ባለታሪክ ወ/ሮ ጥሩነሽ ተስፋዬ ጋር ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። ስለሆነም ከስር ባስቀመጥነው የቴሌግራም ሊንክ እየገባችሁ የቻናላችንን ቤተሰብ በመሆን ዝግጅቱን ዛሬ ምሽት 3:00 በቀጥታ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። ከተመቻችሁ መረጃውን ሼር በማድረግ ለሌሎች ጋር እንዲደርሱ ያድርጉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+nq8SXYh5i0pkZjdk

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ ስራችን ተመልሰናል። ኅዳር 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ የስራ ፈተና ለመፈተን ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ለመጀመር ኮንሶ ዞ...
28/04/2026

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ ስራችን ተመልሰናል። ኅዳር 5/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ የስራ ፈተና ለመፈተን ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ለመጀመር ኮንሶ ዞን ከና ወረዳ መጨቄ ቀበሌ ከሚገኘው መኖሪያ ሰፈር ጥቂት በሞተር እንደተንቀሳቀሰች ከተወሰኑ ደቂቃ በኋላ የገዛ እጮኛዋ መንገድ በመዝጋት ያላትን ዶክመንት፣ ገንዘብ፣ መታወቂያ እንዲሁም ልብሷን በሙሉ ይወስድባት እና ይሰወርባታል። በዚህ መሃል መረጃው እኛ ጋር ደርሶ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲሰባሰብላት የማስተበባር ስራ ሰርተን በእናነት በደጋጎች በአንድ ቀን ከሚፈለገው በላይ ገንዘብ ተሰብስቦላት አዲስ አበባ መጥታ ፈተናዋን እንድትፈተን ማድረግ ችለናል። "አሁን" ትላለች እንግዳችን "ታሪክ ተቀይሯል! የተሻለ ስራ አዲስ አበባ አግኝቻለሁ እንዲሁም ትዳር መስርቻለሁ!" ብላናለች። ስለሆነም የተወደዳችሁ ቤተሰብ የፊታችን ዓርብ ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ላይ በቴሌግራም ቻናላችን በቀጥታ ያለፈችበት የሕይወት ተሞክሮና የምታጋራን ይሆናል። ፕሮግራሙን በቀጥታ ለመከታተል ከስር በሚገኘው የቴሌግራም ሊንክ በመግባት የእንፑርሻ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://t.me/+nq8SXYh5i0pkZjdk

ተመልሰናል! አዲስ ምዕራፍ ለእንፑርሻ ውድ የኢንፑርሻ ቤተሰቦችእንደምን ሰነበታችሁ! አዳዲስ መረጃዎችን ለእናንተ ካደረስን ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል፤ የእንፑርሻን ቤተሰብ በእጅጉ ናፍቀን ነበር።ኢን...
23/04/2026

ተመልሰናል! አዲስ ምዕራፍ ለእንፑርሻ

ውድ የኢንፑርሻ ቤተሰቦች

እንደምን ሰነበታችሁ! አዳዲስ መረጃዎችን ለእናንተ ካደረስን ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል፤ የእንፑርሻን ቤተሰብ በእጅጉ ናፍቀን ነበር።

ኢንፑርሻ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለዕድገትና ለለውጥ በትጋት ሲሰራ ቆይቷል። ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ወጣቶችን፣ የመንግስት ሰራተኞችንና ባለስልጣናትን ጨምሮ ከ2,000 በላይ ሰዎችን በማሰልጠናችን ኩራት ይሰማናል። ከስልጠናዎቹም ባሻገር፣ የቴሌግራም ቻናላችን አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን የቀጥታ ምስክርነቶች የሚጋሩበት ጠንካራ መድረክ መሆኑ ይታወቃል በዚህም በሀገር ውስጥ ይሁን ከሀገር ውጭ እንግዶችን ጋብዘን ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ማድረግ ችለናል።

ባጋጠሙን አንዳንድ ሁኔታዎች በተለይም ደግሞ በየሳምነቱ የምናደርገው የቀጥታ ፕሮግራሞቻችንን ለተወሰነ ጊዜ ለማቋረጥ ተገደን ነበር። ሆኖም ግን፣ ያ የነበረን መነሳሳትና ራዕይ ከእኛ አልጠፋም። አሁን የተሻለ አቅም፣ የታደሰ ጉልበትና እናንተን ለማገልገል የሚያስችል ጠንካራ ራዕይ ይዘን በይፋ ተመልሰናል።

በቅርብ ቀን ቀጥታ የቴሌግራመ ፕሮግራሞቻችንን በድጋሚ እንጀምራለን። እስከዚያው ድረስ፣ የቴሌግራም ቻናላችንን መቀላቀላችሁን እርግጠኛ ሁኑ! እናመሰግናለን። የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ https://t.me/xonsopursha

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች። ላለፉት ወራት በስራ መደራረብ ምክንያት ቀጣይነት ያለው ዝግጅት ማድረግ አልቻልንም በመሆኑም ልባዊ የሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። በቅርቡ Najafi 1...
12/12/2023

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች። ላለፉት ወራት በስራ መደራረብ ምክንያት ቀጣይነት ያለው ዝግጅት ማድረግ አልቻልንም በመሆኑም ልባዊ የሆነ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። በቅርቡ Najafi 100 Million Learners Global Initiative የሚል ማስታወቂያ መልቀቃችን ይታወቃል ይሁንና ብዙዎቻችሁ ስልጠናዎቹን ለመከታተል ፍላጎት አሳይታችሁ ስለአጠቃላይ ሁኔታ ግልጽ እንዳልሆነላችሁ በተለያየ መንገድ ለመረዳት ችለናል። ስለሆነም ስለ ስልጠናው እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር መወያየት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ስለ ጉዳዩ የወሎ ዩንቨርስቲ መምህራኖች እንዲሁም Najafi 100 Million Learners Global Initiative የኢትዮጵያ ኮሜቴ ከሆኑት መ/ር ውብሸት ደግፌ እንዲሁም መ/ር ሰይድ ሽፈራው ጋር ታህሳስ 3/2016 ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በቀጥታ እንፑርሻ ቴሌግራም ቻናል ላይ ውይይት እናደርጋለን። ዝግጅቱን በቀጥታ ለመከታተል እንዲሁም ስለ ስልጠናው የተለያዩ ጥያቄዎች መጠየቅ የምትፈልጉ ከስር ባለው የቴሌግራም ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቤተሰባችን ሆናችሁ ዝግጅቱን በቀጥታ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/xonsopursha

ሰላም ሰላም  #እንፑርሻ ቤተሰቦች  #ተመልሰናል። በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን የጫረው ከተጋቡ ከ14 ዓመት በኋላ ልጅ የወለዱትን ጥንዶችች አቶ ኩሻቦ እና ባለቤቱ ወይዘሮ ኮዪቴ ዓርብ ከምሽቱ ...
16/08/2023

ሰላም ሰላም #እንፑርሻ ቤተሰቦች #ተመልሰናል። በብዙዎች ዘንድ አግራሞትን የጫረው ከተጋቡ ከ14 ዓመት በኋላ ልጅ የወለዱትን ጥንዶችች አቶ ኩሻቦ እና ባለቤቱ ወይዘሮ ኮዪቴ ዓርብ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በቀጥታ የቴሌግራም ቻናላችን ላይ በመቅረብ ያለፉበትን የሕይወት ታሪክ የሚያጋሩን ይሆናል። ስለሆነም ይህንን አስደናቂ የህይወት ተሞክሮ ለመከታተል ከስር ባለው የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ በመጫን ቤተሰባችን ይሁኑ ለሌሎችም ያጋሩ።
👇👇👇👇👇👇👇
TELEGRAM https://t.me/xonsopursha
FACEBOOK https://www.facebook.com/profile.php?id=100081922881893
YOUTUBE https://youtube.com/channel/

20/07/2023

መስከረም 2014 ላይ የእንፑርሻ ስልጠና ስናሰለጥን ''እንደዚህ አይነት ስልጠና ከ16 ዓመት በፊት ብናገኝ ኖሮ እንዴት ያለ የተሻለ ነገር ማድረግ እንችል ነበር ነገር ግን አሁንም አጋጣሚዎች አሉን'' ነበር ያለችው የዛሬዋ የማስተርስ ምሩቅ እናታችን ታደለች በየነ። እንደተመኘሽው ሆኖልሻል በድጋሚ እንኳን ደስ ያለሽ!! እኛም እንደ እንፑርሻ ያሰብሽውን ፈጣሪ ረድቶሽ ስላሳካሺው በጣም ደስ ብሎናል። የዛሬ ሁለት ዓመት እናታችን ታዱ የተናገረችውን ከስር ባለው ቪዲዮ አያይዤላችኋለሁ።

17/07/2023

ሰላም ሰላም የእንፑርሻ ቤተሰቦች። ላለፉት ወራቶች ኢንተርኔት ያለ vpn አለመስራቱን ተከትሎ የቀጥታ ስርጭታችንን ማስተጓጎሉ የሚታወስ ነው። ዛሬ ግን ያለ vpn መስራት ስለጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የምናደርገውን የቀጥታ ስርጭት በቅርቡ በተሻለ አቀራረብ እና ዝግጅት ወደ እናንተ እንደምንቀርብ ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ 12ኛ ክፍል ለሚፈተኑ ተማሪዎቻችን መልካም ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
ከስር በሚገኘው ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/xonsopursha

እንፑርሻ ከኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመሆን ለካራት እና ለፋሻ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል። ተማሪዎች የሰለጠኑት ስልጠና ለብሄራዊ ፈተና መነሳሳት ...
27/05/2023

እንፑርሻ ከኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመሆን ለካራት እና ለፋሻ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል። ተማሪዎች የሰለጠኑት ስልጠና ለብሄራዊ ፈተና መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ሃሳባቸውን አጋርተውናል። በአጠቃላይ ወደ አንድ ሺህ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ማሰልጠን ችለናል በሁሉም ነገር መከናወን የሰጠንን አምላካችን እግዚአብሔርንን እናመሰግናለን። በመቀጠልም ፕሮግራሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ የተወጡት የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ፍሬዘር ኮርባይዶ፣
የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ኩሴ ጭሎ፣ የኮንሶ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ሃላፊ አቶ ገብረሃና ገቢኖ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አቶ አማኑኤል ሲዳም፣ የኮንሶ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ር/መር አቶ ማቲዎስ ጉማንቴ፣
ለኬና ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ካርሻዎ ካስቶ፣ ለፋሻ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ር/መር ፣ለመምህር አራርሶ ጎኚሻ
ልዩ ምስጋና ለዶክተር ሙላት በላይነህ እንዲሁም ስልጠናውን ስፖንሰር ያደረጉልን ግለሰብ።
join our telegram chanel https://t.me/xonsopursha

Address

Addis Ababa

Telephone

+251914900847

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Enpursha motivation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Enpursha motivation:

Share