ዓውደ-ኢትዮጵያ Awde Ethiopia

ዓውደ-ኢትዮጵያ Awde Ethiopia የሁሉም ኢትዮጵያውያን ታሪክ፣ ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት፣ ሰብዓዊነትና መፈቃቀድ በዓውደ-ኢትዮጵያ ይወሳል።

06/01/2024

የገና ጨዋታ
(በካህሳይ ገ/እግዚያብሄር)

የገና ጨዋታ በአገራችን መዘውተር የጀመረው ከጌታ ልደት በኋላ ጀምሮ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡ ጨዋታው በዚህ ዘመንና ዓ.ም ተጀመረ የሚል የጽሑፍ ማስረጃ ባይገኝም በጥንታውያን ገዳማት በሚገኙ የግድግዳና ብራና መጻሕፍት ከጌታ ልደት ሥዕል ጐን ሕፃናት የገና ጨዋታ ሲጫወቱ የሚያሳዩ ሥዕሎች መኖራቸው ሲታይ ጨዋታው በሺሕ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሲዘወተር ለመቆየቱ ተጨባጭ ማሳያ ነው፡፡

የገና ጨዋታ እንዴትና ለምን ተጀመረ ለሚለው ጥያቄ በትውፊታዊ ታሪኮች ላይ የተመሠረቱ ሁለት ምላሾች አሉ፡፡ አንደኛው የገና ጨዋታ በሰብአ ሰገል ሰራዊት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ በፊት በቤተልሔም ከተማና በአካባቢው የተለመደ ጨዋታ ነበር፤ የተለየ ነገር የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዕለት መልአኩ የምሥራቹን ለእረኞች ነግሯቸው የጌታን መወለድ በዓይናቸው ዓይተው፣ ከሰማይ መላእክት ጋር የሰላም መዝሙር ከዘመሩ በኋላ በደስታ የገና ጨዋታ ተጫውተዋል የሚለው ነው፡፡ ጌታችን የተወለደው ንጉሥ ባዜን ኢትዮጵያን ይገዛ በነበረበት ዘመን ነበር፡፡ በወቅቱ የጌታን ልደት የምሥራች በዓል ለመካፈል በኮከብ እየተመሩ ወደ ቤተልሄም ከሄዱት አንዱ የንጉሥ ባዜን ወንድም መለኸ እንደነበር ታውቋል፡፡

የገና አጨዋወት አጀማመርን በተመለከተ የሚቀርበው ሁለተኛው ትውፊታዊ ታሪክ ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡ በኮከብ (በቅዱስ ገብርኤል) መሪነት ወደ ቤተልሔም የተጓዙት ሦስት የምሥራቅ ነገሥታት እያንዳንዳቸው አንድ መቶ ሠራዊት አስከትለው ነበር የሄዱት፡፡ በወቅቱ ኢየሩሳሌምንና አካባቢውን ይገዛ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የእነዚህን ነገሥታት መምጣት በመረጃ ደርሶበት ነበርና እንቅስቃሴያቸውን ለመከታተል ይችል ዘንድ ከሰላዮቹ አንዱን የእነዚህ ነገሥታት ወታደሮች አስመስሎ ከመካከላቸው አስገባ፡፡ ይሁንና ሰላዩ ከሰብአ ሰገል ወታደሮች መካከል ሠርጎ እንደገባ ካሰቡበት ቦታ ሳይደርሱ ይመራቸው
የነበረው ኮከብ አልንቀሳቀስም ብሎ ቆመ፡፡ በዚህን ጊዜ ነገሥታቱ እስቲ ሁላችንም ሰዎቻችንን እንቆጣጠር ብለው ሲቆጣጠሩ ሰላዩ ተገኘና አንገቱ ተቀልቶ እንዲሞት ተደረገ፡፡ በዚህን ጊዜ ታድያ ወታደሮቹ የተቀላውን የሰላዩን ጭንቅላት በዱላ እየተቀባበሉ ይጫወቱበት ጀምር፡፡ ይህንን መነሻ
በማድረግ ከዛን ጊዜ ጀምሮ የገና ጨዋታ ተጀመረ፡፡

የገና ጨዋታ ሥርዓትና ባህል

የዛሬን አያድርገውና የመሬት ጥበት ባልነበረበት ጊዜ ለገና መጫወቻ ተብሎ በየመንደሩ ተከልሎ የሚቀመጥ ሜዳ ነበር፡፡ ይህ ሜዳ ከገና መጫወቻነቱ ባሻገር ለከብቶች የግጦሽ መስክ በመሆንም ያገልግላል፡፡ የገና መጫወቻ ሜዳ (መለጊያ) ስፋት ግን ውስን አይደለም፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ ሜዳ የራሱ የሆነ ወሰንና ድንበር አለው፡፡ ይህ መስመር ማለብ ይባላል፡፡ በመሆኑም በጨዋታ ጊዜ ዕሩርዋ ወይም ጥንግዋ የማለቡን መስመር አልፋ መውጣት የለባትም፡፡ ዕሩርና ጥንግ አገልግሎታቸው አንድ ዓይነት ቢሆንም አሠራራቸው ይለያያሉ፤

ሀ. ዕሩር በአብዛኛው ከክትክታ ሥር ከሚገኘው ጉጥ ተቆርጣና ተስተካክላ የምትዘጋጅ ናት፡፡ ሩርዋ በይበልጥ እንድትጠነክር ሲባል በእሳት እንድትለበለብ ይደረጋል፡፡ ዕሩር የሚለው ቃልም በእሳት ያረረ መሆኑን ለማሳየት የተነገረ ነው፡፡

ለ. ጥንግ በአንጻሩ ከበሬ ቆዳ (ጠፍር) በዚህ ሞያ ባላቸው ሰዎች የምትሠራ የገና ኳስ ናት፡፡ አንዳንዴ ዕሩርዋም ሰውን
እንዳትጎዳ ሲባል በቆዳ እንድትሸፈን ይደረጋል፡፡
ዕሩር ከተወሰኑ የዛፍ ዓይነቶች እንደምትዘጋጅ ሁሉ የመምቻ ዱላውም (ቀልባሳ በትር ከተመረጡ የዛፍ ዓይነቶች ነው የሚሰናዳው፡፡ (በነገራችን ላይ የገና መምቻ ዱላው ማጠንጊያ ወይም ጥርባዳ እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡)
ለጥርባዳ (ማጠንጊያ) ተመራጭ ከሆኑ የዛፍ ዓይነቶች መካከል ቀረጽ፣ አጣጥ፣ ብሳና፣ ጨባ በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከእነዚህ የዛፍ ዓይነቶች የሚገኝ ዱላ በክብደቱ ቀላል ነገር ግን ደግሞ በቀላሉ የማይሰበር ነው፡፡ ዱላው የዚህ ዓይነት መሆኑ በጨዋታ መካከል በስህተት በሰውነት ላይ ቢያርፍ የሚደርሰው ጉዳት አነስተኛ እንዲሆን ይረዳል፡፡ ይሁንና በአንዳንድ አካባቢዎች ለገና ዱላ የሚመረጡት የወይራና የክትክታ ዛፎች ናቸው፡፡ ከጨዋታ ጊዜ ውጭ ባለው ጊዜ ዕሩርዋ (ጥንግዋ) በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት እንድትቀመጥ ትደረጋለች፡፡

የገና ጨዋታ የሚከናወነው ከልደት እስከ ጥምቀት ባለው ጊዜ ነው፡፡ በበዓለ ልደት ከቅዳሴ በኋላ ዕሩርዋ ከተቀመጠችበት ቦታ ወጥታ በዕለቱ እንዲያጫውቱ ለተመረጡ የቡድን አባቶች (ዳኞች) ትሰጣለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የገና ጨዋታ የሚከናወነው በተለይ በመጀመሪያው ዕለት) ከሰዓት በኋላ ነው፡፡ ምክንያቱም ጠዋት ሰው ከቤተ ክርስቲያን መልስ ወደ የቤቱ በመሄድ ለበዓሉ የተዘጋጀውን ድግስ ከቤተሰቡና ከጎረቤት ጋር እየበላ እየጠጣ ስለሚያልፍ ነው፡፡
ወደ ጨዋታው ሂደት ስንመልስ ጨዋታውን መርቀው ዕሩርዋን (ጥንግዋ) ለግተው የሚያስጀምሩት ሁለት የቡድን አባቶች ናቸው፡፡ በዘመናዊ የእግር፣ የእጅና የቅርጫት ኳስ ጨዋታዎች ተፎካካሪ ቡድኖች የየራሳው የሆነ ቋሚ ስም ይኖራቸዋል፡፡ በአገራችን የገና ጨዋታ ሥርዓት ግን ሁለቱም ተፎካካሪ ቡድኖች መጠሪያ ስም የሚሰጣቸው ጨዋታው ሊጀመር ሲል ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ሁለት የቡድን አባቶች ከየቡድኑ አንዳንድ የቡድን መሪዎችን (አምበሎች) ይጠሩና ሁለት ስያሜዎችን በማቅረብ በፈቃደኝነት የየራሳቸው እንዲመርጡ ያደርጋሉ፡፡

በዚህ ስምምነት ከሌለ የቡድን አባቶች በዕጣ ስም ያወጡላቸዋል፡፡ በአመዛኙ በአገራችን ለገና ጨዋታ ለቡድን ስም መጠርያነት በአማራጭነት የሚቀርቡት ከአንበሳ ከነብር፣ ከእንጀራ ከጠላ፣ ከገደል ከሾተል የሚሉና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በጨዋታው ወቅት ተመልካቹ በልቶ ጠጥቶ የሚመጣ ቢሆንም ተጫዋቾቹ ግን ከጨዋታ በፊት በጣም በትንሹ መጥነው ነው የሚበሉት፡፡ ይህም እንደልባቸው መሮጥና መንቀሳቀስ ይችሉ ዘንድ ነው፡፡ ካልሆነ ግን እስኪጠግብ በልቶ መጥቶ መሮጥ አቅቶት የተሸነፈ ጊዜ አሸናፊው ወገን፡-

እየው አካሄዱን አረማመዱን፣
እንደ ቃሪያ ሎሚ ወጥሮ ሆዱን፡፡
ትናንት ማታ የበላው ሽልጦ፣
አላስሮጠው አለ ከጐኑ ተሸጦ፡፡
በማለት ይሳለቅበታል፡፡

ይቀጥላል .....

#ዓኢ

126ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ!
02/03/2022

126ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ!

18/12/2021

ግሩም ዘነበ የገብረ ክርስቶስ ደስታን "አገሬ" የተሰኘ ግጥም በተለያዩ መድረኮች ላይ አቅርቦታል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ማርሽ ባንድ ታጅቦ ሲከውነው ግን የመጀመሪያው ነው። ...

28/11/2021

ሀገር ማለት የእኔ ልጅ
(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣

እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ፣ የተወለድሽበት አፈር፤

እትብትሽ የተቀበረበት፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤

ብቻ እንዳይመስልሽ።

ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤

ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።

ሀገር ማለት ልጄ፣

ሀገር ማለት ምስል ነው፣ በህሊና የምታኖሪው፤

ከማማ ማህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ፤

በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ፣

በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤

በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣

በተሻገርሽው ዥረት፤

በተሳልሽበት ታቦት፣ ወይ በተማፀንሽው ከራማ፤

በእውቀትሽና በሕይወትሽ፣

በእውነትሽና በስሜትሽ፣

የምትቀበይው ምስል ነው፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤

ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው።

ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።

ሀገር ማለት የኔ ልጅ፣

ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤

በጆሮ አያዳምጡት፤

አማርኛ ኦሮሞኛ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤

ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት።

የኔ ልጅ፣

አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው፣ ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤

ያልገባሽው እንዳይመስልሽ፣ ኀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።

የየልቦናችንን ሐቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤

ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ።

ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤

ሲከፋሽ ትሸሸጊበት፣ ሲደላሽ ትኳኳዪበት።

የኔ ልጅ፣

አያት ቅም አያትሽ፣ ሠላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣

ሲያቀና ወረቱን፤

ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያደራጅ ቀዬና ቤቱን፤

ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤

ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ ... ከሁሉም የጦቢያ ልጆች፣

አጥንቱን እየማገረ፤

ሀገር ይሉት መግባቢያ፣ ሰንደቅ ይሉት መለያ፣ ሲያቆይልሽ፤

በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት ታሪክ አለልሽ!

የእኔ ልጅ፣

ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ የሚያስፈልግሽ፤

ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤

ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተወጠነው እድገትሽ።

እና ልብ በይ ልጄ!

ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበት አይናገሩት፤

በጆሮ አያዳምጡት።

ከሁሉም በላይ የእኔ ልጅ፣

ተፈጥሮ ከቸረው በረከት፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤

ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።

ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤

የሰብዕናሽ ግማሽ ውል፣ ወገን ነው ማሕተምሽ።

ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።

መሬትማ የእኔ ልጅ፣

መሬትማ

በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤

ለተስፋሽ ውጥን ካልሆነ፣ ለእድገትሽ ካልተመገብሽው፤

መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤

ለተስማማው የሚስማማ።

ዥረቱም ግድ የለውም፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል

ተራራውም ደንቆሮ ነው፣ ለቦረቦረው ይበሳል።

መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሀገርሽ፤

ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ አፈር ሚያለብስሽ።

በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤

ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።

እና የኔ ልጅ፣

ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤

ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።

(ታህሳስ 1999፣ ለልጃችን ኬርዓለም “ፍካት ናፋቂዎች” መድብል ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

#ዓኢ
#ኢትዮጵያ

26/11/2021

"ኢትዮጵያ- የአፍሪካ የነፃነት ምሽግ"

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውም ሃገር ላይ በእብሪት ወረራ አካሂዳ የማታውቅ ሲሆን በእብሪት ሊወሯት የመጡትን ጠላቶቿንም አሳፋሪ የሆነ ሽንፈትን እያከናነበች እዚህ ደርሳለች። በተለይም በጥቁር ህዝብ ታሪክ የነፃነት ተምሳሌት ተደርጋ እንድትወሰድ አድርጓታል። ይሄንንም የነፃነት ተምሳሌትነቷን በዶናልድ ሌቪን ተፅፎ በአቶ ሚሊዮን ነቅንቅ የተተረጎመው "ትልቋ ኢትዮጵያ የብዙ ነገዶች ማህበረሰብ" መፅሐፍ እንደሚከተለው ይተርከዋል

ጥንታውያን ኢትዮጵያን የሚያስቧት እንደ ኩሩና ነጻ ሀገር ነበር። ዲዎደረስ ስለኑቢያዊ ኢትዮጵያ ሲጽፍ እንዲህ ይላል።

"እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በባዕድ ንጉሥ ከቶ ተገዝተን አናውቅም በመካከላችን ሙሉ ሰላም ሰፍኖ ነጻ ሕዝቦች ሆነን ኖረናል ይላሉ ምንም እንኳ ብዙ ኃይለኞች ነገሥታት ቢወሯቸውም ሙከራቸው አልተሳካላቸውም። ካምቢስ ኃይለኛ ጦር ሠራዊት አስከትቶ በነርሱ ላይ መዝመቱ ለሱም ለራሱም ነፍስ መጥፋት ሆነ ለሠራዊቱም መደምሰስ አደገኛ ነበር። እንዲሁም በድል አድራጊነቷና በጦር ስልት እውቀቷ ዝነኛ የነበረችው ሰሚራሚስ ወደ ኢትዮጵያ ምድር ጥቂት ከገባች በኋላ ያን ሀገር ድል አድርጎ መያዝ መቅኖ እንደሌለው ወዲያው ተረዳችው።"

የኑቢያ ግዛት አዲሲቱ ኢትዮጵያ የሆነችው አክሱም እስክታወድማት ድረስ በኩራትና በነፃነት ትኖር ነበር። በአራተኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ላይ አክሱማውያን ወሳኙንና የመጨረሻውን ወረራ በኩሽ አካሂደው ዋና ከተማዋን ሜሮንን አጠፏት።
ስለዚህ አክሱማውያን ኢትዮጵያ የሚለውን ስም መጠሪያ ከማድረጋቸውም በላይ ነጻ ሀገር የመሆንንም ዝና በመጨረሻው ወረሱ። ስለዚህ ነው የ17ተኛው ምዕተ ዓመት የታሪክ ሊቅ የነበረው ፖርቱጋላዊ ሉዊስ ኡሬታ "ሐበሻ የሚለው ቃል ትርጉም (በዐረብኛ በቱርክና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች) የባዕድ ንጉሥ ግዛት የማታውቅ ነጻና ራስ ገዝ ማለት ነው ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገርም ልክ እንደምነግራችሁ ነች" እያለ የሚገልጸው።

በ19ኛው ምዕተ ዓመት መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉር የነፃነት ምሽግ የመሆኗ ሥዕለ በተለይ እየተስፋፋ ሄደ። የአፍሪካ ሀገሮች በመላው በባዕድ ኃያላን ቀንበር ስር እየወደቁ በሚሔዱበት ወቅት ኢትዮጵያውያን ተከታትሎ የመጣባቸውን ወረራ ሁሉ ድል በመንሳት ነበሩ። በ1870 ገደማ የግብፅን ወራሪ ጦር በ1880 ገደማ የመሀዲዎችን ወራሪ ጦር በ1890 ገደማ ደግሞ የኢጣልያንን ወራሪ ጦር ድል በመንሳታቸው ኢትዮጵያውያን ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር በመቁረጣቸው ኃይለኞች ተዋጊዎች ናቸው የሚል ዝና አገኙ። ኢትዮጵያ የዓለምን እውቅና ያተረፈችው የአውሮፓም መንግሥታት በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ የዲፕሎማቲክ መልዕክተኞች ለማቋቋም የተሽቀዳደሙት ከዚህ በላይ በመጨረሻው በተነገረው ድል በዓድዋ ላይ በ1888 በተገኘው የጦር ድል ነው። በዓድዋ ላይ የኢጣልያ መሸነፍ አሥር ዓመታት ያህል የፈጀ የውልና ስምምነት ድርድር ከአውሮፓ ኃያላን ጋር ሲደረግ ቆይቶ ዘጠኝ የድንበር ውሎች ተፈርመዋል።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አፍሪካውያንና የአሜሪካ ጥቁሮች ሳይቀሩ የነጻይቱን ኢትዮጵያ ሥዕለ ኅሊና ያወድሱ ጀመር። በ1892 ላይ የደቡብ አፍሪካ የባንቱ የክርስትና መሪዎች ከአውሮፓውያን የሃይማኖት ሥልጣን ስር ለመለየት ሲፈልጉ "የኢትዮጵያ ቤተ ክርሰቲያን" ብለው የሰየሙት ነጻ የሆነ የደቡብ አፍሪካ የምዕመናን ቤተ ፀሎት አቋቋሙ። "ኢትዮጵያ" የሚለው ስያሜ ስረ ትርጉሙ መላውን የአፍሪካ ጥቁሮች ያጠቃለለበትን ምክንያት የአፍሪካውያንን በክርስትና ሃይማኖት መጠመቅ በመተንበይ በመዝሙረ ዳዊትና በሐዋርያት ስራ ተጠቅሶ ስለሚገኝ ነው። በኋላ ግን (በደቡብ አፍሪካ) "የኢትዮጵያ ቤተ ክርሰቲያን" ንቅናቄ መሪዎች ነጻው ቤተክርስቲያናቸው ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሐዋርያት ሥራ የተገኘ ከመሆኑም በላይ በእውን ነጻ ከሆነው ከአፍሪካዊ የክርስቲያን ንጉሥ ግዛት ጋር የተዛመደ ነው ብለው ተረጎሙት።

በደቡብ አፍሪካ "የኢትዮጵያ ንቅናቄ" የተባለው ድርጅት ገና ለጋ በነበረበት ጊዜ ዓድዋ ላይ የተገኘው ድል የደቡብ አፍሪካን ጥቁሮች ኃይል አንቀሳቅሶት ነበር። ጄምስ ደዋኔ የተባለ ከዋናዎቹ መሪዎች አንዱ ለአጼ ምኒልክ ደብዳቤ ጽፎ በግብፅና በሱዳን ስለሚገኙት የአፍሪካ ክርስቲያኖች ጉዳይና ሁናቴ ጠባቂ እንዲሆኗቸው ከመጠየቁም በላይ ይህንኑ ጉዳይ በመደገፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ሞክሮ እንደነበር መፅሀፉ ይገልፃል።

(ማስታወሻ፡ ከዚህ ፅሁፍ ጋር ለመግለጫ የተጠቀምነው ምስል በተመለከተ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያን ታሪክ እየተረክን የአሁን ዘመንን የሀገራችንን ካርታ መጠቀሙ የመልክቱን ይዘት ያዛባል ብለን በማሰብ ከኤርትራ ጋር ባንድነት ያለንበትን ከ1983 ዓ. ም በፊት የነበረውን ምስል ተጠቅመናል፡፡)

#ዓኢ
#ኢትዮጵያ

13/11/2021
25/09/2021

ዮዮ ግፋታ!

የዎላይታ ጊዜ አቆጣጠር በጨረቃና በፀሐይ የሚሰላ እንደሆነ ጥናቶች ቢጠቁሙም ከጥንት ጀምሮ በጨረቃ እንደሚቆጠር ብዙ ምንጮች ይጠቁማሉ፣ ግፋታ ደግሞ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ነው። ግፋታ የመጀመሪያ አዲስ አመት ወር ነው። ግፋታ በዎላይታ ብሄር አቆጣጠር መሠረት የሚከበረው ከመስከረም 14- 20 በሚውለው ዕሁድ ይሆናል።

ዛሬ ቅዳሜ ባጪራ ቄራ ይባላል፤ ነገ ዕሁድ ሹሃ ዎጋ ይባላል (የአዲስ አመት የመጀመሪያ ቀን)።

እንኳን አደረሳችሁ።

Via Wolaita Times

10/07/2021

ስለ ታላቋ የድሆች እናት አበበች ጎበና ህልፈት አልተቆጫችሁም? ምነው ትንሽ ዘመን በጨመሩ ብላችሁ አልተመኛችሁም? እሳቸው የድርሻቸውን ተወጥተው አልፈዋል ተራው የእኛ ነው፡፡ የእጃችንን እንሰንዝር፤ የዛሬዎቹ አበበች ጎበና እኔና እናንተ ነንና፡፡ አንዷ እናት በአምሳያቸው ብዙ እንዳፈሩ ነፍሳቸው ታይ ዘንድ፤ ዛሬ ከቤታችሁ ወደየጉዳያችሁ ስትወጡ የማትጠቀሙባቸውን አልባሳትና ጫማዎች ይዛችሁ ውጡና ከታች ከተቀመጡት መቀበያዎች የሚመቻችሁ ጋር አስቀምጡልን።

ሸራውንም እየገዛችሁ አቀብሉን። ሸራውን ለመግዛት ጊዜ የለንም ያላችሁ ደግሞ
Jemal abdella hussen
1000009738208
Commercial bank of Ethiopia ብላችሁ ገቢ ብታደርጉ እንደእናንተ ሆነን ገዝተን እናደርሳለን።

1. ፒያሳ ሶማሌ ተራ ቤቶ ህንፃ ቁጥር- 416
ስልክ 0912 604555
2. ዘነበወርቅ ዘነበወርቅ ሞባይል ሴንተር
ስልክ +251901472050
3. ቦሌ ደንበል አካባቢ ቢትወደድ ባህሩ ህንፃ የፅህፈት መሳሪያ
ስልክ 0913 776060
4. አየር ጤና ንብ ባንክ ጀርባ የህፃናት አልባሳት መሸጫ
ስልክ 0939 657972
5. ገርጂ መብራት ኃይል አንበሣ ጋራዥ ቶቶት አጠገብ 251 Foods Catering
ስልክ 0972202020/ 0975106690
6. ስቴድየም አካባቢ አን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ሴንተር አዳም የወንዶች የውበት ቤት Adam Barber
ስልክ +251 91 010 1572
7. ቦሌ DH geda ታወር Winta Mehari
ስልክ 0912455339
8. ሜክሲኮ Mexico Book Corner ኤልያስ
ስልክ 09193 70881
9. ልደታ Marta Mengistu
ስልክ 0920680045
10. መሳለሚያ Rahel Mengistu
ስልክ +251 93 421 5237
11. መገናኛ ሳላም ታወር
ስልክ 0913796808 Emni Ye Zewdu እምነት
12. አያት ሎሚያድ ሱፐርማርኬት ፊትለፊት ጥሩ ሽሮ 90's ካፌ ያለበት ህንፃ ግራውንድ ላይ
ስልክ 0960047087 ፍቅር አሜን ኤልሻዳይ
13. ቦሌ ሚካኤል የቡልቡላ ማሪያም ታክሲ መያዣው ጋር ወይም ቴዲ ባር
ስልክ 0911 676851 Binyam Teshome
14. 6killo ቅ.ማርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ግቢ ውስጥ የሱቅ ቁጥር 14/04/ Dewol stationary
እና ሚኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ ሳንፎርድ ት/ቤት ፊት ለፊት
ስልክ 0923622539 ታምር
15. መገናኛ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ ታረቀኝ ቁርጥ ገባ ብል ዳኪ ሬስቶራንት
ስልክ 0911137378 Marcon Ermiyas
16. 22 አካባቢ ባታ ኮምፕሌክስ ግራውድ ላይ ወይም አቤል ሲኒማ የሚገኝበት ህንጻ
ስልክ 09 38 38 31 37 ውዳሴ ከፍይበሉ
17. መርካቶ ምዕራብ ሆቴል አካባቢ ጃቡላኒ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ 0911 111253
18. አራትኪሎ አካባቢ
ስልክ 0913648552 ቅድስት
19. ቤተል ጃካራንዳ አካባቢ
ስልክ 0910682332 Dere Gebrezena ደረጄ
20. ወሠን፣ ኮተቤ አካባቢ
ስልክ 0913627502 Genet Meaza ገነት
21. ቢ ሜዳ ኮንደሚኒየም ለቂርቆስና ቄራ አካባቢ
ስልክ 09 11 16 62 11 የውብዳር
22. ለጎፋና አካባቢው
ስልክ +251944744034 Hanna Getachew
23. ሽሮ ሜዳ አካባቢ ዞላ ምባይል
ስልክ 0912371755 እያሱ
24. ሰሜን ማዘጋጃ ላዛሪስት
ስልክ 0912371755 እያሱ
25. ጎተራና አካባቢው
ስልክ +251935608815 Wasyhune Getachew

ጥያቄ፣ ሃሳብ፣ አስተያየት እንቀበላለን። ከእናንተ የሚጠበቀው
በ+251912 604555 ወይም +251913670905 ላይ መደወል ወይም ሰለሞን መንገሻ ወይም Kiram Kebede በውስጥ ማውራት ብቻ ነው።





ሼር በማድረግ ለብዙ ሰው እናዳርስ!!!

Address

Addis Ababa

Telephone

+251945906262

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዓውደ-ኢትዮጵያ Awde Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ዓውደ-ኢትዮጵያ Awde Ethiopia:

Share