05/11/2025
ዞህራን የኒው ዮርክ ከንቲባ እንዲሆን ንቅናቄ ያደረጉ እና ድምጽ የሰጡ ነዋሪዎችንም በንግግሩ ሳይጠቅስ አላለፈም። "የመናውያን የመደብር ባለቤቶች፣ ሴኔጋላውያን የታክሲ ሹፌሮች፣ ኡዝቤክስታናውያን ነርሶች እና ኢትዮጵያውያን 'አክስቶች' " ሲል ድጋፍ የሰጡትን ዘርዝሯል። ዞህራን ባደረገው የ30 ደቂቃ ንግግር "በዚህ ጨለማ የፖለቲካ ዘመን ኒው ዮርክ ብርሃን ትሆናለች" ብሏል። "ዶናልድ ትራምፕ [ንግግሬን] እየተመለከትክ እንደሆነ አውቃለሁ። አራት ቃላት ልናገር እፈልጋለሁ። ድምጹን ከፍ አድርገው። እኛ ጋር ለመድረስ ሁላችንንም ማለፍ አለብህ" ሲልም ዞህራን ተናግሯል።
https://bbc.in/3WETmCg