13/08/2026
🐎 በኢትዮጵያ የፈረሶች ደህንነት (Horse Welfare)!!!
በኢትዮጵያ ፈረሶች ለመጓጓዣ፣ የጭነት ስራ፣ ግብርና እና የቤተሰብ ገቢ ማስገኛ አስፈላጊ ሚና ይጫወታሉ። ነገር ግን ብዙ የስራ ፈረሶች የተሟላ እንክብካቤ አያገኙም።
1. 🐴 ከመጠን በላይ ማሰራት
ለረጅም ሰዓት ያለበቂ ዕረፍት ማሰራት ታመው፣ ቆስለው ወይም እግራቸው ተጎድቶ እንኳን ማሰራት ከፈረሱ አቅም በላይ ከባድ ጭነት መጫን
2. 🪢 ተገቢ ያልሆነ ማሰሪያና ጋሪ
የማሰሪያ መሳሪያዎች በትክክል ካልተገጠሙ፦ በአንገትና በደረት ላይ ቁስል ሊፈጥሩ ይችላሉ የቆዳ ጉዳትና ህመም ያስከትላሉ የፈረሱንም የመንቀሳቀስ ችሎታ ይቀንሳሉ።
3. 🌾 በቂ ምግብና ውሃ አለመኖር
የስራ ፈረስ ከማይሰራ ፈረስ የበለጠ ኃይል ይፈልጋል። ስለዚህ፦ በቂ ምግብ፣ ንጹህ ውሃ፣ ተገቢ የማዕድንና የቫይታሚን አቅርቦት እና በቂ የእረፍት ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል።
4. 🩺 በሽታና ጉዳት
በስራ ፈረሶች ላይ የሚታዩ ችግሮች ውስጥ የእግር አካል ችግርና አንካሳነት ፣ቁስል ፣የቆዳ በሽታ ፣የጥገኛ ተዋስያን ችግር፣ የመተንፈሻ ችግር እና Epizootic Lymphangitis (EZL) ይገኙበታል።
5. 👨⚕️ የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት እጥረት
በተለይ በገጠር አካባቢ የሚገኙ የፈረስ ባለቤቶች በቀላሉ የእንስሳት ሐኪም ማግኘት ላይ ችግር ሊኖርባቸው ይችላል። ቀላል የሚታከም ቁስልም በሕክምና እጥረት ወደ ከባድ ችግር ሊለወጥ ይችላል።
የፈረስ ደህንነት ማለት ፈረሱ ከረሃብ፣ ከጥማት፣ ከህመም፣ ከጉዳት፣ ከፍርሃትና ከአላስፈላጊ ስቃይ ነፃ ሆኖ በተፈጥሮው መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት መቻሉ ነው። የፈረስ ደህንነትን ማሻሻል ማለት ፈረሱን ብቻ መርዳት አይደለም፤ ከፈረሱ ጋር የሚኖረውን የባለቤቱን ኑሮና ገቢም መጠበቅ ነው።
ዶክተር አልዓዛር አየለ የዉቤ ልጅ
ከተማሪነት በላይ ለለውጥ