Ethiopian community association in Victoria

Ethiopian community association in Victoria ድር ቢያብር አንበሳ ያስር።
Bridging the gap through active engagement.
(1)

የወጣት ማርቆስ ጆርጅ ሲድረዲስ (የእህታችን መስከረም ታደሰ ልጅ) ቀብር ተፈጸመነፍስ ይማርMarcus George Sidreidis, the son of our dear sister Meskerem Ta...
18/06/2026

የወጣት ማርቆስ ጆርጅ ሲድረዲስ (የእህታችን መስከረም ታደሰ ልጅ) ቀብር ተፈጸመ
ነፍስ ይማር

Marcus George Sidreidis, the son of our dear sister Meskerem Tadesse, funeral service.
Farewell! Too young to die.
Rest in eternal peace

The European Centre for Law and Justice (ECLJ) has released a detailed report documenting the massacre of Orthodox Chris...
17/06/2026

The European Centre for Law and Justice (ECLJ) has released a detailed report documenting the massacre of Orthodox Christians in East Arsi, outlining patterns of targeted violence, the failure of local authorities to protect civilians, and the urgent humanitarian implications of the attacks.

The report calls on the United Nations Office on Genocide Prevention and the Responsibility to Protect (OSAPG, https://www.un.org/en/genocide-prevention) to investigate the situation, assess the risk factors for mass atrocity crimes, and take immediate preventive measures in line with its mandate. It urges the international community to ensure accountability, protect vulnerable populations, and support mechanisms that can prevent further escalation.

Embassy of Ethiopia, Canberra
Australian Embassy, Ethiopia
Ethiopian Human Rights Commission
Ethiopian Human Rights Council
Ethiopian Civil Society Organizations Council
Human Rights Watch
Amnesty International
SBS Amharic
BBC News Amharic
DW Amharic

At least 37 Orthodox Christians were killed and churches burned during coordinated attacks in Ethiopia's East Arsi Zone between 30 May and 1 June 2026.

17/06/2026

In 615 CE (BC), the first Hijra led early Muslims from Mecca to Aksum, Ethiopia, where they were welcomed and protected by Al‑Najashi. A timeless reminder of Ethiopia’s role in safeguarding people of all faith.

Happy 1448 Hijra to all who are celebrating. May the new year bring peace and blessings.

Victorian Multicultural Commission
Ethnic Communities' Council of Victoria

ይህንን የምታሟይ እህታችን ባል ተገኝቶልሻል (ካልተቀደምሽ)የሚስት ፈላጊው ዝርዝር • እውነተኛ ስም: ስማርት (Smart)• የመኖሪያ አድራሻ: ሜልበርን አውስትራሊያ• ሀይማኖት: እንዴት እንደ...
16/06/2026

ይህንን የምታሟይ እህታችን ባል ተገኝቶልሻል (ካልተቀደምሽ)

የሚስት ፈላጊው ዝርዝር
• እውነተኛ ስም: ስማርት (Smart)
• የመኖሪያ አድራሻ: ሜልበርን አውስትራሊያ
• ሀይማኖት: እንዴት እንደሆነ አላውቅም ፕሮቴስታንት ነኝ ነገርግን ኦርቶዶክስን አልቃወምም
• እድሜ: ይቅር አልናገርም
• ቁመት: 178 ሴሜ
• ከዚህ በፊት የነበረ ትዳር/ልጅ: የለም
• በትርፍ ጊዜ ምን ታደርጋለህ? ቤት ውስጥ ቁጭ ማለት፣ ዋና፣ ስቲም፣ ሳውና፣ ሲኒማ፣ ባህር ዳርቻ መንጎራደድ

ተፈላጊዋ ሚስት
• ሀይማኖት: የክርስትና እምነት ተከታይ
• እድሜ: 28 - 35 አመት
• የመኖሪያ አድራሻ: በመላው አለም ያለች
• የሰውነት ሁኔታ: ቀጠን ብላ መካከለኛ እና እራሷን የምትጠብቅ
• ቁመቷ: እርጅም ወይም መካከለኛ
• ካሁን በፊት ያላገባች ወይም ልጅ የሌላት
• ከሴት የማትቀበለው ምንድን ነው? ደግ ያልሆነች፣ ጥሩ ሰው ያልሆነች፣ ልቧ ጥሩ ያልሆነ፣ መርዛማ የሆነች፣ አምሽቸ ብመጣ የምትቆጣ፣ ቀና ያልሆነች፣ ሰላም የማትስጥ

ሙሉ መረጃውን ቪድዮው ላይ ማግኝት ይቻላል።

የዓለም የአረጋውያን ጥቃት ግንዛቤ ቀን - ጁን 15የአረጋውያን ጥቃት ከምናስበው በላይ አዘውትሮ ይከሰታል። በዚህ ቀን በማህበረሰባችን ውስጥ የአረጋውያንን ክብር እና ደህንነት ለመጠበቅ አንድ...
15/06/2026

የዓለም የአረጋውያን ጥቃት ግንዛቤ ቀን - ጁን 15

የአረጋውያን ጥቃት ከምናስበው በላይ አዘውትሮ ይከሰታል። በዚህ ቀን በማህበረሰባችን ውስጥ የአረጋውያንን ክብር እና ደህንነት ለመጠበቅ አንድ ላይ መቆም አለብን።

የአረጋውያን ጥቃት ምንድን ነው? የገንዘብ፣ የስሜት፣ የስነልቦና፣ የአካል፣ የወሲብ ወይም ማህበራዊ ሊሆን ይችላል።

ይህንን ጥቃት የሚያደርሰው ማነው? አብዛኛዎቹ ጉስቁልናዎች በቤተሰብ ውስጥ ይከሰታሉ። 88 በመቶ የሚሆኑት አጎሳቋዮች የቤተሰብ አባላት ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት የተጎሳቋዮች አዋቂ ልጆች ናቸው።

በአብዛኛው ይህ ጥቃት የሚደርስበት በማን ላይ ነው? እርዳታ ከሚፈልጉት ሰዎች ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት እንግሊዘኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆኑ ወይም ዘራቸው ከአውስትራሊያ ቀደምት ነዋሪ ህዝቦች የሚመዘዝ ሴቶች ናቸው።

እድሜያቸው ከ65 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ ሰዎች ውስጥ ከስድስት ሰዎች አንዱ በየዓመቱ አንድ ዓይነት የአረጋውያን ጥቃት ይደርስባቸዋል።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው እርዳታ የሚፈልግ ከሆነ፣ የአረጋውያን መብቶች ቪክቶሪያ (Seniors Rights Victoria) ነፃ እና ሚስጥራዊ የህግ ምክር እና ድጋፍ ይሰጣል። እነሱን ለማግኝት ወደ 📞 1300 368 821 ይደውሉ ወይም ድረ ገጻቸውን ይጎብኙ 🌐 www.seniorsrights.org.au

አረጋውያንን በአክብሮት፣ በእንክብካቤ እና በተግባር እንጠብቅ።

World Elder Abuse Awareness Day – June 15

Elder abuse happens more often than we think. Today we stand together to protect the dignity and safety of older people in our community.

What is elder abuse? It can be financial, emotional, psychological, physical, sexual or social.

Who commits it? Most cases happen within families.
88 percent of abusers are family members out of which 70 percent are adult children.

Who is most affected? Two thirds of people seeking help are women from CALD, Aboriginal and Torres Strait Islander communities.

One in six people aged 65 and over will experience some form of elder abuse each year.

If you or someone you know needs help, Seniors Rights Victoria offers free and confidential legal advice and support.

📞 1300 368 821
🌐 www.seniorsrights.org.au

Let us protect our elders with respect, care and action.

COTA Victoria & Seniors Rights Victoria

ሙሉ ክፍያ ለሚከፍሉ ተጏዧች (full fare) ከጁን 14 2026 ጀምሮ በሁሉም ባቡሮች ላይ ከማይኪ (myki) በተጨማሪ በባንክ ካርድዎ (Visa or Mastercard), በስልክዎ ወይም በ...
14/06/2026

ሙሉ ክፍያ ለሚከፍሉ ተጏዧች (full fare) ከጁን 14 2026 ጀምሮ በሁሉም ባቡሮች ላይ ከማይኪ (myki) በተጨማሪ በባንክ ካርድዎ (Visa or Mastercard), በስልክዎ ወይም በሰአትዎ (smartwatch) መክፈል ይችላሉ።

በጉዞዎ ላይ በዘርዎ ምክንያት ማንኛውም አይነት ጥቃት ከደረሰብዎ ወይም ሌሎች ላይ ሲደርስ ካዮ ወደ 0499 455 455 መልእክት ይላኩ

ይህ እንዴት እንደሚሰራ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ይሚከተለውን ድረ ገጽ ይጎብኙ

Transport Victoria

ማሳሰቢያ ከቤተክርስትያን ወደ ቀብር ስፍራው ወስዶ የሚመልስ አውቶብስ ተዘጋጅቷል።የወጣት ማርቆስ ጆርጅ ሲዴሪዲስ (04/04/2006 - 18/05/2026)የቀብር ሥነ-ሥርዓት ቀን: አርብ ሰኔ ...
14/06/2026

ማሳሰቢያ ከቤተክርስትያን ወደ ቀብር ስፍራው ወስዶ የሚመልስ አውቶብስ ተዘጋጅቷል።

የወጣት ማርቆስ ጆርጅ ሲዴሪዲስ (04/04/2006 - 18/05/2026)
የቀብር ሥነ-ሥርዓት
ቀን: አርብ ሰኔ 12 2018 (ጁን 19 2026)

የጸሎት እና ማስታወሻ ሥነ-ሥርዓት
በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን
አድራሻ: 7-9 Navigator Street, Maribyrnong, 3023, VIC
ሰአት: ከ9:00 ኤኤም ጀምሮ

የቀብር ስፍራ Springvale Botanical Cemetery
አድራሻ: Sloan Garden - Springvale Botanical Cemetery, Springvale, 3171, VIC
ሰአት: ከ11:30 ኤኤም - 12:30 ፒኤም

ከቀርብ በኋላ የነብስ ይማር ምሳ
አድራሻ: 5 Bakers Road, Oakleigh South, 3167, VIC

መጭውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ስፖንሰር ማድረግ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ Be Part of Ethiopian New Year 2019 – Sponsorship Opportunities N...
13/06/2026

መጭውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ስፖንሰር ማድረግ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ

Be Part of Ethiopian New Year 2019 – Sponsorship Opportunities Now Open

መጭውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሁለት ዝግጅቶችን እያዘጋጀን እንገኛለን። የመጀመሪያው ሴፕቴምበር 05, 2026 (Footscray) ሲሆን ሁለተኛው ሴፕቴምበር 19, 2026 (Kensington town hall) ይሆናል። እነዚህን ዝግጅቶች በተመለከተ የሚከተሉትን ጥሪዎች ማስተላለፍ እንፈልጋለን
1. ይህንን ዝግጅት በሀሳብ እና በጉልበት ማገዝ የምትፈልጉ/የምትችሉ ወገኖቻችን
2. ምርት እና አገልግሎታቹህን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ ወይንም ስፓንሰር ማድረግ የሚችል ድርጅት/አካል የምታውቁ ከሆነ
ወደ 0414 467 766 ይደውሉልን ወይንም [email protected] ላይ ኢሜይል ያድርጉልን።

To celebrate the upcoming Ethiopian New Year, we are organising two distinct events. The first one will be held on September 05, 2026, in Footscray, and the second event will be held on September 19, 2026, at Kensington Town Hall.

Please call 0414 467 766 or send an email to [email protected]
1. If you would like to volunteer in organising these events,
2. If you want to advertise your services or products, please contact us using the above details.

The Victorian Electoral Commission
LanguageLoop
MasterRemit
Cohealth
Bunnings Warehouse Australia
Coles
Woolworths
AMES Australia

ቪክቶሪያ ፓሊስ አመታዊውን በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ቅቡልነት ለማወቅ የሚያስችለውን የዳሰሳ ጥናት እያካሄደ ነው።የዳሰሳ ጥናቱ የቪክቶሪያ ፖሊስ ማህበረሰቡ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እንዲ...
12/06/2026

ቪክቶሪያ ፓሊስ አመታዊውን በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ቅቡልነት ለማወቅ የሚያስችለውን የዳሰሳ ጥናት እያካሄደ ነው።

የዳሰሳ ጥናቱ የቪክቶሪያ ፖሊስ ማህበረሰቡ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እንዲረዳ፣ አዝማሚያዎችን በጊዜ ሂደት እንዲከታተል እና ቪክቶሪያ ውስጥ የፖሊስ አገልግሎቶችን እንዲያሻሽል ግብአቶችን ለመሰብሰብ ያግዘዋል።

ይህንን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ከፈለጉ የሚክተለውን ማስፈንጠሪያ ጠቅ ያድርጉት https://engage.vic.gov.au/project/vicpol-2026/survey/6585 -nav

Victorians are invited to participate in the 2026 Victoria Police Community Sentiment Survey.

The survey helps the Victoria Police understand community priorities, track trends over time, and improve policing services across the state.

Access the survey here: https://engage.vic.gov.au/project/vicpol-2026/survey/6585 -nav

Eyewatch - Wyndham Police Service Area
Eyewatch - Moonee Valley Police Service Area

As part of the Neighbourhood Policing Framework, Victoria Police is...

Address

21 Yardley Street Maidstone
Melbourne, VIC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian community association in Victoria posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian community association in Victoria:

Share