25/03/2025
አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው
ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው
ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)
ከልጅነት የተሸከመኝ
እስከሽምግልና የሚመራኝ
አሳዳጊ ይህ ወላጅ የሆነኝ
ያለእርሱ ወገን ማነው ያለኝ
አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው
ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው
ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)
ቢከፋኝ ቢደላኝ እርሱ ነው
ሁልጊዜ ከጐኔ ማገኘው
ከእናት ከአባት በላይ ወዳጄ
ኢየሱስ ነው ተቆርቋሪ ለእኔ
አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው
ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው
ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)
እግሬን ከጨለማ መልሷል
በፍቅሩ ገመድ ውስጤን አስሯል
ልዩ ነው ልዩ ነው ለእኔ
በፍቅሩ ተማርካለች ነፍሴ
አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው
ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው
ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)
ሕያው ነው ምንም አያረጅም
ዘመን ሲያልፍ እርሱ አይለወጥም
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው
ታማኝነቱ ለእኔ ብዙ ነው
አዝ፦ የእኔ ጌታ/የእኔ ወዳጅ ኢየሱስ ነው
ግዙፉን ቀንበሬን የሰበረው
ከእርሱ በቀር ሌላ አላውቅም
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)
በጣም ተዋደናል አንለያይም (፪x)