የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ Wag Development Association /WDA/

  • Home
  • የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ Wag Development Association /WDA/

የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ Wag Development Association /WDA/ Wag Development Association (WaDA) is a developmental, non-profit, non-political and charitable organization which is found in Amhara region.

ዋግ ኽምራ ዞን፥ የረዥም ጊዜ ታሪክ ባለቤት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ወደ ኋላ ከቀሩ የአገራችን ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ ጤና እና ትምህርትን በመሳሰሉ መሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች ሳይቀር በጣም አነስተኛ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይህን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር የተለያዩ አካላት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ቢሆንም የዋግ ተወላጆችን ጥረት ግን ሙሉ በሙሉ ሊተኩ አይችሉም። በመሆኑም ይህን መጥፎ እውነታ ለመቀየር በሚደረገው ጥረት የዞኑ ተወላጆች አቅማቸው በፈቀደው ልክ እንዲሳተፉ ለማድረግና ይህንንም ተሳትፏቸውን ለማስተባበር የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) ተቋቁሟል። የማህበሩ ዋና ዓላማም በተወላጆቹ የተቀናጀ ጥረት በማንኛውም መልኩ የተሻለችና መሰረታዊ የማህበራዊ አገልግሎቶች ብርቅ የማይሆኑባት ዋግ ኽምራን መፍጠር ነው።

የቅጥር ማስታወቂያ
16/04/2026

የቅጥር ማስታወቂያ

የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ሀይሌ ወልዴ ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት...
10/04/2026

የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ሀይሌ ወልዴ ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

=======///=======
ሰቆጣ፣ ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (WDA Communication) የተከበራችሁ የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) የስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ ሰራኞች፤ የልማት ማህሩ አባላት፤ ደጋፊዎች፤ የልማት ማህራችን አጋሮች፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ!! እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል፡ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፤ ብዓሉ የሰላም፤ የጤና ፤ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆን በራሴ እና በልማት ማህበሩ ስም መልካም ምኞቴ ነው ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

እንደሚታወቀው የትንሳዔ በዓልን ስናከብር ያለው ከሌለው የምንረዳዳበት ፤በሀቅማቸው የተቸገሩ ሰዎችን የምንጠይቅበት ፤ጎረቤት ከጎረቤት የሚጠያየቅበት እና ጨዋ የሆነ የመረዳዳት የመጠያየቅና የመተሳሰብ እሴቶቻችንን ለማዳበር በዓሉን በጋራ ማሳለፍ ይኖርብናል ብለዋል ።

#!!በድጋሜ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፡፡ መልካም በዓል!!
"ህብረት ለዋግ ልማት"
።"በመተባበርር ዋግን እናልማ"
#በታደሰ በላይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

የዋግ  ልማት  ማህበር  /ዋልማ/  CDA  ፕሮጀክት  ለባለድርሻ   አካላት  የቅድመ  1ኛ ደረጃ   ት/ቤትን  አስጎበኘ ።----------------////////-----------------...
24/03/2026

የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ CDA ፕሮጀክት ለባለድርሻ አካላት የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤትን አስጎበኘ ።
----------------////////-----------------
ሰቆጣ 15/07/2018ዓ.ም /WDA communication/ በዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ አሰፈፃሚነት እየተተገበረ የሚገኝውን የቅድመ አንደኛ ህፃናት ትምህርት ፕሮግራም የትምህርት አሰጣጥ ሂደት በሰቆጣ ከተማ የሚገኝውን የሌትራል ጀኔራል ሀይሉ ከበደ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

በመስክ ጉብኝቱ የተሳተፉት አካላት:-የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ም/አስተዳደሪና የኢንበስትመንት መምሪያ ሃላፊ፣ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አፈ ጉባኤ ፣የሁሉም ወረዳ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የትምህርት ሀላፊዎች እና የውሀ ፅ/ቤት ሀላፊዎች የሰቆጣ ከተማ ከንቲባ፣ የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሀላፊ ፣ ዞን ፋይናንስ ሀላፊ ፣ የመ/ኮሙኒኬሽን፣ የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር እና ባለሞያዎች ፣ የLego Foundation CDA/Project ባለሞያዎች ተገኝተው ጎብኝተዋል።

ከምልከታ ቡኋላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ም/አስተዳደሪና የኢንበስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን በራስ አቅም የመልማት ምልክት የሆነው የዋግ ልማት ማህበር ከህዝባችን ጎን በመሆን በብሔረሰብ አተዳደራችን በርካታ የልማት ሰራዎችን ሰርቷል። ይህ ዛሬ ያነው ፕሮጀክት በህፃናት ላይ ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሆነ አይተናል ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በብሔረሰብ አስተዳደራችን በርካታ ህፃናት በተለያዩ ምክኒያቶች ከትምህርት ገበታቸው እርቀው ቆይተዋል ይህንን በሚያካክስ መልኩ በዚህ ፕሮጀክት ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሆን ተመልክተናል። ህፃናት ላይ መሰረት አድርጎ መሰራት በትምህርት ጥራት ላይ መሰረት መጣል ነው እና ጠንክረን መሰራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል። በመጨረሻም በዚህ ፕሮጀክት እየሰራችሁ ላችሁ ባለድርሻ አካላትን በራሴ እና በብሔረሰብ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ሲሉ ምስጋናቸው ን ገልፀዋል።

የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሀይሌ ወልዴ /ረዳት ፕሮፌሰር /በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዋነኛነት አላማው በጦርነትና በድርቅ የተጎድ አካባቢዎች ላይ ምንም አይነት የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት እድል ያላገኙ ህጻናትን የትምህርት እድል እንዲያገኙ በማድረግ በህጻናት ላይ ሁለንተናዊ እድገት እንዲመጣ የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ አምስት ዓመት ቆይታ ያለው ሲሆን ሴቭ ዘችልድረን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ ጋር በመቀናጀት የሚፈጸም መሆኑን ና የገንዘብ ድጋፍ ከሌጎ ኦፎ ፋውንዴሽን /CDA/ ፕሮጀክት የተገኝ መሆኑን ሀይሌ ወልዴ /ረዳት ፕሮፌሰር / ገልጸዋል።

አክለውም ፕርጀክቱ በመደበኛው ፕሮግራም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት 14ሺህ 500 ህጻናትን፣ በፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት/ accelerated school readiness ፕሮግራም 4000 ሺህ ህጻናትን፣ ELM at home/ በቤት ለቤት ትምህርት 4ሺህ 612 ህጻናት በአጠቃላይ በስድስት ወረዳዎች 23ሺህ 112 ህጻናትን በአምስት አመት ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ያለ ፕሮጀክት ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ህጻናት ሁለንተናዊ ለውጥና እድገት እንዲያመጡ መማር ማስተማርና ከምገባ ፕሮግራሙ ባሻገር ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት የመማሪያ ክፍሎችን በማስዋብና በማስጌጥ በጨዋታ መልኩ በማዝናናትና በማጫወት የሚያተምሩበትን ምቹ ሁኔታ ፈጥረናል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ። በተለይም የምግባ ፕሮግራሙ መኖር የማቋረጥ ምጣኔን በእጅጉ ዝቅ በማድረግ የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ እንዲሆን አድርጓታ ል ብለዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ኮሙኒኬሽን ዋና ሀላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ይህ ፕሮጀክት ህፃናት ላይ የሚሰራ በመሆኑ ፍሬ ያለው ለትውልድ መሠረት የሚሆን ነው። ህፃናት ነገ አገር ተረካቤዎች ናቸው። ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ደግሞ ነገ አገራችን የተሻለ የተማረ ሀይል አገር የሚያስቀጥል ትወልድ እዲኖራት ያደርጋል ብለዋል በውይይቱ።

"ህብረት ለዋግ ልማት"
"በመተባበርር ዋግን እናልማ"
#በታደሰ በላይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxgi

የዋግ ልማት ማህበር ዋና  ዳይሬክተር ሀይሌ ወልዴ (ረዳት ፕሮፌሰር)  ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች   1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አ...
19/03/2026

የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሀይሌ ወልዴ (ረዳት ፕሮፌሰር) ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።
========//////=======

ሰቆጣ :- መጋቢት 10/2018 ዓ/ም (WDA Communication) የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሀይሌ ወልዴ (ረዳት ፕሮፌሰር) ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ሀይሌ ወልዴ (ረዳት ፕሮፌሰር) በሀገራችን በህዝበ ሙስሊሙ በድምቀት የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት በዓሉ በሙስሊም ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ የሚውል ሀይማኖታዊ በዓል መሆኑን ገልፀው ማህበረሰቡን የሚያስተሳስር በመሆኑ በሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ የሚታሰብና የሚናፈቅ ዓመታዊ በዓል ነው ።

ይህ ታላቅ በዓል የእርስ በርስ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክር ፣መንፈሳዊ እሴቶችን የበለጠ የሚያዳብር ተቻችለንና ተከባብረን በጋራ መኖርን ለመላው ዓለም ህዝቦች በምሳሌነት የምናሳይበት በዓል ነው ብለዋል።

ይህን ታላቅ በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት የተራቡትን በማብላት እና በማጠጣት እንዲሁም የአንድነት እሴቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ሊሆን ይገባል በማለት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብና የአንድነት ይሁንልን በማለትም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

መልካም በዓል !! ኢድ ሙባረክ !!

"ህብረት ለዋግ ልማት"
""በመተባበርር ዋግን እናልማ"
#በታደሰ በላይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

የዋግ ልማት ማህበር  11 የስራ መራር ቦርድ አባላትን በማስመረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ።=========///////======ጥር 09/2018 ዓ/ም /WDA/ communication/ማኅበሩ በዛሬው...
17/01/2026

የዋግ ልማት ማህበር 11 የስራ መራር ቦርድ አባላትን በማስመረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ።
=========///////======
ጥር 09/2018 ዓ/ም /WDA/ communication/ማኅበሩ በዛሬው 13ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴው ያስገመገመ ሲሆን የልማት ማህበሩ ከ2015-2017 ዓ.ም የ ፊዚካል ና ፋይናንስ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015-2017 ዓ.ም የውጭ ኦዲት ሪፖርት እና የሚሻሻሉ ልዩ ልዩ ህጎች ቀርበው በተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ጉባኤው ከ2015-2017 ዓ.ም የ ፊዚካል ና ፋይናንስ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015-2017 ዓ.ም የውጭ ኦዲት ሪፖርት እና የሚሻሻሉ ልዩ ልዩ ህጎች ቀርበው በሙሉ ድምፅ ካፀደቀ በኋላ የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው በሚለቁ የ ስራ መራር ቦርድ አባላትን ተተኪ የመረጠ ሲሆን በዚህም፦

1ኛ ዶ/ር ብርሃኑ ሮዳስ (የቦርዱ ሰብሳቢ)

2ኛ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ(ምክትል ሰብሳቢ)

3ኛ ሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

4ኛ የደሀና ወረዳ አስተዳዳሪ

5ኛ የሰሀላ ወረዳ አስተዳዳሪ

6ኛ ወ/ሮ ፋንታይቱ ካሴ

7ኛ አቶ ተገኘ ብርሃኑ

8ኛ ዲ/ን ኪዳነማሪያም ገ/ህይወት

9ኛ አቶ ወርቁ አበባው

10ኛ አቶ አበበ ተቀባ

11ኛ አቶ ምትኩ በየነ(አባል) በአጠቃላይ ከሶስት ወረዳዎችና 3 አባላት በድምሩ 11 አባላትን በመምረጥ ቀሪዎች 6 ወረዳዎች ቁጥጥርና ክትትል ሆነው እንዲቀጥሉ በመወሰን ጉባኤው በሰላም ተጠናቋል።

"ህብረት ለዋግ ልማት"
""በመተባበርር ዋግን እናልማ"
#በታደሰ በላይ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

የዋግ ልማት ማህበር  (ዋልማ) 13ኛውን  መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ  እያካሄደ ነው። -----------------/////---------------- ጥር 09/2018 ዓ/ም /WDA/ communic...
17/01/2026

የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) 13ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ ነው።
-----------------/////----------------
ጥር 09/2018 ዓ/ም /WDA/ communication/ የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) 13ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሰቆጣ ከተማ ቴድሮስ አንቦ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤውም የብሔረሰብ አስተዳደሩና የልማት ማኅበሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባላት ተገኝተዋል።

ማኅበሩ በዛሬው 13ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴው ያስገመግማል ።የልማት ማህበሩ ከ2015-2017 ዓ.ም የ ፊዚካል ና ፋይናንስ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015-2017 ዓ.ም የውጭ ኦዲት ሪፖርት እና ልዩ ልዩ ህጎች ይቀርባል በተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት ይሰጥበታል።

በመጨረሻም ጉባኤው የ2018 ዓ.ም እቅድን በሙሉ ድምፅ ካፀደቀ በኋላ የዋግ ልማት ማህበር የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው በሚለቁ የቦርድ አባላት ተተኪ ስራ አመራር ቦርድ አባላትን በጉባኢተኛው ያሰመርጣል።

ለማኅበሩ አሻራቸውን ላበረከቱ ተቋማት ፣የልማት ማህበራት ፣ ለ በጉ አድራጊ ድረጅቶች ፣ለሀይማኖት ተቋማት ፣NGOዎች እና ለበጎ አድራጊ ግለሰቦች እንዲሁም የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው ለሚለቁ ስራ መራር ቦርድ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

"ህብረት ለዋግ ልማት"
""በመተባበርር ዋግን እናልማ"
#በታደሰ በላይ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

12/01/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም፣ በጤና ፣ በአብሮነት አደረሰን፤አደረሳችሁ።  እያለ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ የዋግ ልማት...
06/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም፣ በጤና ፣ በአብሮነት አደረሰን፤አደረሳችሁ። እያለ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ የዋግ ልማት ማህበር/ዋልማ/ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
=======////========
ታህሳስ 28/2018ዓ.ም (WDA communication) በአገር ውስጥም በውጭ አገርም ለምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን እና የልማታችን ደጋፊዎች፣ የተወደዳችሁ የልማት ማህበራችን ስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ ደጋፊዎቻችን እና አጋሮቻችን፤ የልማት ማህበራችን አባላት፤ በሙሉ እንኳን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ፡፡ ሲል የዋግ ልማት ማህበር/ዋልማ/ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
መልካም የገና በዓል!!!!
"ህብረት ለዋግ ልማት"
።"በመተባበርር ዋግን እናልማ"

#በታደሰ በላይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

የኢትዮጵያ  ስኩል  ሚል  ኢኒሼቲቭ  በሰቆጣ  ከተማ  የሚገኝውን  የአልሚ  ምግብ  ማቀነባበሪያ  ፋብሪካ  ለዋግ ልማት  ማህበር /ዋልማ/  በስጦታ  አበረከተ።===========/////==...
02/01/2026

የኢትዮጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭ በሰቆጣ ከተማ የሚገኝውን የአልሚ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ በስጦታ አበረከተ።
===========/////======
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም (WDA communication) የወ/ሮ ፍሬ አለም ሽባባው ንብረት የሆነው የኢትዮጵያ ስኩል ሚል ኢኒሼቲቭ የአልሚ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የርክክብ ኮሜቴዎች በተገኑበት በስጦታ ለዋግ ልማት ማህበር ተበርክቷል።

ወ/ሮ ፍሬ አለም ሽባባው ከዚህ በፊት ለዋግ ልማት ማህበር የቋንጣ ፋብሪካን፣ የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ፣ለተማሪዎች የወተት የምገባው የሚሆኑ የወተት ላሞችን እንዲሁም የሴራሚክ ፋብሪካን 7.56% የባንክ ሸር በስጦታ ያበረከተች ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የሰቆጣ አልሚ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለልማት ማህበሩ በስጦታ አበርክታለች።
#ልጆቸ ባሉበት ሁሉ ምግብ ይኑር!!
#በታደሰ በላይ
"ህብረት ለዋግ ልማት"
።"በመተባበርር ዋግን እናልማ"
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ የተለያዩ
መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
Facebook ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=100022758102105
ዌብሳይት :-https://www.wag-ethiopia.org/
You tube ዩቲዩብ፡-https://m.youtube.com/channel/UCeNGCZjNmLcGvvSdujXECxg

Address

Amhara Region

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 00:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ Wag Development Association /WDA/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization?

Share