AWANA Wolayta

AWANA Wolayta AWANA - Wolayta Association in North America

08/09/2022
08/04/2022

የዎላይታ ብሄር ተወላጆች የዎላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት መብት እንዲከበር ጠየቁ።

ክላስተር የተባለው አደረጃጀት ከሀገሪቱ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረንና ሃሳቡም ኢ-ህገ መንግስታዊ ከመሆኑም በሻገር ተግባራዊነቱም እጅግ አስቸጋሪ ነው ያሉት አስተያየታቸውን ለኦ ኤም ኤን የሰጡ የብሄሩ ተወላጆች፣ ውሳኔውን አውግዘዋል።

የዎላይታ ህዝብ ለዘመናት ከተጫነበት መዋቅራዊና ሁለንተናዊ ጭቆና ነፃ ለመውጣት በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ምዕራፎች ያሉትን ብርቱ ትግል ሲያደርግ የቆየ ህዝብ መሆኑን የዎላይታ ብሄር ተወላጆች ጠቁመዋል።

ህዝቡ የተነጠቀውን መዋቅራዊ ነፃነት መልሶ ለመጎናፀፍ ያደረጋቸው የትግል ሂደቶች እጅግ መራራ ናቸው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ፣ ውድ ዋጋን ያስከፈሉ ስለመሆናቸውም አክለዋል።

ሕዝቡ ህዝበ ውሳኔን ብቻ እየተጠባበቀ ባለበት በዚህ ወቅት ክላስተር የተባለ አደረጃጀት ከመንግስት በኩል መምጣቱ አግባብ አይደለም ሲሉ የመንግስትን ውሳኔ ተችተዋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ : https://omnglobal.com/am/14152/

03/14/2022

"ታኒ ዎላይታ የተሰኘ" መፃፍ የኦንላይን መገበያያ በሆነዉ አማዞን ለሽያጭ በቃ

በደራሲ ማንያህልሻል ማዴቦ የተጻፈዉ ታኒ ዎላይታ የተሰኘ በጉድፈቻ ህፃናት ላይ ትኩረቱን ያደረገ መፃፍ የኦንላይን መገበያያ በሆነዉ አማዞን ላይ ለሽያጭ በቅቷል።

ማንያህልሻል ማዴቦ ተወልዳ ያደገችው በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሲሆን ከኢትዮጵያ እ ኢ አ በ2013 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜርካ ተዛወረች፣ አሁን በሰሜን ቨርጂኒያ ከባለቤቷ እና 3 ልጆቿ ጋር የምትኖረዉ ማንያህልሻል በጉዲፈቻ ለሚያድጉ ህጻናት የቤተሰብ ፍለጋ፣ የቋንቋ ሥልጠና፣ የባህል ዝንባሌ፣ የደብዳቤ ትርጉም፣ የስልክ ጥሪ እና ትርጓሜ በፈቃደኝነት እየሰራች ነው።

27 የማደጎ ልጆችን ከወላድ ወላጆቻቸው ጋር እንደገና አገናኝታለች። ዎላይታ ውስጥ ተወልዳ ያደገች ሴት እንደመሆኗ መጠን ስለ ዎላይታ ባህል እና ወግ ብዙ መረጃ አላት። ከበርካታ የማደጎ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸዉ ጋር የሰራችዉ የማደጎ ህጻናት መብት ተሟጋች ደራስ ማንያሂሊሻል ማደቦ ቤተሰቦች እና ልጆች ስለትውልድ ቦታቸው የሚጠይቋቸውን ብዙ የተለመዱ ጥያቄዎችን በመጻፉ ለመመለስ ሞክራለች።

እኔ ዎላይታ ነኝ የተሰኘዉ መጸሐፍ የመጀመሪያዋ መጽሃፍ ነው ሁሉንም ጥያቄዎች ላይመልስ ይችላል ነገር ግን በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን አካትቷል ስትል ደራስዋ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግራለች።https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Fwww.amazon.com%2Fdp%2F1662921217%2Fref%3Dtsm_1_fb_lk&h=AT06xkv1zc3Lfg33Rj_Swu6HZMxzs695znhYUUzP96MWlYe6St144qsftza6wSZ0evm8DD5ggLbdecEiZvd9UpV9i0CIkeiz7BKcoyBVFS-AwNX5yhtvJNpCfffNttZTDiDs3_MpV1k

https://wolaitatimes.com.et/ባህልና-ቱሪዝም/ታኒ-ዎላይታ-የተሰኘ-መፃፍ-የኦንላይን-መገ/

https://t.me/WolaitaTimes/2645

02/07/2022

ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ Feb. 12, 2022 በዲሲ ሰዓት ልክ 8:00PM ላይ በሚኖረን በZoom በምናደርገው ስብሰባ ላይ የማኅበራችን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዳታ ዴኣን ጨምሮ ሌሎችም ተወካዮቻችን ከአገር ቤት ጉብ....

Address

Sacramento, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AWANA Wolayta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to AWANA Wolayta:

Share