Afar Development Association

Afar Development Association Afar Development Association (AFDA) is membership based, indigenous, non-for-profit local non-governmental organization established in July 2011.

Mr Nuradin Sedik
Email:- [email protected]

additional Phone:- +251913913471
Email:- [email protected]

31/08/2026
የአፋር ልማት ማህበር በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳዎች በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ የአፋር ልማት ማህበር (AfDA) በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሸ ፈንታሌ ወረዳ...
30/08/2026

የአፋር ልማት ማህበር በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳዎች በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

የአፋር ልማት ማህበር (AfDA) በገቢ ረሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሸ ፈንታሌ ወረዳዎች የቀበና ወንዝ በመሙላቱ ምክንያት በሁለት ወረዳዎች ላይ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የ2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ በጎርፍ አደጋው ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች በወቅታዊ ሁኔታ የሚያስፈልጉ የእርዳታ አቅርቦቶችን ለማሟላት የሚያግዝ ነው።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የገቢ ረሱ ዞን አስተዳደር አቶ ሁሴን መሐመድ ጉረታ እና የአፋር ልማት ማህበር ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ሁመድ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።

የአፋር ልማት ማህበር በችግር ጊዜ ከማህበረሰቡ ጎን በመቆም፣ የተጎዱ ወገኖችን በመደገፍ እና የማህበረሰብ ተጋላጭነትን በመቀነስ የሚያደርገውን ሥራ ያጠናክራል።

አፋር ልማት ማህበር — ከማህበረሰቡ ጎን ሁሌም ይቆማል! 🤝

በአሳይታና ዱብቲ ወረዳዎች ፕሮጀክቱን ለሚተገብሩ 6 አጋር ድርጅቶች ባለሙያዎች የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና ተሰጠየአፋር ልማት ማህበር (አፋልማ) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና ከአጋር ድርጅቶቹ ...
06/08/2026

በአሳይታና ዱብቲ ወረዳዎች ፕሮጀክቱን ለሚተገብሩ 6 አጋር ድርጅቶች ባለሙያዎች የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ
የአፋር ልማት ማህበር (አፋልማ) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር በመተባበር ለ3,500 ወጣቶች ዘላቂና ክብር ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የአጎ ፕሮጀክትን በአሳይታና ዱብቲ ወረዳዎች በመተግበር ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ለወጣቶች የክህሎት ስልጠና፣ የፋይናንስ ተደራሽነት (በዓይነት የግብዓ) ድጋፍ በመስጠት ከጥገኝነት ተላቀው ራሳቸውን የሚችሉና ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንድኖራቸዉ እየሰራ ይገኛል።
በፕሮጀክቱ ድጋፍ ወጣቶች በኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው በአግሪ-ቢዝነስ ዘርፍ፣ ማለትም በሰብል ምርት፣ በፍየል ማደለብ እና በእንስሳት መኖ ማምረትና አቅርቦት ተሰማርተው ይገኛሉ።
ይህንን በማስፋፋት የፕሮጀክቱን ጥራትና ውጤታማነት ለማጠናከር፣ በአሳይታና ዱብቲ ወረዳዎች ፕሮጀክቱን ለሚያስፈጽሙ 6 አጋር ድርጅቶች ባለሙያዎች በሰብል ምርት፤ በእንሰሳት (ፍየል) ማድለብ እና በእንሰሳት መኖ ማምረትና አቅርቦት የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና በሰመራ ሩፍታና ሆቴል ተሰጥቷል። ስልጠናውም በዘርፉ በቂ ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ከአፋር ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ እንዲሁም ከእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ በተመረጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎችም ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች በማስተላለፍ ተመሳሳይ የቴክኒክ ስልጠና እንደሚሰጡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ይህም የወጣቶችን አቅም በማጎልበት የፕሮጀክቱን ውጤት በዘላቂነት ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

እንኳን ደስ አለን! 🎉የአፋር ልማት ማህበር (AfDA) በአፋር ክልል ያከናወነውን የልማትና የሰብአዊ ድጋፍ ሥራ፣ ቁርጠኝነትና ተፅዕኖ በማድነቅ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ...
05/08/2026

እንኳን ደስ አለን! 🎉
የአፋር ልማት ማህበር (AfDA) በአፋር ክልል ያከናወነውን የልማትና የሰብአዊ ድጋፍ ሥራ፣ ቁርጠኝነትና ተፅዕኖ በማድነቅ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የእውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶልናል።
ይህ እውቅና ለተቋማችን ብቻ ሳይሆን ከእኛ ጎን ለቆሙ አጋሮቻችን፣ ደጋፊዎቻችን፣ ሠራተኞቻችን እና የአፋር ህዝብ የጋራ ስኬት ነው።

"Beeri Hora Sabhallale Mano Geytuh Asaaku Daabisnay" Qafar Daddos Egla Taama Abeynit Cox Daabisiyat🌾🌾 "የነገው ትውልድ የተረጋጋ ህ...
03/08/2026

"Beeri Hora Sabhallale Mano Geytuh Asaaku Daabisnay" Qafar Daddos Egla Taama Abeynit Cox Daabisiyat🌾🌾

"የነገው ትውልድ የተረጋጋ ህይወት እንድያገኝ ዛሬን እንትከል" 🌾🌾

በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ🌱 ተከላ መርሃ ግብር የአፋር ልማት ማህበር የተለያዩ የፍራፍሬና የደን ችግኞችን በመትከል ላይ ይገኛል።

"Asaakih Murti gaaboyso kimal tekkeh tan maqar le taamah Xalootu!" - Dr. Konte MuusaQafar Rakaakayak Dubti Daqaaral Qafa...
06/07/2026

"Asaakih Murti gaaboyso kimal tekkeh tan maqar le taamah Xalootu!" - Dr. Konte Muusa
Qafar Rakaakayak Dubti Daqaaral Qafar Daddoosih Egla Abak Sugteh tan Buqre Daddoosih Taama Masho kee Salit Murti Gaaboyso Meqe Gurral Abak Macisen.
50 hektaarak daga takke baaxol buqre abteh tan ta cugayso away kaxxa caddo gufteh Murti gaaboysot tan. Agdaabele Murti Qafar Rakaakayak Baarle Buqre Dudda Yaybulleewak Qafar Daddos Eglak kaadu Hadaf Abtol Korisaanamal Leh Tan Fayxi Tascasse. Ta Xaaloot fooca fanah sarrimaane le buqreh daddosih baarisoonuh maqarle rakiibo daffessa.
Murti gaaboysoh Taamal Qafar Daddoosih Eglak N/Saqalah yan Massakaxxale Dr. Konte Moussa Edde Anuk Cugaysô Aracat Gufne Abak Akkuk Geytimta Taama Yuble. Ta Murtil Meqeh tan Xalitte kah geytimtem Cubbil Ekraarisiyyaay, kee Butta Taamaa kee Qafar Daddos Egla Buqreh teceh tan baxsale hangi kee Fayxi Kinnim Kassiise.
Qafar Daddoosih Egla, Dacarsittoh xiina diggoysak, sarrimaane le daddos yaysexeexegeenimiiy, qidaddo saamitte ginaanamaay, Qafar ummattah mano milaagaanamal diggowteh tan Egla kinnim qaddoyse.

"የዛሬው ምርት መሰብሰብ የትናንቱ ጥረት ፍሬ ነው!" — ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ
በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የአፋር ልማት ማህበር በራሱ እያከናወነ የሚገኘው የግብርና ልማት ፕሮጀክት የሰሊጥ እና የማሾ ምርት በአመርቂ ውጤት ወደ ምርት መሰብሰብ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ከ50 ሄክታር በላይ መሬት ላይ በጥንቃቄ የተከናወነው የእርሻ ልማት ዛሬ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የማህበሩን ራዕይ ወደ ተግባር መቀየሩን አረጋግጧል። ይህ ውጤት በቀጣይም የአፋርን የግብርና እምቅ አቅም በተግባር ለማሳየት ጠንካራ መሠረት ይሆናል።
በምርት መሰብሰብ ሂደቱም የአፋር ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ በቦታው በመገኘት የሥራውን እንቅስቃሴ ተከታትለዋል። በዚህ አጋጣሚም የተገኘው አመርቂ ውጤት የተቀናጀ እቅድ፣ የትጋት ሥራ እና የጋራ ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
አፋር ልማት ማህበር የክልሉን የግብርና አቅም በማሳደግ፣ ለህዝቡ ዘላቂ የልማት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ጥረት በቀጣይነት ያጠናክራል።
Afar Agriculture and Natural Resource Development Bureau
Afar Mass Media Agency

Address

Semera

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar Development Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Afar Development Association:

Shortcuts

Share