Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ

Youth-Mission
 የወጣቱ ተልእኮ አሏህ የሰማይ እና የምድር ብርሃን ነው። [አል-ቁርአን 24:35] 🕌

የወጣቱ ተልዕኮ ምንነት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

==

1 በጊዜያት እምላለሁ።
2 በእርግጥ ሰው ሁሉ በኪሳራ ውስጥ ነው።
3 እነዚያ ያመኑት ፣ መልካም ስራን የሰሩት ፣ በእውነት እና በትዕግስት አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው። የአሏህﷻ እዝነት በረሱል(ﷺ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ እለተ ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

የወጣቱ ተልእኮ ኢስላማዊ መርህን የሚከተል ሲሆን የአድራሻውን ስም እንድሰጥ ምክኒያት የሆነኝ የራሴ የእድሜ ክልል እና ሙስሊም ወጣቶች በኡ

ማው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የነቃ ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ሌላው ያነሳሳኝ ነገር አብዛሃኛው የማህበረሰባችን ክፍል ከአሊሞች ጋር ቁጭ ብሎ ከመማር እያፈገፈገ ፣ አሊሞችም በየቦታው ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ፣ ወጣቱ ክፍል ከማወቅ ከመማር እየራቀ ፣ የማንበብ ባህሉ እየደከመ ፣ ከእውቀት ይልቅ ጨዋታ አሉቧልታ ያአሉ ወሬ እጥቅቶት የእውቀት ድሃ ሆኖ ሲንከራተት በማየቴ እና ወጣቱ ክፍል መጽሐፍ ገዝቶ ከሚያነበው ይልቅ በማህበራዊ ድህረገፆች ኦንላይን ላይ የሚያዘወትር ብዙ በመሆኑ እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ ተደራሽነቱ ከህትመት ስራዎች ሁሉ የበለጠ በመሆኑ ኡማውን በድህረገፅ ፣ በማህበራዊ ሚድያ እና በተለያ የህትመት ውጤቶች ማገልገል እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ነው።

የወጣቱ ተልዕኮ ሙሉ በሙሉ ኢስላማዊ መርሆዎችን የሚከተል እና ከማንኛውም አይነት ሃይማኖታዊ ክፍፍል ወይም ቡድንተኝነት የፀዳ ነው። ለዚህም ቁንርንና ሱናን ተንተርሶ አሏህ በሰጠን ሙስሊም በሚለው ቁርአናዊ መጠሪያ ብቻ የተብቃቃ ነው።

የወጣቱ ተልዕኮ ዋና አላማው "ወደ ጌታህ በጥበብና በመልካም ግሳፄ ጥራ" የሚለውን መለኮታዊ ራዕይ እና "ከእኔ የሰማችሁትን አንዲትም አንቀፅ(አረፍተ ነገር) ብትሆን አስተላልፉ" የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ ተመርኩዞ የኢስላምን ትክክለኛ መልእክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረስ ፣ የአሏህንና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ንግግር የበላይ ማድረግ ፣ ኡማውን በድህረገፅ ፣ በማህበራዊ ሚድያ አገልግሎት ማገልገል ፣ የአንብብ ትውልድ ለንባብ እና ለእውቀት ትኩረት እንዲሰጥ ማገዝ ፣ በከፊልም ቢሆን ስለዲኑ የሚያውቅ ወጣት ማፍራት ፣ ኡማውን በቁርአን እና በሱና ገመድ ማስተሳሰር ፣ የካፊሮችን እና ለአክፍሮት ሃይላት አፀፋዊ ምላሽ መስጠት እና ስለ ኢስላም የምንማርባቸውን መንገዶች ማመቻቸት እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር ነው።


የወጣቱ ተልእኮ የወጣቱን ንቅናቄና ተሳትፎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ስትራቴጅ በመተግበር በወጣቱ ዘርፍ የእውቀትና የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ፣ ተግባራዊ ወጣት መፍጠር ፣ የዳዕዋ ስራ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ እና የልዩነት ሃሳብን ቢኖርም ልዩነቱን ለእራስ ትቶ በዲነል ኢስላም ጥላ ስር ለአንድቱና ለህብረቱ የሚቆም ወጣት ለመፍጠር እና በአጠቃላይ ህዝበ ሙስሊሙ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ማሳደግ ስለሚያስፈልግ ይህን ስትራቴጅ ነድፎ መንቀሳቀስ አስፈልጓል፡፡


መስራች: አህመድ የሱፍ
ኢሜል: [email protected]

ዌብሳይት:
http://youth-mission.mobie.in

page:
http://facebook.com/youth.mission29

17/06/2026

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ:

Share