CoTm Association

CoTm Association CoTM Club | Professional association for Construction Technology and Management students and professionals. Building future construction leaders.

Outcome based curriculum Review workshop ተካሄደ።ግንቦት 17፣ 2018 ዓ.ምበወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጅ ኢንስቲቱት በሲቪልና ውሃ ሃብት ምህንድስና ት/ቤት ኮንስትራ...
25/05/2026

Outcome based curriculum Review workshop ተካሄደ።

ግንቦት 17፣ 2018 ዓ.ም

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጅ ኢንስቲቱት በሲቪልና ውሃ ሃብት ምህንድስና ት/ቤት ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል የቅድመ ምረቃ ስርዓተ-ትምህርት ክለሳ የውጭ ግምገማ (ወርክሾፕ) አካሂዷል።

በስርአተ ትምህርት ክለሳ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር መ/ር ሳሙኤል ንጋቴ፣ የት/ቤቱ ዲን መ/ረ ምላሹ ሲሳይ፣ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ዳይሬክተር ወ/ሮ ዙፋን አበበ ፣የትምህርት ክፍል ሃላፊዋ መ/ርት ሰላማዊት አባይ ፣ ከየክፍሎቹ የመጡ መምህራን በአካል የተገኙ ሲሆን፤ የውጭ ገምጋሚ ባለሙያዎች ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የተከበሩ አቶ አቦነህ ተስፋየ እና ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ደሳለኝ ግርማ በበይነ-መረብ በመገኘት ሰፊ ግምገማ አካሂደዋል።

ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መ/ርት ሰላማዊት አባይ ለገምጋሚዎች ከልብ የመነጨ ምስጋና በመስጠት የወርክሾፑ ዋና ዓላማ ተማሪዎችን በተግባራዊ እውቀትና በምርምር ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል ውጤት ተኮር (Outcome-based) ስርዓተ-ትምህርት መቅረጽ መሆኑን ተናግረዋል።

የት/ቤቱ ዲን መ/ር ምላሱ በበኩላቸው በዘርፉ ያለውን ወቅታዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ያገናዘበ እና የሀገሪቱን ፍላጎት የሚያሟላ የቴክኖሎጂ ትምህርት ለመስጠት እንዲቻል፣ ቀደም ሲል የነበረውን ስርዓተ-ትምህርት አሻሽለናል። ከትምህርት ክፍል እስከ ኮሌጅ (ት/ቤት) ደረጃ የተገመገመውን ይህንን ሰነድ ዛሬ ለውጭ ምሁራንና ባለሙያዎች ግምገማ ማቅረብ ችለናል ብለዋል።

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን በትምህርት ክፍሉ የተከናወነ የዳሰሳ ጥናትና የስርዓተ-ትምህርት ክለሳ ሰነድ በአዘጋጅ ኮሚቴው አማካኝነት ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ ላይ በመነሳት ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አቶ አቦነህ ተስፋየ ፣ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ደሳለኝ ግርማ እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች በበየነ መረብ በመግባት በርካታ ጠቃሚና ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

በማጠቃለያውም፣ የትምህርት ክፍሉ አዘጋጅ በውስጣዊና በውጫዊ ተሳታፊ አካላት የተሰጡትን ጠቃሚ ሀሳቦችና የተግባር ትምህርትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ግብዓቶችን በሙሉ በመውሰድ፣ ደረጃውንና ጥራቱን የጠበቀ ስርዓተ-ትምህርት አዘጋጅተው ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ስለ ፎቶው : በስልክ የተቀረፀ ነው።
Addresses
E-mail
[email protected]" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]
TG: t.me/CoTM_assocciation
FB: facebook.com/CoTMassociation
YT: youtube.com/
TT: tiktok.com/

 [ወልድያ፤ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም]የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጧቸውን ትምህርቶች በጥራትና በደረጃ መመዘኛ (Accreditation) ማለፍ እን...
09/05/2026


[ወልድያ፤ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም]

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጧቸውን ትምህርቶች በጥራትና በደረጃ መመዘኛ (Accreditation) ማለፍ እንዳለባቸው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሲቪልና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ቤት ስር የሚገኘው የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት (CoTM) የትምህርት ክፍል ይህንኑ መመዘኛ በብቃት አሟልቶ አፅድቋል።

በተካሄደው ልዩ ጉባኤ፣ የትምህርት ቤቱ ዲን አቶ ምላሹ ሲሳይ እና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ወረ/ት ሰላማዊት አባይ እንዲሁም የSAC አባላት በሙሉ በተገኙበት፣ የክለሳ ሰነዱ በጥልቀት ተገምግሞ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።

Outcome-Based Education (OBE) መሸጋገሩ ከሀገራዊ ፋይዳው ባሻገር የሚከተሉትን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ያስገኛል፦

1. International Recognition: ይህ ስርዓተ-ትምህርት እንደ Washington Accord ያሉ ዓለም አቀፍ የምህንድስና ስምምነቶችን መመዘኛ የተከተለ በመሆኑ፣ ተማሪዎቻችን በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የትምህርት ተቋማትና የሥራ ገበያዎች በቀጥታ እውቅና እንዲያገኙ ያደርጋል።

2. Student Mobility: ምሩቃኖቻችን በውጭ ሀገር የትምህርት ዕድሎችን (Scholarships) ሲያመለክቱ የወሰዱት ትምህርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመጣጣኝነቱ (Equivalency) በቀላሉ የሚረጋገጥ ይሆናል።

3. Industry Alignment: ትምህርቱ በውጤትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፣ አሰሪ ድርጅቶች የሚፈልጉትን ብቁ ባለሙያ በቀጥታ ለማግኘት ያስችላቸዋል።

4. Continuous Quality Improvement: ስርዓቱ በየጊዜው ራሱን የሚገመግምና ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር አብሮ የሚራመድ እንዲሆን ያደርገዋል።



ይህንን ውጤት ተከትሎ፣ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በስርዓተ-ትምህርት አተገባበር እና በዘርፉ የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ታላቅ ወርክሾፕ (Grand Workshop) በቅርቡ ይካሄዳል። በዘርፉ ባለድርሻ አካላት የሆናችሁ ሁሉ በዚህ መድረክ ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

መልካም ቀን




Addresses
E-mail
[email protected]" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]
Telegram
https://t.me/CoTM_assocciation
Youtube:
www.youtube.com/
Tiktok
tiktok.com/
Facebook https://www.facebook.com/CoTMassociation

`

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማናጅመንት (CoTM) የተማሪዎችና የባለሙያዎች ማኅበር አባላት፤ማኅበራችን በክለብ ...
11/04/2026

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማናጅመንት (CoTM) የተማሪዎችና የባለሙያዎች ማኅበር አባላት፤

ማኅበራችን በክለብ (Club) ደረጃ ከተመሰረተ የ10ኛ ዓመታቱን ባስቆጠረበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ስንል ታላቅ ደስታ ይሰማናል።

📖 “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

የትንሣኤው በዓል ለሁላችንም የደስታ፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

ባለፉት 10 ዓመታት በጋራ የገነባነው ጠንካራ መሠረት ለቀጣይ ስኬቶቻችን መረጋገጫ ነው። ዛሬ በምናገኘው ዕውቀት ነገን በተሻለ ጥበብ ለመገንባት በምናደርገው ጥረት የትንሣኤው ጌታ ብርሃኑን ይግለጽልን።

"Learn Today, Build Tomorrow!"

🌿 መልካም በዓል! 🌿

📍 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
🏗️ COTM Association
📅 2026 G.C

26/03/2026

With Woldia University – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!

21/03/2026

ማስታወቂያ
ለትምህርት ማህበረሰቡና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፉ በተዘጋጁ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤
1. በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ https://forms.gle/KiRAQn6kjsZ6yymt6
2. የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ https://forms.gle/YEsQJwjE3wYUypJz6
3. በትምህርት ሚኒስቴር ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ
https://forms.gle/HLqZm83W2ANMWMLt5

Dears, Answer the  question.
21/03/2026

Dears, Answer the question.

የConstruction Technology and Management (CoTM) ባለሙያዎች ማኅበር፣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ ተማሪዎችና የዘርፉ ተዋናዮች በሙሉ እን...
20/03/2026

የConstruction Technology and Management (CoTM) ባለሙያዎች ማኅበር፣ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የሥራ ባልደረቦቻችን፣ ተማሪዎችና የዘርፉ ተዋናዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።

ይህ በዓል የሰላም፣ የመተሳሰብና የፍቅር እንደመሆኑ መጠን፣ እኛም በሙያችን ለሀገር ግንባታ የምናበረክተው አስተዋጽኦ በጠንካራ መሠረትና በቅንነት የታጀበ እንዲሆን እንመኛለን። የግንባታው ዘርፍ ትዕግስትን፣ ትክክለኛ ዕቅድንና ጠንካራ ጥረትን እንደሚጠይቅ ሁሉ፣ የረመዳን ወርም እነዚህን መልካም እሴቶች በተግባር የምናሳይበት ወቅት ነው።

በዓሉ፦
⤻ለባለሙያዎቻችን አዲስ የሥራ መነሳሳትን የሚፈጥር፤
⤻በዘርፉ ባሉ ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ትብብርና አንድነት የሚገነባበት፤
⤻ለሀገራችን ብልጽግናና ዕድገት ተስፋ የሚሰጥ እንዲሆንልን እንመኛለን።

ዒድ ሙባረክ!

Technology and Management (CoTM) ባለሙያዎች ማኅበር

E-mail
[email protected]" rel="ugc" target="_blank">https://[email protected]
Telegram
https://t.me/CoTM_assocciation
Youtube:
www.youtube.com/
Tiktok
tiktok.com/
Facebook https://www.facebook.com/CoTMassociation


`

15/03/2026
አስደሳች ዜና    በ2ኛ ዲግሪ  በConstruction Engineering  and  Management  ትምህርት ዘርፍ አመልካቾችን በምዝገባ ላይ ይገኛል።   ትምህርት ክፍሉ ባሁኑ ሰዓት በመ...
08/03/2026

አስደሳች ዜና


በ2ኛ ዲግሪ በConstruction Engineering and Management ትምህርት ዘርፍ አመልካቾችን በምዝገባ ላይ ይገኛል።


ትምህርት ክፍሉ ባሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛው መርሃግብር በሁሉም ባቾች ተማሪዎች ያሉት ሲሆን እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ሁለት ባች የመደበኛ እና አንድ ባች በክረምት መረሀ ግብር ተማሪዎች እያስተማረ ይገኛል።

በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ቀኑ ሳያልፍባችሁ ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ ስንል በድጋሜ እናሳስባለን።

ለበለጠ መረጃ
www.wldu.edu.et

Address

Sheh Halamudin Street
Woldia
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CoTm Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to CoTm Association:

Share