የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Wereta
  • የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office

የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office ይህ Page የፎገራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት official ገጽ ሲሆን የወረዳው የትምህርት ጉዳዮች የሚንፀባረቁበት ነው።

የ2018 ዓ.ም ክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ይመለከታል👇ፎገራ የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office  እና ሌሎችም...
17/05/2026

የ2018 ዓ.ም ክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ይመለከታል👇ፎገራ የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office እና ሌሎችም ይመለከታል። ላልደረሰ አድርሱ።👇

በፎገራ ወረዳ በትምህርት ጥራት ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም በድምቀት ተካሄደ! 📑✨በፎገራ ወረዳ በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታትና የትምህርት ጥራ...
11/05/2026

በፎገራ ወረዳ በትምህርት ጥራት ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም በድምቀት ተካሄደ! 📑✨
በፎገራ ወረዳ በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሲካሄዱ የቆዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት የወረዳ አቀፍ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ከየጉድኝት ትምህርት ቤቶቹ የተመረጡ ምርጥ የጥናት ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን፤ የመምህራን ማህበር አመራሮች፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። 🤝🎓
🏆 የውድድሩ ውጤትና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት
የቀረቡትን ጥናቶች በጥልቀት በባለሙያዎች ሲገመገሙ ቆይተው፣ በሁለት ዘርፎች የሚከተሉት መምህራን የደረጃ አሸናፊ በመሆን ተሸልመዋል፦
1️⃣ በድርጊታዊ ጥናት (Action Research):
• 🥇 1ኛ ደረጃ፦ መምህር አየነው አደመ (ከሻጋ ጉድኝት)
• 🥈 2ኛ ደረጃ፦ መምህር አግማስ አዱኛ (ከኖራ መንደር ጉድኝት)
• 🥉 3ኛ ደረጃ፦ መምህር ያየሰው ክንዱ (ከበበክስ ጉድኝት)
2️⃣ በመሰረታዊ ጥናትና ምርምር (Basic Research):
• 🥇 1ኛ ደረጃ፦ መምህር የቆየ አደባባይ (ከምንጡራ ጉድኝት)
የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤትና የመምህራን ማህበር ለአሸናፊዎቹ የማበረታቻ ሽልማት ያበረከቱ ሲሆን፣ ለተሳታፊ መምህራንና ለዳኞችም የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል። 📜🎁
📢 ማሳሰቢያ፦ ለአሸናፊዎችና ለተሳታፊዎች በሙሉ አጠቃላይ ዝርዝር ግብረ-መልስ በቀጣይ ሳምንት የሚላክ መሆኑን እንገልጻለን።
የቀጣይ አቅጣጫ፦ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ መምህራን በቀጣይም ትኩረታቸውን በድርጊታዊ ጥናትና ምርምር ላይ በማድረግ፣ በክፍል ውስጥ በመማር-ማስተማር ሂደት የሚያጋጥሙ ተጨባጭ ችግሮችን በምርምር የመፍታት ልምዳቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
የእውቀት ባለቤት መምህር ለሀገር ብርሃን ነው! 💡🇪🇹
🎓

አዲስ መጸሐፍ ምርቃት በወረታ ከተማ! 📚✨በደራሲ ይበልጣል ጓዴ አሰፋ የተሰናዳው  # “ልበ-ብር” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።በዕለቱ  #አንጋፋ  #ደራሲያን፣  #የኪነ-ጥ...
10/05/2026

አዲስ መጸሐፍ ምርቃት በወረታ ከተማ! 📚✨

በደራሲ ይበልጣል ጓዴ አሰፋ የተሰናዳው # “ልበ-ብር” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።

በዕለቱ #አንጋፋ #ደራሲያን፣ #የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን እና የሥነ-ጽሑፍ ቤተሰቦች የሚታደሙበት ሲሆን፤ እርሶም የዚህ ፕሮግራም አካል እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

📅 ቀን፦ ግንቦት 8/2018 (ቅዳሜ)
📍 ቦታ፦ #ወረታ ከተማ፣ #ብራንድ ሆቴል አዳራሽ
🕒 ሰዓት፦ ከ7:00 ሰዓት ጀምሮ

የቃላት ማዕድ ተዘርግቷል፤ የእርሶ መገኘት ለዝግጅቱ ድምቀት ነው።
#ለማበረታታት አይቀርም!

#ጥሩ ጊዜም እንመኛለን

#ምርቃት #ወረታ #ኪነጥበብ

Address

Woreta
Wereta

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የፎገራ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት/Fogera Woreda Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share