Damota Wolayta Farmers' Cooperative Union L/L

Damota Wolayta Farmers' Cooperative Union L/L ይህ ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁ/ገ/ኀ/ሥራ ዩኒየን ኃላ. የተወሰነ ትክክለኛ የፌስቡክ ፔጅ ነው።ገፁን ላይክና ሼር በማድረግ መረጃዎችን በየዕለቱ ይከታተሉ::

17/06/2025

Official website link

ዳሞታ የወላይታ ገ/ሁ/ህ/ሥ/ዩንዬን 20ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በሠላም መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋና ፕሮግራም አካሂዷል።የወላይታ ዞን ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት፣የዩን...
17/06/2025

ዳሞታ የወላይታ ገ/ሁ/ህ/ሥ/ዩንዬን 20ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በሠላም መጠናቀቁን ተከትሎ የምስጋና ፕሮግራም አካሂዷል።
የወላይታ ዞን ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት፣የዩንዬኑ ቦርድ አመራር፣ የዩንዬኑ ማኔጅመንት አካላት፣ የጉባኤ ዝግጅት ኮሚቴ፣ የዩንየኑ ቴክኒክ ኮሚቴ እና የዩንዬኑ ሠራተኞች በተገኙበት በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ኅብረት ስራ ዩኒዬን 20ኛ ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን እያካሄደ ነው::ዩኒዬኑ በውስጡ 73 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባላትን ያቀፈ ሲሆን ከ33 ሺህ 5...
14/06/2025

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ኅብረት ስራ ዩኒዬን 20ኛ ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን እያካሄደ ነው::
ዩኒዬኑ በውስጡ 73 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባላትን ያቀፈ ሲሆን ከ33 ሺህ 500 በላይ አባላት አሉ።

ለዩኒዬኑ አሁን ያለው አጠቃላይ ካፒታል ከ60 ሚሊዮን 542 ሺህ በላይ ያለው ሲሆን የአከባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ በማድረግ እና በሚያቀርቡት ምርት ላይ እሴት በመጨመር የተሻለ ዋጋ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራም ይገኛል።

በጉባኤው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም፣ የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳንኤል ዳሌን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒዬኑ ስራ አመራር አካላትና አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

13/06/2025
 የፊታችን ዓርብ ማለትም 04/04/2017 ዓ/ም ይታሸጋል
10/12/2024


የፊታችን ዓርብ ማለትም 04/04/2017 ዓ/ም ይታሸጋል

ከ64 ሚሊየን በላይ ብር እየተገነባ ያለው የሜካናይዜሽን ማዕከል ግንባታ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ተገመገመወላይታ ሶዶ፤ህዳር 27/2017 የዳሞታ ወላይታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን እና የ...
06/12/2024

ከ64 ሚሊየን በላይ ብር እየተገነባ ያለው የሜካናይዜሽን ማዕከል ግንባታ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ተገመገመ

ወላይታ ሶዶ፤ህዳር 27/2017 የዳሞታ ወላይታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ATI ከ64 ሚሊየን ብር በላይ ካፕታል ወጭ በጋራ የሚያስገነቡት የሜካናይዜሽን ማዕከል ግንባታ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ተገምግሟል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጰጥሮስ ወ/ማሪያም ሜካናይዜሽን ማዕከል ግንባታ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን መለየትና መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።

ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እስከሚሆን ድረስ የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግና በግንባታ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን አቅም በፈቀደ መልኩ ለመፍታትም ቁርጠኛ መሆኑንም ገልፀዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል የሜካናይዜሽኑ ማዕከል ለአካባቢው አርሶአደሩ የሚያበረክተው ፈይዳ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

የግንባታው መጓተት ምክንያቶችን መለየትና መፍታት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዘውዱ ለዚህም የባለድርሻ አካላት ቅንጅት መጠናከር እንደሚገባም አመላክተዋል።

የሜካናይዜሽኑ ዋና ዓላማ ግብርናውን ማዘመን የሚያስችሉ የስልጠና ማዕኬል፣ የእርሻ ማሽኖች የጥገና አገልግሎት መስጫ እንዲሁም የመለዋወጫ ዕቃዎችን ለአርሶ አደሩ በአቅራቢያው ለማቅረብ ታስቦ እየተሰራ እንደሚገኝ በመድረኩ ተመላክቷል።

የዳሞታ ወላይታ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ከኢትዮጵያ የግብርና ሜካናይዜሽን ኢንስቲትዩት ATI በጋራ የሚገነባው የሜካናይዜሽን ፕሮጀክት ግንባታ መጓተት በማስመልከት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የሜካናይዜሽን ማዕከል ግንባታ ሂደትን ለማቀላጠፍ ዩኒየኑ በ2013 ዓ.ም ከATI ጋር በጋራ በመሆን ከኤን ኤን ዲ ከተባለ ህንፃ ተቋራጭ ውል ተገብቶ ስራ የጀመረ ቢሆንም የስራ ተቋራጭ ድርጅቱ በወቅቱ በፋብርካ ምርቶች የዋጋ መናር ምክንያት ግንባታውን ማቋረጥ መቻሉ ተጠቁሟል።

የግንባታ የአሰራር ህደትን በመከተል ዩኒየኑ ከዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባኒያ ጋር አዲስ ውል በመግባት ወደ ስራ የተገባ ስለመሆኑም በሪፓርቱ ተመላክቷል።

የሜካናዜሽን ማዕከል ግንባታ ስራ ተግባራዊ ለማድረግ ዩኒየኑ በቁጥር 2 (ሁለት) የእርሻ የትራክተር ማሽን ግዢ በመፈፀም ለአርሶአደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ችሏል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ህደት መፋጠን እንዲችል የፈደራል ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ቀደም ሲል ከድጋፉ በጀት አካል የነበረ የ9.4 ሚሊየን ብር ለመልቀቅ ቃል የተገባ ሲሆን የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ቀሪ በጀቱን መሸፈን እንዲችል መግባባት ላይ ተደርሶበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ የወላይታ ዞን የአስተባባሪ አካላትን ጨምሮ ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ሕብረት ሥራ ዩንየን፣ የፌደራል ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት፣ የወላይታ ዞን ሕብረት ሥራ ጽ/ቤት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተሳትፈውበታል።

18/06/2024
https://www.damotawfcu.org.et/images/
15/06/2024

https://www.damotawfcu.org.et/images/

Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services Our Services O...

ሰራዎቻችን.....
15/06/2024

ሰራዎቻችን.....

Address

Wolaitta S**o
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Damota Wolayta Farmers' Cooperative Union L/L posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share