Habtamu W/Mariam Gobebo

Habtamu W/Mariam Gobebo News and Media Company

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን ሕግ ጥሶ ከእግዚአብሔር ጋር የታጣላው ራሱ የሰው ልጅ ነበረ፡፡ ዕርቅን አውርዶ ሰላምን ለማስፈን በረት ድረስ...
06/01/2025

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን ሕግ ጥሶ ከእግዚአብሔር ጋር የታጣላው ራሱ የሰው ልጅ ነበረ፡፡ ዕርቅን አውርዶ ሰላምን ለማስፈን በረት ድረስ የመጣው ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ አሸናፊ፣ የሚሳነው አንዳች የሌለ ነው፡፡ ነገር ግን ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል ወደ ማይገባው ሥፍራ መጣ፡፡ አሸናፊ ቢሆንም እንደ ተሸናፊ ሆነ፡፡ ዐቅም ቢኖረው እንደ ዐቅመ ቢስ ሆኖ ታየ፡፡ በሁሉ ሀብታም ሲሆን፣ ራሱን ታናሽ አደረገ፡፡ ይህ ሁሉ ለዕርቅና ለሰላም የተከፈለ የታላቅነት ዋጋ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል በደካማዋ ከተማ በቤተልሔም፣ በተናቀችው ሥፍራ በበረት መገኘቱ የገባቸውም ያልገባቸውም ነበሩ፡፡ የገባቸው፤ ከሰማየ ሰማያት ወርደው “ሰላም እና ዕርቅ በምድር ይሁን” ብለው ዘመሩ፡፡ የገባቸው፤ ከምሥራቅ ኮከቡን አይተው፣ እጅ መንሻውን ይዘው መጡ፡፡ የገባቸው፤ በረታቸውን ለቅቀው ለድንግል ማርያም እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጡ፡፡ የገባቸው፤ የሰማይ መላእክቱን ተከትለው ወደ በረት ሄደው እርቅና ሰላምን አመሰገኑ፡፡

ያልገባቸው ሰዎች፣ የዕርቅ እና የሰላሙ ዐዋጅ እየታወጀ እነርሱ ግን ተኝተው ነበር፡፡ የመንደር ጌቶች እነ ሄሮድስ፣ የሰው ልጅ ሰላም ማግኘት ሳይሆን ከጠላት ያገኙት ሥልጣን ያስጨንቃቸው ነበር፡፡ የይሁዳ ሰዎች፤ ዓለም በማይመለስበት ሁኔታ እየተቀየረ፣ እነርሱ ግን እየሆነ ያለውን ለውጥ አያዩም አይሰሙም ነበር፡፡ ከሰማይ መላእክት ወርደው፣ ከምድር እረኞች ነቅተው ተአምር ሲሠራ፤ እነርሱ ግን በዕንቅልፍ ደንዝዘው ነበር፡፡እ ነርሱ እያንቀላፉ ከተማቸው ቤተልሔም ተቀይራለች፡፡ የእንጀራ ቤት ሆናለች፡፡ ታሪኳ ተቀይሯል፡፡ ታናሽ ከተማነቷ ተቀይሯል፡፡

ያልገባቸው፣ ሰላምና ዕርቅ ሲባሉ የድካምና የዐቅመ ቢስነት ምልክት አድርገው ተመለከቱት፡፡ ሰይፍና ጎራዴ የለመዱ፤ መግደልና ማጥፋት ጀግንነት የሚመስላቸው ነበሩና፡፡ ሰላም ድካም፣ ዕርቅም ሽንፈት ይመስላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ከመሸ፣ በከብቶች በረት ለሁሉ የመጣውን ሰላም አቅለው አንቀበልም አሉ፡፡ እነ ሄሮድስ ሰይፍ መዘዙ፡፡ ሰላምን አሳደዱ፤ ሰላማዊ ሕጻናትንም ፈጁ፡፡ ሄሮድስ የገዛ ሕዝቡን ለመጨፍጨፍና ለመግዛት በጠላት የተሾመ ሰው ነበር፡፡ የሚያስፈጽመው የእሥራኤል ጠላቶችን ዓላማ ነበረ፡፡

ይሄንን በዓል የምናከብር፤ ወይ ሰላምና ዕርቅን ከሚወዱት ወገን ነን፡፡ አለያም ሰላምንና ዕርቅን ከሚያሳድዱት ወገን ነን፡፡ መንግሥት ሰላምና ዕርቅን ደጋግሞ የሚያውጀው ዐቅም ከማጣት፣ ጉልበቱ ከመድከም የተነሣ አይደለም፡፡ ሁሉም ዓይነት መንግሥታዊ ዐቅሞች በእጁና በደጁ አሉ፡፡ ሰላምና ዕርቅ ግን ከሁሉ በበለጠ፤ ዘመን አሻጋሪ፣ ታሪክ ቀያሪ፣ የችግርና መከራ ዘመን ማብቂያ መፍትሔዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ሁሉን አሸናፊ፣ ሁሉን አሻጋሪ ያደርጋሉ፡፡ ጠባሳ ሳይተዉ ቁስልን ያሽራሉ፤ ለልጅ ልጅ ቂምን ሳይሆን ሐሴትን ያወርሳሉ፤ ከመጠፋፋት ይታደጋሉ፡፡ የሰላምና የዕርቅ መንገድ የሚመረጠውም ለዚህ ነው፡፡

ሰላምና ዕርቅን መምረጥ፤ የኃያል ባለ-ራዕይ፣ የፍጹማዊ-አሸናፊና ባለታላቅ-ዐቅም በውዴታ የሚሸከመው የከፍታ ግዳጅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ሰላምን እያወጀ ወደ ከብቶች በረት የመጣው ግን እርሱ ኃያሉ ነው፡፡ የአዳም ልጆች በሠገነት ሲወለዱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በበረት የተወለደው፡፡ እግዚአብሔር ነው ለሰላምና ለዕርቅ ሲባል ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ መከራን የተቀበለው፡፡
መንግሥት ዛሬም ለሰላም እና ለዕርቅ እጁ እንደተዘረጋ ነው፡

በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የቮልካኖ ፍንዳታ ተከሰተ ታሕሣሥ 25፣ 2017  ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ...
03/01/2025

በዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የቮልካኖ ፍንዳታ ተከሰተ

ታሕሣሥ 25፣ 2017 ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የቮልካኖ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የሟጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው÷ የቮልካኖ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው (FBC)

29/10/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mamila Man, Siyon Siyo

በዛሬው እለት ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፓታታ ቀበሌ በደረሰዉ ትራፍከክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች እግዝአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንድያኖርልን፣ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናና...
25/09/2024

በዛሬው እለት ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፓታታ ቀበሌ በደረሰዉ ትራፍከክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች እግዝአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንድያኖርልን፣ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናቱን እንድሰጣቸው እመኛለሁ።

😭😭😭

ዮ ዮ ጊፋታ 🌻🌻    እንኳን ለ2017 ዓ.ም የወላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ «ጊፋታ» በዓል በሠላም፣ በደስታ፣ በፍቅር አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! 🌻🌻ዮዮ ጊፋታ 🌻🌻በወላይታ ብሔር ዘንድ በታላቅ...
18/09/2024

ዮ ዮ ጊፋታ 🌻🌻
እንኳን ለ2017 ዓ.ም የወላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ «ጊፋታ» በዓል በሠላም፣ በደስታ፣ በፍቅር አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! 🌻🌻ዮዮ ጊፋታ 🌻🌻

በወላይታ ብሔር ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ ታላቅ የብሔሩ የማንነት መገለጫ ነው-ጊፋታ። የአሮጌ ዓመት ማብቂያ፥ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ እንዲሁም የመጀመሪያው ወር መጠሪያ የበኩርነት መገለጫ እንዲሁም "ጊፋታ" ባይራ (ታላቅ) መሆንን ያመላክታል።

በሌላ መልኩ በወላይታ ብሔር ዘንድ ጊፋታ «መሻገር» ማለት ሲሆን፤ ከአሮጌ ዓመት ወደ አዲስ ዓመት፥ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከአሮጌ ወደ አዲስ መንፈስ የምንሻገርበት በተለይም ጥላቻን በፍቅር የምናሸንፍበት፤ ሠላምና እርቅ የምናወርድበት፤ ወንድማማችነትን የምናጎለብትበት፤ በመተሳሰብ፥ በመደጋገፍ፥ በመቻቻል፥ በአብሮነት፥ ይቅር በመባባል ወደፊት የምንዘልቅበት የአዲስ ዘመን ብስራት ነው።

በወላይታ ብሔር ዘንድ “ጊፋታ” ከመስከረም ወር ብሔሩ ዘመን አቆጣጠር መሠረት ባለው አንዱ እሁድ "በጉጉት" "SHUHA WOGA" ትርጉሙም የእርድ እሁድ ማለት ነው። ጊፋታ በከፍተኛ ዝግጅት በየዓመቱ የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን፤ ቂም በይቅርታ የሚታለፍበት፤ ዕዳ የሚከፈልበት፤ አዲስ ልብስ የሚለበስበት፥ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት ወደ አዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስ የሚሻገሩበት ድንቅ በዓል ጭምር ነው።

የመጀመሪያው ወር መጠሪያ፥ የበኩርነት መገለጫ፥ የዕርቅና የሰላም ማውረጃ የሆነውን የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓልን ስናከብር በወንድማማችነት፣ በመተሳሰብ፣ በመደጋገፍ፣ በመቻቻል፣ በአብሮነት፣ ይቅር በመባባል እንዲሁም ስለ ሠላም ስንል እጅ ለእጅ ተያይዘን በአብሮነት የምንዘልቅበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ

በመጨረሻም ቀደምት የወላይታ ብሔር አባቶች ያቆዩት ጊፋታ የዳበረ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴትነቱ ተጠብቆ የበለጠ ማበልጸግና ማልማት ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ እንዲቀጥል መላው ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ እየጠቆምኩኝ፤ አሁንም በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

🌻🌻መልካም የጊፋታ በዓል!🌻🌻
ሀሹ ሳሮ ጋቴስ🌻🌻
ዮዮ ጊፋታ 🌻🌻

11/09/2024

እንኳን በሠላም ተሸጋገርን ተሸጋገራችሁ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

2017 ዓ.ም መልካም ምኞታቸውን የሠላም ፣ የፍቅርና የመቻቻል ያላችሁ በሙሉ ሰላምና ፍቅር በመሆን አርዓ እንድትሆኑ አደራ ማለት ፈልጋለሁ።

መልካም በዓል 🌻🌻

ባንቴ ልፋትና ውጤት የመጣ ምንም ወርቅ የለም እንደውም!ተጠባባቂ ያደረከው ልጅ ነው የመጣው!  ዘራፊ ሁላ!👊👊
14/08/2024

ባንቴ ልፋትና ውጤት የመጣ ምንም ወርቅ የለም እንደውም!
ተጠባባቂ ያደረከው ልጅ ነው የመጣው!
ዘራፊ ሁላ!👊👊

የሟቾች ቀጥር ከ146 በላይ መድረሱ ተገለፀ #ጎፋ: በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ እስካሁን የሟቾች ቀጥር ከ146 በላይ መድረሱ ተገለ...
23/07/2024

የሟቾች ቀጥር ከ146 በላይ መድረሱ ተገለፀ

#ጎፋ: በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ እስካሁን የሟቾች ቀጥር ከ146 በላይ መድረሱ ተገለፀ።

የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እና አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ መልሶ ማቋቋሚያ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ፌተና አደጋውን አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ

ወንድ 96 እና
ሴት 50
በድምሩ የ146 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል።

የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
አቦ ታሳ!
Taasa Tanamo!

በዓለም ታርክ ከመጫወታቸው በፊት የተጠናቀቀ የመጀመሪያው ጨዋታ ልሆን ይችላል።ከበሰበሰው ፈደሬሽን የበሰበሰ ውሳኔ ልተላለፍ ስለምችል  የሚመለከተው አካል አህ ፍታዊነትን በመቃወም የድርሻችሁን...
08/07/2024

በዓለም ታርክ ከመጫወታቸው በፊት የተጠናቀቀ የመጀመሪያው ጨዋታ ልሆን ይችላል።
ከበሰበሰው ፈደሬሽን የበሰበሰ ውሳኔ ልተላለፍ ስለምችል የሚመለከተው አካል አህ ፍታዊነትን በመቃወም የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ።
ለማነኛውም የጦና ንቦች ኮርተንባችኋል አሸናፊዎችም ናችሁ

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habtamu W/Mariam Gobebo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Habtamu W/Mariam Gobebo:

Share