21/05/2026
🎒 7 ፈገግታዎች፣ 1 ታላቅ እርምጃ ወደፊት! 🎒
ዪልድ ኢትዮጵያ (YIELD Ethiopia) «አንድ ማዕድ ብቻ» (Just One Meal - JOM) የተሰኘውን አዲስ የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምሯል!
ዛሬ ጉዟችንን ከ7 ህፃናት እና ታዳጊዎች ጋር የጀመርን ሲሆን፣ ለእነዚህ ልጆች ትኩስና አልሚ ምግብ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በነፃነት የሚስቁበት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የሚረዱበት እና በነገ ብሩህ ተስፋቸው ላይ የሚያተኩሩበት አስተማማኝና ምቹ ቦታ ፈጥረናል።
በክልላችን በርካታ ህፃናት ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች (multi-dimensional deprivations) የሚጋፈጡ በመሆኑ፣ አልሚ ምግብ ማግኘት መሰረታዊ ሰብአዊ መብት መሆኑን በተግባር ለማሳየት ቆርጠን ተነስተናል።
ዛሬ በክፍሉ ውስጥ የነበረው የልጆቹ ደስታ እጅግ ልብ የሚነካ እና ውብ ነበር። በደቡብ ኢትዮጵያ የህፃናትን ጥበቃ፣ ትምህርት እና የተመጣጠነ ምግብ ተጠቃሚነትን ለማስፋፋት ለምናደርገው ሰፊ ጉዞ ይህ የመጀመሪያው ስኬታችን ብቻ ነው። በዚህ ቅዱስ ዓላማ ላይ አብራችሁን ስለቆማችሁ ከልብ እናመሰግናለን! 🙏✨
🎒 7 Smiles, 1 Major Step Forward! 🎒
YIELD Ethiopia has officially launched the Just One Meal (JOM) initiative!
We started today with 7 children and teenagers, providing them not just with a hot, nutritious meal, but with a safe space where they can laugh, feel protected, and focus on their future.
With many of children in our region facing deep multi-dimensional deprivations, we are determined to show that access to nutrition is a fundamental human right.
The joy in the room today was absolutely beautiful. This is only the first milestone of many as we scale up child protection, education, and nutrition in South Ethiopia! Thank you for walking this path with us. 🙏✨