Menze Guassa Community Conservation Area office

Menze Guassa Community Conservation Area office Menze Guassa Community Conservation Area page

ክፍለ-2በቃላቸዉ መሰረት ወዲያዉኑ ጌራ ወደ ደቡብ  አስቦም ወደ ሰሜን ጫፍ  በመሄድ ሰፈሩ፡፡የዉድድር ዝግጅቱ ቀጠለ፤ቅልብ ፈረሶቻቸዉን ጓሳዉ ዉስጥ በመልቀቅ እንዲግጡ  ተደረጉ፡፡ከጓሳዉ ወደ...
07/04/2026

ክፍለ-2

በቃላቸዉ መሰረት ወዲያዉኑ ጌራ ወደ ደቡብ አስቦም ወደ ሰሜን ጫፍ በመሄድ ሰፈሩ፡፡የዉድድር ዝግጅቱ ቀጠለ፤ቅልብ ፈረሶቻቸዉን ጓሳዉ ዉስጥ በመልቀቅ እንዲግጡ ተደረጉ፡፡ከጓሳዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ የገብስ ጥሬ እየተሰጣቸዉ ሲቀለቡ ቆዩ፡፡ፈረሶቹ በድሎት ከመቀለባቸዉ የተነሳ ጥጋበኛ በመሆናቸዉ ለጅብ እንኳ የማይቀመሱ ጥጋበኛ ቅልቦች ሆኑ፡፡ፈረሶቹ አልፎ አልፎ ለማሟሟቅ ሲጋልቧቸዉ ልጓም የማይገዛቸዉ አልንጋ የማያርፍባቸዉ ሽምጥ ሯጭ ሆኑ፡፡በዚህ መሰረት ጌራ እና አስቦ በአረፋበት ሆነዉ የሚጋልቡበትን መንገድ ሲያጠኑና ሲመረምሩ ፈረሶቻቸዉን ገብስ ሲቀልቡ ሰነበቱ፡፡
ቀኑም ደረሰ ጌራ ከደቡብ አስቦም ከሰሜን ጫፍ ፈረሶቻቸዉን ጎህ ሳይቀድ ጭነዉ የፀሐይ መዉጫ ላይ አይኖቻዉን ተክለዉ መጠባበቅ ያዙ፡፡ትልቅ ዉድድር ትልቅ ፋክክር የርስት ማሰከበር ጉዳይ ቢሆንም ያለፊሽካ ያለሩጫ ማሰጀመሪያ ሽጉጥ ያለመነሻ መስመር ያለዳኛ በእምነት ብቻ ዝም ብለዉ የፀሐይቱን መዉጣት መጠባባቅ ጀመሩ፡፡ተፈጥሮ ኡደቱን አይስትምና ፀሐይቱ የእሳት አለሎ መስላ በምስራቅ የተራሮች አናት መሐል ዉስጥ ስትወጣ አስቦ በጥቁር ቦራ ፈረሱ ጌራ በጥርኝ ፈረሱ ላይ ወጥተዉ መጋለብ ጀመሩ፡፡ፈረሶቻቸዉ ቁጥቋጦዉን ጉድባዉን ጥሻዉን እየዘለሉ ሲጋልቡ አርካቡ ላይ ቆመዉ ሰዉነታቸዉን ከፈረሶቻቸዉ ጋር ልክክ አድርገዉ ይሰፋታል ገላጣ ሜዳ ሲያገኙ ደግሞ የሰዉ ዘር በማይታይበት በዚያ ዘመን ጠፈፍ ባለዉ በህዳር ወር መሬት ላይ እንዲህ እያለ ይፎክራሉ
ጌራ፡ የጥርኝ ጌታ ጌራ ቀጭኑ
ጉዳዩ አይደለም ጓሳና ደኑ፡፡
እንኳን በልጓም አዝምሮ ገብሱ
ድንበሩ አይቆምም ተኝቶ ነፍሱ እለ ሲጋልብ
አስቦም በበኩሉ እንዲህ ሲል ይፎክራል
ቦራ ፈረሴ አትዘናጋ
ለዘሮቻችን ታሪክ ይወጋ፡፡
የጌራ ወንድም እህል የያዘዉ
በፈረሱ እግር ጓሳዉን ወቃዉ፡፡
እንዲህ እያሉ እየፎከሩ አስቦ እና ጌራ መንገዱን ቋጥኙን እንደ ቋያ እሳት እየገሰገሱ ጉዞዉን ለበለቡት፡፡ጓሳዉ ላይ ያረበበዉ አመዳይ እና ጤዛ እረግፎ የፀሐይ ሙቀት ሰዉነትን ለማፍታታት ሲደርስ ወንድማማቾቹ ከሁለት አቅጣጫ መጥተዉ ዲጃ ወንዝ ወይም ድጃ አፋፍ ተገናኙ፡፡የፈረሶቻቸዉ አፍ ደም የቀላቀለበት አረፋ ይደፍቅ ነበር፡፡ሁለቱም ከፈረሶቻቸዉ ጀርባ ላይ ተፈናጥረዉ እግራቸዉ መሬት ሲነካ አንድ ሆነዉ ተቃቅፈዉ ተሳሳሙ፡፡ ፈረሶቻቸዉ ደግሞ አፍና አፋቸዉን ገጥመዉ በትኩስ ትንፋሻቸዉ ተገፋፉና በፊት የቀኝ እግራቸዉ መሬቱን ድቅ ድቅ በማደረግ ይፍሩት ገቡ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌራ የእናቴ ልጅ ይኽ ነገር ከፈጣሪ ነዉ የርስታችን ድንበር ለይተዉ እንስሳቶቹ ምልክት አበጁበት ሲለዉ አሰቦ ፈገግ አለና ጌራን መልሶ አቀፈዉ፡፡ጓሳዉ ተለካ በዚህ መሰረት ለካስ የአስቦ ፈረስ ጉልበቱ ፍጥነቱ የተሻለ ኖሮ የአስቦ ይዞታ ከጌራ ይዞታ በልጥ ብሎ ተገኘ፡፡
አሁን ድረስ የአስቦ ጓሳ በለጥ ይላል ስሙም የአራድማ ጓሳ በመባል ይታወቃል፡፡የጌራ ደግሞ አነስ ይላል፡፡

መንዝ ጓሳ!!                                     ክፍለ-1                  የመንዝ ጓሳ የማህበረሰበ ጥብቅ ስፍራ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ...
07/04/2026

መንዝ ጓሳ!!
ክፍለ-1
የመንዝ ጓሳ የማህበረሰበ ጥብቅ ስፍራ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ውስጥ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የሚገኝ ጥብቅ ስፍራ ሲሆን ከባህር ዳር በ779ኪ.ሜ ፣ከአዲስ አባባ በ265 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ፣ከደ/ብረሃን ከተማ በ165ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ይህ ጥብቅ ስፍራ ላለፉት 400ዓመታት በማህበረሰቡ ሲጠበቅ የኖረ ድንቅ ውብ እና ማራኪ መልከዓምድር ያለው እንዲሁም ብርቅዬና ሌሎች የዱር እንሰሳትን ፣እፅዋትንና አዕዋፍን በ ውስጡ ይዞ ይገኛል፡፡
የመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ስያሜውን ያገኘው በጥብቅ ስፍራው ከሚበቅለው እና ከጠቅላላ ስፋቱ ዉስጥ 19% የሚሸፍነው የጓሳ ሳር ነው፡፡
ጓሳ በደጋ የሚበቅል የሳር ዝርያ ሲሆን በህዳር፣ታህሳስና ጥር ደረቅ ይልና በየመሃሉ አንገታቸውን አስገው በበቀሉ ልዩ ልዩ አበባዎች የቁንጅና ውድድር የሚያደርጉበት መድረክ ያስመስሉታል ፡፡የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መናገሻ ከሆነችው የመሐል ሜዳ ከተማ ደርሰው ከማረፍዎት በፊት በጥብቅ ስፍራው ውስጥ ያሉትን ሸንተረሮች ሰዓሊ በብዕሩ የተጠበበት ስዕል ዕንጂ በአይን እይታ መሆኑን ያጠራጥራል፡፡ሸለቆውና ተራራዉ እንዲሁም ቁልቁለቱ ለተመለከተው እውቅ ልብስ ሰፊ ተጨንቆና ተጠቦ የሰራው ሽንሽን ቀሚስ እንጂ ………….
የመንዝ ጓሳ ጥብቅ ስፍራ ከ17ኛዉ ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በሁለት ወንድማማቾች አስቦና ጌራ በተባሉ ወንድማማቾች ያንን ጊዜ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ባልተስፋፋበት እንዲህ ትምህርት ባልተስፋፋበት የአካባቢዉን ማህበረሰብ በማስተባባር ወደፊት የተፈጥሮ ሃብት ዉድመትና መጥፋት ለማህበረሰቡ መቅሰፈትና ፈተና እንደሚሆን በመረዳት ፣ማስጠበቅ አንደጀመሩ ይነገራል፡፡የመንዝ ጓሳ አንድ የሆነ መጠሪያ ክልል ስም ያለዉ መሆኑ ቢታወቅም በወቅቱ በሁለት ክፍልና በሁለት ዋና ዋና ስሞች ይታወቃል፡፡ ይኸዉም የጌራና አስቦ በመባል ይታወቃሉ፡፡፡ጌራና አስቦ ወንድማማቾች ሲሆኑ ወንድማማቾቹ ያን ጊዜ ወደ መንዝ ጓሳ እንደመጡ ጓሳው ውስጥ ውሎ በማደር ከጫፍ ጫፍ ዞረው ተመለከቱት ፡፡በቃ! ይህ ድንቅ የተፈጥሮ ሃብት ጋራዉ ሸንተረሩን ወንዙም ሜዳዉን አእዋፋቱን የዱር እንስሳቱን ተመልክተዉ ይህማ የፈጣሪ ስጦታ ድንቅ ነዉና ለምን አናስጠብቀዉም ብለዉ በአንደ ቃል ተስማሙ፡፡
ከዚህ ቦታ ውጭ ለከብቶቻቸው፣ለልጆቻቸው፣ለጠቅላላ ቤተሰቡ የተመቸ ቦታ እንደማያገኙ ለአፍታም አልተጠራጠሩም የቀራቸው ነገር ቢኖር የየግል ይዞታቸውን መከለል ብቻ ሆነ፡፡ወንድማማቾቹ በጓሳው ትንሽ ከሰነባበቱ በኋላ የእንከፋፈል ጥያቄ ተነሳና በየት በኩል ትፈልጋለህ አንተ መጀመሪያ ምረጥ አረ በፍፁም በመባባል ሲባባሉ ቆዩና ብዙ ጊዜ ከተነጋገሩ በኋላ ወደ ስምምነት የሚያደርስ ሃሳብ የሚያመጣው አስቦ እንዲህ የሚል ሃሳብ አቀረበ፡፡ወንድሜ ጌራ የእናቴ ልጅ ፈጣሪ ሳይለየን አብሮ እዚህ ቦታ አድርሶናል፡፡ የእሱ ፈቃድ ሆነና እንዲህ ያለ ለመምረጥ በሚያዳግትበት ቦታ ገጠመን እንዲያው ቸኮልክ አትበለኝና አንድ ሃሳብ ነበረኝ አለ፡፡ጌራም አይ ወንድም አለም ለልጆቻችን ቅርስ ጥለን እንድናልፍ ነው እንጂ እኔማ የአንተስ ጋሻ እጅግሬ ሆኜ ብኖር ምን ገዶኝ ነበር ፡በዚያ ላይ አንድ ወንድሜ እኔን የሚጎዳ ነገር አታመጣም እስኪ ንገረኝ በሞቴ ልስማው ሃሳብክን አለው፡፡ አስቦም በወንድሙ መልስ እጅጉን ደስ አለዉ፡፡ጉሮሮዎን ከጠራረገ በኋላ አያ!እንግዳዉስ ያሰብኩት እንደዚህ ነዉ፤አለ አንተ ከደቡብ ከጓሳው ጭፍ እኔም ከሰሜኑ ጫፍ ልነሳ ።ከዚህ በኋላ ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመሰል ጠዋት ፀሐይ ከመዉጣቷ በፊት ልክ ፀሐይ በምስራቅ ተራሮች ጫፍ ላይ አንገቷን ብቅ ስታደርግ ፈረሶቻችን ላይ እንዉጣ አንተም ወደ ሰሜን አቅጣጫ እኔም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ሽምጥ እየጋለብን እንገስግስና የተገናኘንበት ቦታ ድንበራችን ይሆናል፡ ማለት ነዉ፡ ብሎ ሃሳቡን አቀረበ፡፡ጌራም ምን ገዶኝ ማለፊያ አለና ነገር ሳያበዛ ቀነ ቀጠሮ ለህዳር ማርያም ተያዘለት፡፡

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ውስጥ ቄውላ ቀበሌ ውስጥ የምትገኘው የዷት ልደታ ቤተክርስቲን።
06/04/2026

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ውስጥ ቄውላ ቀበሌ ውስጥ የምትገኘው የዷት ልደታ ቤተክርስቲን።

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአናዝ ፅድ ቀበሌ የአልሷ የየጤፍራና ፈንገለት እንዲሁም ዳርገኝ ቀበሌ የሙጃን አካባቢ የአርሶ አደሮች መንደርና መልከዓ-ምድር።
04/04/2026

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአናዝ ፅድ ቀበሌ የአልሷ የየጤፍራና ፈንገለት እንዲሁም ዳርገኝ ቀበሌ የሙጃን አካባቢ የአርሶ አደሮች መንደርና መልከዓ-ምድር።

ክፍል-4 የዱር እንስሳትበየጋና ደን ዉስጥ 15 የሚሆኑ  ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት  ዝርያዎች ተጠልለዉ ይገኛሉ፡፡ እነሱም ነብር ዝንጀሮ ሽኮኮ ጦጣ አራጅ ሸለመጥማጥ ጥንቸል አደሴ ቁኒ ዉ...
04/04/2026

ክፍል-4
የዱር እንስሳት
በየጋና ደን ዉስጥ 15 የሚሆኑ ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ተጠልለዉ ይገኛሉ፡፡ እነሱም ነብር ዝንጀሮ ሽኮኮ ጦጣ አራጅ ሸለመጥማጥ ጥንቸል አደሴ ቁኒ ዉላጋ አነር ጃርት ጅብ ሰስ ተኩላ እና በቅርብ ወደ ደኑ የመጣ ጉሬዛ ጭምሮ የሚገኙ ሲሆን በደኑ ዉስጥ ይገኛሉ›፡፡የምኒልክ ድኩላ ነበር አሁን ጠፍቷል፡፡ትናንሽ አጥቢ የዱር እንስሳት እንደ አይጥ ተሳቢ እና ተራማጅ እንስሳት የያዘ ጥብቅ ደን ነዉ፡፡

የየጋና ደን ምን ጠቀሜታ ምድነዉ?

ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር ያላቸዉ ግብግብ ዘለቄታዊ የተፈጥሮ ገጽታ መኖርን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እንዲሆን ማድረግ ያስችላል፡፡ በዚህም ዘለቄታዊ ጥቅም አለዉ
በአካባቢው ያለው ስርዓተ ምህዳር እንዳይዛባ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋል ፡፡
ለክለት ተጋላጭ የሆነው የከፍተኛ ቦታዎች ሰነምህዳር ለመጠበቅ ያስችላል፡፡
የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል ጎርፍ በአካባቢዉ እንዳይከሰት ይከላከላል የእርሻ መሬት የግጦሽ መሬት በደለል እንዳይሸፎን መንደሮች በጎርፍ እንዳይጠፋ አንዲሁም ሰብዓዊ ቀዉስ እንዳይደርስ ከመከላከል አንጻር ያለዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ፡፡
የከርሰ ምድር ዉሃ እንዲጨምር እና ምንጮች አመቱን ሙሉ እንዲፈሱ ያደርጋል፡፡በዚህም መሰረት ለሰዉ እና ለቤት እንስሳት ንፁህ መጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

ጥብቅ ደኑ ውስጥ ያለው ብዝሃ ህይወት ሳይጠፋ እንዲኖር ያስችላል
በአካባቢው የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በአይነትም ሆነ በብዛት ይጠበቃሉ፣
የዱር እንስሳትና ዕፅዋት በቦታቸው እንዲጠበቁና እንዳይጠፉ ይረዳ
የተስተካከለ የውሃ ሃብት እንዲኖር ያስችላል ከጥብቅ ደኑ የሚነሱ ምንጮችና ጂረቶች አመቱን በሙሉ እንዲፈሱ ያስችላል)

ከምርምርና ሣይንሳዊ ጥናት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን ገቢና አቅም ያጐለብታል፣
የአካባቢው የአየር ሚዛን ስለሚጠበቅ ከእርሻ ስራ የሚገኘው ገቢ ዘላቂና አስተማማኝ ይሆናል፡፡የመስኖ ስራ በማከናወን የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት ያስችላል፡፡በሌላ በኩል ለንብ እርባታ ከፍተኛ አስተዋኦ ያለዉ በመሆኑ የማር ምርት በማምረት የአርሶ አደሩን ገቢ ይጨምራል፡፡
-ለእንስሳት እርባታ የመኖ ምንጭ በመሆን ያለዉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነዉ ::
በአካባቢዉ ፍየል በማርባት የአርሶ አደሩን ገቢ ከመጨመር አንፃር ከፍተኛ ነዉ፡፡

የዱር እንሰሳትና ዕፅዋትን ባሉበት ሁኔታና በተፈተሮአዊ አኗኗራቸዉ ለሚደረግ ምርምር በማእከልነት ያገለግላል
የባህላዊ መድሃኒቶችን ደህንነት በመጠበቅና በመንከባከብ ጥቅም ላይ በማዋል ሣይንሳዊ ጥናትንም ለማካሄድ ይረዳል፡፡
በመጥፋት ላይ ላሉ የዱር እንስሳትና እጽዋት ሳይንሳዊ ምርምር ለማድረግ ያስችላል፡፡
የደኑ ገጽታዉ ለከባቢያዊ ደህንነት፤ ለብዝሃ ህይወትና ለስርአተ ምህዳር መስተካከል ያላቸዉ አስተዋጽዖ ይታወቃል በዚህ ረገድ ለሚደረጉ ምርምሮች የመስክ ላቦራቶር ሊሆን ይችላል፡፡
ተፈጥሯዊነትን ጠብቆ ለመቆየት ያስችላል፡፡ በዉስጡ ያሉትን ብዝሃ ህይወትና ሌሎች (አፈር፤ዉሃና የመሬት አቀማማጥ) በተፈጥሮአዊ ገጽታቸዉ ቆይተዉ ዘለቄታ ባለዉ መልክ ጥቅም እንዲሰጡና ተፈጥሮአዊ ይዘታቸዉ እንዳይጓደል ይረዳል፡፡
-አካባዉ አስገራሚ እና አስደማመሚ መልከዓ-ምድር ያለዉ በመሆኑ ለቱሪዝም መዳረሻነት ያለዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ፡፡
-ጥቅጥቅ ደን ያለዉ በመሆኑ ለዕይታ ማራኪ በመሆኑ
-በጥብቅ ደኑ ዉስጥ እና አካባቢ የተለያዩ ትላልቅ እና አነስተኛ ዋሻዎች ፏፏቴዎች ያሉ በመሆኑ ለሃገር ዉስጥ ቱሪስቶች ሳቢ እና ማራኪ በመሆናቸዉ:
-በጥብቅ ደኑ አካባቢ ጥንታዊ እና ታሪካዊዉ የገሜ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የመንዝ ጓሳና የአናዝ ጓሳ በዙሪያው የሚገኙ በመሆናቸው ለቱሪስት መዳረሻነቱ የላቀ ነው።
አጫጭር መረጃ በየጋና ጥብቅ ደን ዙሪያ ያዘጋጀነው በዚህ ተጠናቋል።♥♥♥♥

ክፍለ-3በየጋና ደን ወስጥ የሚገኙ ዋሻዎችና ወንዞች በተመለከተበየጋና ጥብቅ ደን ዉስጥ የተለያዬ መጠን ያለቸዉ የተፈጥሮ ዋሻዎች ሲገኙ አንዳንዶቹ ዋሻዎች የዱር እንስሳት መኖሪያ ሲሆኑ ወንዞች...
02/04/2026

ክፍለ-3
በየጋና ደን ወስጥ የሚገኙ ዋሻዎችና ወንዞች በተመለከተ
በየጋና ጥብቅ ደን ዉስጥ የተለያዬ መጠን ያለቸዉ የተፈጥሮ ዋሻዎች ሲገኙ አንዳንዶቹ ዋሻዎች የዱር እንስሳት መኖሪያ ሲሆኑ ወንዞች በተመለከተ የሰረና ወንዝ በጥብቅ ደኑ ዉስጥ ረጅሙ ወንዝ ሲሆን አመቱን ሙሉ ፍሰት ያለዉ ወንዝ ሲሆን ሌሎች አጫጭር ወንዞች እና ፏፏቴዎች በክረምት ወቅት ብቻ የዉሃ ፍሰት ያላቸዉ ሲሆኑ ቀልብን የሚሰቡ ፏፏቴዎችን የያዘ ጥብቅ ደን ነዉ፡፡
የተፈጥሮ ዋሻዎችን በተመለከተ የአቦ ዋሻ ፣ዳራ ዋሻ፣ ምድር ዋሻ፣ ዘርጥ እንቧይ ዋሻ ፣ጨን ዋሻ፣ ሉዋበር ዋሻ(በመጠኑ ሰፊዉ ዋሻ) ፣አቡዬ ሸንጎ ዋሻ፣ የንቀሎ ዋሻ፣ ልዝቢት ዋሻ፣እሪቅ ዋሻ(በሆነ ጊዜ የካባቢዉ ማህበረሰብ በዋሻዉ ዉስጥ የእህል ዉጤቶችን በዋሻዉ ዉስጥ ያስቀምጡ እንደነበር የሚያሳይ የፈረሰ እሪቅ ወይም ጎተራ ድብኝት የመሳሰሉት የእህል ማከማቻ ቁሶች ያመላክታሉ) ማሳን ጽድ ዋሻ የመሳሰሉትን የተፈጥሮ ዋሻ የያዘ ሲሆን ወንዞችን በተመለከተ የሰረና ወንዝ ፣ቀለዋ ወንዝ፣ አልቅት ዉሃ ወንዝ፣ ደረቅ ወንዝ ፣ፊላ ወንዝ ፣ምሳን ጥድ ወንዝ ፣ማንኮሎ ወንዝ ፣የጠባቢት ወንዝ የጠባብ አርህ ወንዝ የመሳሰሉትን ወንዞች ይዞ ይገኛል፡፡

ክፍል-2                  በየጋና የሚገኙ እፅዋት ዝርያዎች እስከአሁን ባደረግነዉ የመስክ መረጃ ማሰባሰብ ስራ በየጋና  ጥብቅ ደን ዉስጥ  ከ 89 በላይ  የእጽዋት ዝርያ የተገኙ ሲ...
02/04/2026

ክፍል-2
በየጋና የሚገኙ እፅዋት ዝርያዎች
እስከአሁን ባደረግነዉ የመስክ መረጃ ማሰባሰብ ስራ በየጋና ጥብቅ ደን ዉስጥ ከ 89 በላይ የእጽዋት ዝርያ የተገኙ ሲሆን ከዚህ በላይ የእጽዋት ዝርያዎች ሊኖር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በየጋና ጥብቅ ደን ዉስጥ አንድ ረጅም የእግር መንገድ ሲኖር የደኑ መግቢያ የፈንገለት መንደሮችን ትንሽ ወጣ ብሎ ሚገኝ ሉዋ በር በተባለ ቦታ ሲሆን አስከመዉጫዉ የወዠድ ቀበሌ የሚዋሰንበት የአንገት መዉጊያ አካባቢ ድረስ የ2 ስዓት የሚያስጉዝ የእግር መንገድ አለዉ፡፡ሌሎች አጫጭር የእግር መንገዶች ወደ ጥብቅ ደኑ የሚያስገቡ መንገዶች ቢኖርም መረጃ ለመሰብሰብ ምቹዉ መንገድ ከሉዋበር አስከ አንገት መዉጊያ ያለዉ መንገድ ምቹ ያደርገዋል፡፡
የየጋና ደን ከትላልቅ ዛፎች እንደ ኮሶ ብሳና ጥፌ ወይራ ሎይል ሎል ዝግባ የሃበሻ ጽድ ሽነት የመሳሰሉትን የያዙ ሲሆን በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙት እንደ አሰታ አጣጥ ዉልክፋ አጋም የመሳሰሉትን ያያዘ ሲሆን በ3ኛ ደረጃ የሚገኙት የቁጥቋጦና የሳር ዝርያን እንዲሁም ጠንካራ ግንድ የሌላቸዉ በሌሎች እጽዋቶች ተጠምጥመዉ የሚያድጉ እንደ አዞ አረግ ቀስተንቻ አብታ ሃረግ የቡሄ አረድ እንጎጅት ሃረግ የመሳሰሉትን እጽዋችን የያዘ ሲሆን በደኑ ዉስጥ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪያደርገዋል፡፡
ከእነዚህ እፅዋች መካከል የአካባበዉ ማህበረሰብ ለባህላዊ መድሃኒትነት ከሚጠቀምባቸዉ መካከል ቁልቋል ጠንበለል ጦስኝ ሙዥን ግሜ ቀለዋ አመራሮ ግርፋት ቢሄ አረግ ጨጎጎት ኮሶ ቀጨሞ ከስከሶ ሽነት የመሳሰሉት ለባህላዊ መድሀኒትነት የአካባቢዉ ማህበረሰብ ይጠቀሙበታል፡፡
በየጋና ደን ዉስጥ የሚገኙ የእጽዋት ዝርያዎች ከብዙ በጥቂ ቱ እንደሚከተላዉ ይገለጻል፡፡

1 ጥፌ
2 ኮሶ
3 ወይራ
4 የሃበሻ ጥድ
5 የፈረንጅ ፅድ
6 አመጃ
7 ኮሸሌ
8 አጋም
9 አጣጥ
10 ክትክታ
11 ቀረጥ
12 አስታ
13 አብታ ሃረግ
12 አዞ አረግ
13 ባቡቴ
14 ግሜ
15 አዛምር
16 የጦጣ ቁላ
17 ሰንሰል
18 ጠዶ
19 ከሴ
20 ሽቡቴ
21 ገረንገሬ
22 የፍየል ዳቦ
23 አይደርቄ((ዝንጀሮ ጣት
24 ወንዴ እሬት
25 ሴቴ እሬት
26 እንሰፈፈሪ
26 ቄጠማ
27 የገደል ላይ ሳር
28 ጎቲ
29 የሽኮኮ ሳር
30 ብሳና
31 ቡጆ አመረሮ
32 ነጭ አመራሬ
33 ነጭሎ
34 ከስከሶ
35 እንቧጮ
36 ዝንኪላ
37 ሟጥሽ
38 ኮሽም
39 ሾላ
40 ጠጋ
41 ጅብራ
42 ሽነት
43 አካያ
44 እንዶድ
45 ጥቁር እንጨት
46 ሎል
47 ትለም
48 ቀጨሞ
49 ቀጠጥና
50 ዶግ
51 እንጀሬ
52 ዳሞቴ ወይራ
54 ቀስተንቻ
55 እንጎችት ሃረግ
56 ቡሄ አረግ
57 እንገጠጥ
58 የአህያ ኮሸሌ
59 ዳምዛ
60 ፍየለ ፈጅ
61 እንቡስ
62 ሽኮኮ ጎመን
63 አስኳር
64 አንፋር
65 ቁልቋል
66 እፀ በለስ
67 በለስ
68 ጥንጁት
69 ጌሾ
70 ላንቁሶ
71 ወይል
72 ቀለዋ
73 መውደር ሃረግ
74 ጠበለል
75 ቃጫ
76 ሳማ
77 ጦስኝ
78 አስታምባ
79 ደም አድርቅ ሙዥኝ
80 አደስ
81 ራስክምር
82 ጉዳሬ ሳር
83 ፊላሳር
84 ውልክፋ
85 አሸሾ
86 ጉሎ
87 ግርፋት
88 ጨጎጎት
89 ጫሬ የመሳሰሉት ሲሆኑ ስማቸው በተመለከት በአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠሩበት ስም መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።
አዝጋጅና ፎቶግራፍ በአድማሱ ጌታነህ!!
ክፍል-3 ይቀጥላል...

01/04/2026

ጭላደ ዝንጀሮ በመንዝ ጓሳ!!!

የጋና የተፈጥሮ ደን የየጋና የተፈጥሮ ደን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በአናዝ ፅድ ቀበሌ እና ዳርገኝ ቀበሌዎች መካከል የሚገኝ የተፈጥሮ ደን ሲሆን በእዚህ የተፈጥሮ ደን መኖር ምክንያት የሁለቱ...
01/04/2026

የጋና የተፈጥሮ ደን
የየጋና የተፈጥሮ ደን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በአናዝ ፅድ ቀበሌ እና ዳርገኝ ቀበሌዎች መካከል የሚገኝ የተፈጥሮ ደን ሲሆን በእዚህ የተፈጥሮ ደን መኖር ምክንያት የሁለቱም ቀበሌ አርሶ አደሮች በባህላዊ የንብ እርባታው ዘርፍ በመሳታፍ የማር ምርት ያመርታሉ።
የየጋና የተፈጥሮ ደን ውስጥ የሚኖሩ ዋሻዎች የዱር እንስሳት እንዲሁም በውስጡ የሚገኙ የእፅዋትና በደኑ ላይ አሁን ያሉበትን ጫና በአጭር በአጭሩ በክፍል በክፍል እናቀርባለን።
ፎቶ ግራፍ ፦አድማሱ ጌታነህ።

በኤፍራታ ግድም ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የየገልዳ እየሱስ ቤተክርስቲያ እና አካባቢው።
31/03/2026

በኤፍራታ ግድም ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የየገልዳ እየሱስ ቤተክርስቲያ እና አካባቢው።

የአዋሽ ወንዝወንዞች ከአንድ ሃገር ተነስተው ሌሎች ሐገሮችን አቋርጠው ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዘው መዳረሻቸው ባህር ወይም ውቅያኖስ ሊሆን ይችላል።በቁጥር ትንሽ የሆኑ ወንዞች ደግሞ ከተነሱበት ሐገ...
29/03/2026

የአዋሽ ወንዝ
ወንዞች ከአንድ ሃገር ተነስተው ሌሎች ሐገሮችን አቋርጠው ብዙ ኪሎ ሜትር ተጉዘው መዳረሻቸው ባህር ወይም ውቅያኖስ ሊሆን ይችላል።በቁጥር ትንሽ የሆኑ ወንዞች ደግሞ ከተነሱበት ሐገር ሳይወጡ ሐይቅ ውስጥ ወይም በበረሃ በሚገኝ አሸዋ ውስጥ ሰርገው ይገባሉ።እነዚህ ወንዞች በእንግሊዘኛው (Inland river )ይባላሉ።
በሐገራችን ከእነዚህ ወንዞች መካከል መዳረሻቸውን ባህር ወይም ውቅያኖስ ከማያደርጉ ወንዞች መካከል የአዋሽ ወንዝ አንዱ ነው።ይህ ወንዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ የመስኖ ስራ የሚከናወንበት ወንዝ ጭምር ነው።የአዋሽ ወንዝ ባለው ፏፏቴ እና በፏፏቴው አካባቢ የሚኖሩ አዞዎችበዙሪያው የሚገኙ ውብና ማራኪ መልከዓ-ምድር ቱሪስትን የመሳብ አቅም እንዳላቸውና በየአመቱ የሃገርና የውጭ ሐገር ቱሪስቶች ይጉበኙታል።ከመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ ውስጥ ከሚገኙ አነስተኛ ወንዞች ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የሚፈሱት የአዋሽ ወንዝ መጋቢ ወንዞች ናቸው።

Address

Adis Abeba Mehale Meda
Mehal Meda

Telephone

+251116850211

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menze Guassa Community Conservation Area office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share