ላሥታ ወረዳ ፍርድ ቤት Lasta Woreda First Instance Court

ላሥታ ወረዳ ፍርድ ቤት Lasta Woreda First Instance Court Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ላሥታ ወረዳ ፍርድ ቤት Lasta Woreda First Instance Court, Community Organization, Debre Sina kebelle, Lalibela.

01/08/2023
30/07/2023

#ነጻነቱ የተጠበቀ #የዳኝነት አካል #ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው❗(አዬነ ተስፌ ታረቀ President of North Wollo Zone High Court)
-------------------------------------------------------------------
👉ፍርድ ቤቶች #3ኛዉ #የመንግሥት አካል የሆኑና #የዜጎችን መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች በፍትሐዊነት;በገለልተኝነት;በሚዛናዊነት እየተመሩ ፍትሕን የሚሰጡ;ሁሉም ወገን #በሕግ የበላይነት #ማዕቀፍ ውስጥ እንድመራ የሚሰሩ; #ሕጋዊ ሥርዓትን የሚያጸኑ የፍትሕ-መድረክ የሆኑ ተቋማት ናቸው።
The judicial arm of the government is regarded as the last hope of citizens❗
እንኪያስ የዳኝነት አካሉ መሠረታዊ መንግስታዊ ሥሪት ይህ ከሆነ ዘንዳ --
👉 ፍርድ ቤቶች ለዜጎች ሁሉ መሠረታዊ መብቶች መከበር; #ለማኅበራዊ #መረጋጋት; #ለተሣለጠ #የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ እና #ለዴሞክራሲያዊ #ማኅበረሰብ #ቀረጻና ለዴሞክራሲያዊ #መራሔ -ሥርዓት ዝርጋታ አበክረው የሚሰሩ ሕዝባዊ ተቋማት ናቸዉ።
በተለይም Courts play an invaluable role in securing a better society-a society wherein human rights and democratic values are entrenched in action❗ ታዲያ እኝህ መዳረሻዎች ገቢራዊ መሆን የሚችሉት ፍርድ ቤቶች ከተፈጥሮአዊ ሥሪታቸዉና ካነገቡት ተልዕኮ አኳያ ነጻነታቸው የተጠበቀ ተቋማት ሆነዉ መዝለቅ ሲችሉ ነዉ።
የዳኝነት ነጻነትን የመጠበቅና የማስጠበቅ ጉዳይ #ለሕግ የበላይነት የቆሙ ጠንካራ የፍርድ ቤት ተቋማትን የመገንባት ጉዳይ ነዉ። #የሕግ የበላይነት ጉዳይ ደግሞ The interests of all ወይም የማኅበረሰብ Highly regarded Common good ስለሆነ ሁሌም ሊጠበቅ የተገባው ነዉ❗The rule of law and an independent judiciary are the fundamental preconditions of personal flourishing and stable prosperous society. The rule of law enables to maintain ❗

1: የፍርድ ቤት ነጻነት ለዜጎች ዕኩልነት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሰዎች ሁሉ በዳኝነት አካላት ፊት በዕኩልነት ይታያሉ። የቀረቡ ጉዳዮችን በዕኩልነት ማስተናገድ የሚቻለውም ነጻ የፍርድ ቤት ተቋም ሲኖር ብቻ ነው።
It must be noted that Judicial independence is a prerequisite to the rule of law and a fundamental guarantee of a fair trial.
ፍርድ ቤቶች በሕግ ችሎት ፊት የቀረቡ ዜጎችን ወይም ድርጅቶችን አሊያም የመንግስት አካላትን ሁሉም በሕግ ፊት ሲቀርብ አንዱ ከአንዱ የሚበላለጥ ሳይሆን ሁሉም ዕኩል ሆኖ የሚታይበትን ገሐዳዊ ምስል ገቢራዊ አድርገዉ
የሚያሳዩ የጋራ የፍትሕ መድረኮች ናቸዉ።
ይህም ሲባል ፍርድ ቤት የቀረበን ማንኛውንም ዓይነት ባለጉዳይን ሁሉ:
👉በፍርድ ቤት ፊት የቀረቡ ሁሉም ዕኩል ናቸው❗ ዕኩል ክብር;ዕኩል የመናገር መብት; ዕኩል ማስረጃ የማቅረብ ዕድል: ዕኩል የመሰማት ነጻነት;ዕኩል የመደመጥ እና በገለልተኝነት ዕኩል የመመዘን መብት አላቸው ማለት ነዉ❗ ዜጎችን በዕኩልነት መመልከት ዓይነተኛ የዴሞክራሲያዊ ዕሴትና የሰለጠነ ማኅበረሰብ መገለጫ ነዉ።

2: የፍርድ ቤቶች ነጻነት የዳኞች ከለላ ሳይሆን የዜጎች መሠረታዊ መብት ነዉ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
The judiciary is mandated to sustain equality and lawfulness.የነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት መኖር ሕጋዊነትን የማስፈንና በሕግ ፊት ዕኩል መታየትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነዉ።
ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ሲገነባ ዜጎች በሕግ የበላይነት ያላቸዉ ዕምነት ይጨምራል። ዜጎች ጉዳያቸዉ በሕግና በማስረጃ ብቻ እንደሚወሰን አመኔታ ካሳደሩ የመንግስት አሰራር ሕጋዊ ቅቡልነትን(Legitimation) እንድኖረው ያደርጋል ። ነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ሲኖር The parties at a bone of contention and the wider public can have confidence that cases will be decided fairy and in accordance with the law.

#የዳኝነት ነጻነት ጉዳይ #የዜጎች #መሠረታዊ መብት ነዉ።
ዜጎች በሕግ በተቋቋመ;ሥልጣን ባለዉ ብቃት ባለዉ ፍርድ-ሰጭ አካል ነጻና ገለልተኛ ዳኝነት የማግኘት መብት አላቸው። ይህም ማለት ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡ አካላት ሁሉ ያለልዩነት;እንድሁም የሌሎች ጫና እና ግፊት በሌለበት ዕኩል ተሰምተዉ የቀረበው ጉዳይ በሕግ ዐይን ታይቶ በማስረጃ ተመዝኖ አመኔታ የሚጣልበት ዉሳኔ መሰጠት መቻል አለበት ማለት ነዉ። ከዚህ የምንረዳው ነጻ በሆነ ፍርድ ቤት ዳኝነት የማግኘት ጉዳይ ዜጎች በመብትነት የሚጠይቁት ሌሎች አካላት ደግሞ ጉዳዩ የዜጎች መብት መሆኑን አውቀው የማክበርና የማስከበር ግዴታቸውን የሚወጡበት ሂደት መሆኑን ነዉ።

3: ነጻ የፍርድ ቤት ተቋማትን የመገንባት ፋይዳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የዳኝነት አካላት ዓይነተኛ ሚና ሕግን በገለልተኝነት በመተርጎም በክርክር ተፋላሚዎች መካከል ያለዉን ጉዳይ በሕግ አዉድ መፍታት ነዉ።
ይህን ታላቅ ኃላፊነት የሚወጣዉ ፍርድ ቤት ነጻነቱ የተጠበቀ መሆን ያለበት ሲሆን የዳኝነት ነጻነት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እና ለፍትሐዊ የሕግ አተገባበር ዋስትና ነዉ። ገለልተኛ የዳኝነት አካል የተረጋጋ ማኅበረሰብን ለመገንባት ይረዳል።

በአንድ ሃገር ዉስጥ የፍርድ ቤት ነጻነት ሲጠበቅ እና የሕግ የበላይነት ሲፀና ዉጤቱ በሃገሬው ዉስጥ የሚገኝ ሁሉም የሰዉ ልጅ በተገራ በጎ ዕሴት እንድመራ የሚያደርግ;Strong culture of lawfulness በማስረጽ ሃገርንና ኅብረተሰብን ወደ ሕግ-አክባሪነት የዴሞክራሲያዊ ባሕል ግንባታና የሰላማዊ ጎዳና የሚመራ እንድሁም በሕግ የበላይነት ማዕቀፍ ዉስጥ የተገነባ እንደራሴ የሆነ የመንግስት ሥርዓትን ለማንበር የሚረዳ ዓይነተኛ መንገድ የሚታይበት ማለት መሆኑ ነዉ። ይህም ማለት ፍርድ ቤት ከሦስቱ የመንግስት አካላት አንዱ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተቀመጡትን ዐቢይ ጉዳዮች ይዞ በመፈጸም እረገድ የሃገርንና የዜጎችን ዕጣ-ፈንታ የመወሰን ዕድል ያለዉ 3ኛዉ መንግስታዊ መዋቅር መሆኑ ነዉ።

4: የሕግ የበላይነት እና የፍርድ ቤት ነጻነት ጉዳይ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የሕግ የበላይነት መኖር ሁሉም የሰው ልጆች በሕግ አግባብ እንድመሩ የሚያደርግ;የዘፈቀደ አሰራር እንዳይኖር;በሕግ የበላይነት የተገራ ሥርዓት እንድፈጠር;ተጠያቂነት በሁሉም የሚሰፍንበት አሰራር እንድኖር በአጠቃላይ ሕግ ለሁሉም በዕኩልነት እና በፍትሐዊነት እንድተገበር የሚያደርግ ሁኔታን የሚፈጥር ነዉ። የሕግ የበላይነት ዓይነተኛ ፍቱንነት ይህ ሲሆን የሕግ የበላይነት በሁሉም ዘንድ የሚረጋገጠው የፍርድ ቤት ነጻነት ሲኖር ነዉ። The Rule of Law requires judicial independence so that people can take their disputes to court and have them resolved according to law.

የሕግ የበላይነት እና የፍርድ ቤት ነጻነት ሲጣሱ ሥርዓት አልበኝነት ይንሰራፋል;የዜጎች ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች አደጋ ዉስጥ ይገባሉ። ይህ እንዳይሆን የዳኝነት ነጻነትን መጠበቅና ማስጠበቅ የግድ የሚል ዕሙናዊ ሐቅ ነዉ። የዳኝነት ነጻነትን የመጠበቅና ያለመጠበቅ ሁናቴ ሃገራዊ የዴሞክራሲ ባሕል በደረሰበት ደረጃ ልክ የሚወሰን ሲሆን ያደገ የዴሞክራሲ ባሕል ያላቸው ሃገራት ከፍ ያለ የዳኝነት ነጻነት ደረጃ አላቸው። More democratic countries tend to have a higher level of de facto judicial independence. የሆነ ሆኖ የዳኝነት ነጻነት ማለት የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የቆመ;ሁሉም ሰዉ በሕግ ፊት ዕኩል ሆኖ የሚታይበት ሕጋዊ አሰራር እንድኖር ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት ነዉ።
ይህን ኃላፊነት የሚወጡት በሕዝብ እንደራሴዎች ተሾመው የሚመደቡት ዳኞች ናቸው። ዳኞች ሕግ ተርጓሚዎች ሲሆኑ የሕዝብ እንደራሴዎች ያወጡትን ሕግ ተርጉመዉ ገቢራዊ በማድረግ ለዜጎች የዳኝነት ፍትሕ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የሕግ የበላይነትን ያረጋግጣሉ። ይህን ታላቅ ሕዝባዊና ሃገራዊ ኃላፊነት የሚወጡ ዳኞች በዜጎች የፍትሕ-መድረክ የሕግ ልዕልናን የሚያፀኑ የሕዝብ ምስሎች ናቸው። ይህ ከሆነ ደግሞ በሌሎች ሃገራት የተሰጠዉ ለዳኞች ያለመከሰስ ከለላ(Judicial Immunity) ሊሰጣቸዉ ይገባል። ያለመከሰስ መብት ማለት ዳኛዉ ወንጀል ከሰራ አይጠየቅም;አይከሰስም ማለት አይደለም። ነገር ግን በዘፈቀደ ዐፈና የማድረግ አሰራር ሕጋዊነት የለዉም ማለት ነዉ። ፍትሕን ለዜጎች በገለልተኛነት የሚሰጥ ዳኛ ነገ ላይ በሚሰጠው ዳኝነት በሕግና በማስረጃ መዝኖ ዉሳኔ የመስጠት ሙያዊ ግዴታዉን እንዳይወጣ ለሥጋት መዳረግ የለበትም።
ዳኞች ያለምንም ተፅዕኖ ፍትሕን መስጠት መቻል አለባቸው። Judges must be able to dispense justice without constraints. ያለመከሰስ መብት ጥቅሙ ለኅብረተሰቡ ሲሆን የኅብረተሰብ ጋሻ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ። ያለመከሰስ መብት ከፍርድ ቤት ነጻነት እና የሕግ የበላይነትን አስከብሮ ከመሥራት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነዉ። ያለመከሰስ መብት ማለት ከ3ኛ ወገኖች ጣልቃገብነት;የዐፈና ተግባር እንድሁም ተፅዕኖ እና ከእነዚሁ 3ኛ ወገኖች ዕክል-ፈጣሪነት የመጠበቅ ጉዳይ ማለት ነዉ። Judicial immunity helps to protect the reputation and the perception of the judiciary and enables to maintain the trust of the society. በዋነኛነት ይህ ጉዳይ #የመንግስት አካል የሆነዉን #ተቋም ስም #ለመጠበቅ እና #የኅብረተሰቡን #አመኔታ #ለማጽናት የሚጠቅም ትልቅ ፋይዳ ያለው ጉዳይ እንጂ የግለሰቡ ዳኛ አላግባብ የሆነ መብት ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም።
ስለሆነም የዳኞች ጥበቃ ለነጻና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ወሳኝ ሲሆን ነጻነቱ የተጠበቀ ፍርድ ቤት ደግሞ ለዜጎች ዕኩልነት እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የማዕዘን ድንጋይ ነዉ።

5: ለመሆኑ ፍርድ ቤት ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጋር እንዴት ይገናኛል?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
The judiciary is the guiding pillar of democracy.
ከዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ አንዱ የሁሉም ሰው ሐሳብ የሚከበርበት ሁኔታ መኖሩ ሲሆን ከዳኝነት አካላት አንዱ ገጽታ ደግሞ ሁሉም ሰው ጾታ፣ ሃይማኖት እና የቆዳው ቀለም ሳይለየዉ በሕግ ፊት በዕኩልነት የሚስተናገድበት መድረክ መሆኑ ነዉ።
ሌላዉ የዴሞክራሲ አስተዳደር አመላካች ከሆኑት ሁነቶች መካከል መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች መከበር እና የሕግ የበላይነት ሥርዓት ማንበር ነዉ። የፍርድ ቤት ዋነኛ ተልዕኮም እነዚህን ወሳኝ ጉዳዮች ማዕከላዊ ያደረገ ነዉ። የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶችን ማክበርና በሕግ የበላይነት መመራትን ይጠይቃል። ፍርድ ቤት ደግሞ ሕግ ተርጓሚ አካል ነዉ። ዋነኛው ሥራው ሰብዓዊ መብቶችን ማስከበር እና ሕግን በመተርጎም የዜጎችን ዕኩልነት እና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነዉ። The judiciary is placed to establish rule of law-based system. በተጨማሪም ፍርድ ቤት ከተፈጥሮአዊ ተልዕኮው አኳያ የሌሎች የመንግስት አካላት ድርጊት ከሕግ ዉጪ የተሰራ እንዳይሆን ይቆጣጠራል;ተግባራትን review የማድረግ ሥራ ይሰራል;በሕግ በተሰጠ ሥልጣን መሠረት ኃላፊነታቸዉን የተወጡ ስለመሆናቸው ያረጋግጣል። The judiciary acts as a watchdog by ensuring that all the organs of the state are functioning within their limits.
ፍርድ ቤቶች ተጠያቂነትን የማስፈን ሥራ ይሰራሉ። የዜጎችን ነጻነቶች(Civil Liberties) ያስጠብቃሉ;መሠረታዊ መብቶችን በማስከበርና በማስፈጸም በሕግ የበላይነት ማዕቀፍ ዉስጥ የሆነ #ነጻና #ፍትሐዊ #ማኅበረሰብ እንድኖር ያደርጋሉ። As such, an independent and impartial judiciary is one of the cornerstone of a democracy that ensures a free and fair society under the rule of law..በአጠቃላይ የዳኝነት ሚና እና የዴሞክራሲያዊ ግንባታ ሂደት ተመጋጋቢ መሆናቸውን ልብ ይሏል።
በመሆኑም ዓይነተኛ ሚናቸው ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጋር የተቆራኘው ፍርድ ቤቶች ነጻ እና ጠንካራ ተቋም ሆነዉ ሊገነቡ እና ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ሊሆኑ ይገባቸዋል።

የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት የ 2015 ዓ/ም ስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ ።================================ #በበጀት ዓመቱ 5778 መዝገቦች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዋል ። #ከቀረቡ...
19/07/2023

የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት የ 2015 ዓ/ም ስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ ።
================================
#በበጀት ዓመቱ 5778 መዝገቦች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዋል ።
#ከቀረቡት ዉስጥ 5740 መዝገቦች ተሰርተዋል ።
#ከዚህ ዉስጥ 4950 መዝገቦች የፍትሐብሔር ሲሆኑ ቀሪ 790 መዝገቦች ደግሞ የወንጀል መዝገቦች ናቸዉ።
#አጠቃላይ ከቀረቡት መዝገቦች ዉስጥ በፍትሐብሔር 34 መዝገቦች በወንጀል 4 መዝገቦች በድምሩ 38 መዝገቦች ወደሚቀጥለዉ በጀት ዓመት ተላልፈዋል ።
#በ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጣጠር በ 2891 መዝገብ ጭማሪ አሳይቷል ።
#99.14 % መዝገቦች ከ 6 ወር በታች የተሰሩ ናቸዉ ።
#0.86 %ብቻ ከ 6ወር በላይ የጨረሰ ሲሆን ፥ከ 1 ዓመት በላይ የወሰደ መዝገብ የለም ።
#በበጀት ዓመቱ የተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት ተሰጥቶ 148 መዝገቦች ተወስነዋል ፥5 መዝገቦች ወደ ወረዳዉ ተመልሰዋል ።
#ለተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት ፍርድ ቤቱ 10,500 ብር ያወጣ ሲሆን ባለጉዳዮች ግን ወደ ፍ/ቤቱ ቢመጡ ያወጡ የነበረዉን 339,200 ብር ማዳን ተችሏል ።
#በገና በዓል የልዩ ችሎት በማቋቋም 12 መዝገቦች ታይተዉ ለ 10 መዝገቦች ዉሳኔ ተሰጥቷል ።
#በነጻ ታይተዉ ዉሳኔ ካገኙ በኋላ የተከፈለ የዳኝነት ገንዘብ 129,810.60 ብር ሲሆን ይህም ከፍተኛ ዉጤት የተገኘበት ነዉ ።
#ባለጉዳዮች ለአጫጭር አቤቱታዎች በፎርም እንዲጠቀሙ የተደረገ ሲሆን ይህ በመሆኑም ያወጡት የነበረዉን 197,950 ብር ማዳን ተችሏል ።
#ግንባታን በተመለከተ በዚህ በጀት ሁለቱም "ብሎኮች " G+0 እና G+1 አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እየሰጡ ሲሆን G+2 ደጋፊ ብረት ፣የ 3 በር እና የ8 መስኮት ስራ ተሰርቷል ።የጥበቃ ቤት ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ ተሰርቷል ።በዚህ በጀት ዓመት 309,000 ብር ወጪ ተደርጎ ተሰርቷል ።
#የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ከደሞዛቸዉ በመቀነስ በ HIV ወላጆቹን ያጣ ህጻን በወር 505 ብር ድጋፍ ያደርጋሉ ።
#በበጀት ዓመቱ 2 ጊዜ የዳሰሳ ጥናት ተካሂዶ አማካኝ የማርካት መጠናችን 89.8 % ሆኖ ተመዝግቧል ።
#በመጨረሻም በየሂደታቸዉ ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል ።

14/07/2023

ሁለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ሰራተኞች በስልጣን የመነገድ ወንጀል ተከሰሱ
***********************************

ተከሳሾቹ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የላይብረሪ ሰራተኛ እና የመልዕክት ሰራተኛ ናቸው።

ተከሳሾቹ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ 1ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር ደቡብ ምዕራብ ክልል ቦንጋ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከእንጀራ እናቷ ጋር በነበራት የንብረት ይገባኛል ክርክር የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ አቤቱታዋን ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርባ ፋይል ካስከፈተች በኋላ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት እግድ ትዕዛዝ ያልተሰጠበት በመሆኑ ንብረቱን ለማሳገድ በቀን 09/10/2015 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ታቀርባለች።

1ኛ ተከሳሽ "እኔ መዝገብ ክፍል ነው የምስራው ጉዳይሽ የሚያልቀው በብር ነው፤ ብር ካልከፈለሽ መዝገቡ ይዘጋል ነገር ግን ያቀረብሽውም ይግባኝ ከ3 ዳኛ ወደ 5ኛ ዳኛ እንዲተላለፍ ከፈለግሽ እንዲሁም ይዞታው እንዲታገድልሽ ከፈለግሽ 2 መቶ ሺ ብር ክፈይ ከዳኞቹ ጋር ስለምሠራ ጉዳይሽን አስፈፅምልሻለሁኝ" በማለት ገንዘብ መጠየቁን ነው የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ክስ የሚያስረዳው።

2ኛ ተከሳሽ ተበዳይ እግዱን በተመለከተ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለቀን 12/10/2015 ዓ.ም ተቀጥራ ስለነበር ውሳኔውን ለመውሰድ በቀረበችበት ወቅት ‹‹ጉዳዩ እንዲያልቅልሽ 200,000 ሺህ ብሩን ቶሎ እስከ ምሽት 11፡00 ሰዓት ድረስ ይዘሽ ነይ በማለት የገለፀችላት ቢሆንም 1ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር የሆነችው ተበዳይ በወቅቱ እግዱ መታገዱን ካረጋገጠች በኋላ ብሩን ሳትከፍል ቀረች።

1ኛ ተከሳሽ የተበዳይ ጓደኛ ወደ ሆነችው 3ኛ ምስክር ስልክ ላይ በመደውል ‹‹እህትሽ ዳኞች ጋር ገብቼ ካሳገድኩላት በኋላ ክፍያውን ሳትከፍል ስልኳን አጥፍታለች ብሩን ካልከፈለች አሁን ይዞታው ቢታገድም መዝገቡም ያስቀርቧል ቢባልም 5 ዳኞች ጋር ጉዳዩ ሲቀርብ አበላሽቼ ጉድ እሰራታለሁ ›› በማለት አስፈራርታ ከ3ኛ ምስክር በቀን 22/10/2015 ዓ.ም 4 ኪሎ አካባቢ የሚገኝ ካፌ ውስጥ “10,000 ሺ ብር” ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘች።

ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በስልጣን የመነገድ ወንጀል የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸዋል።

በጥላሁን ካሳ

05/07/2023

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት #የሁሉንም ወረዳ ፍርድ ቤቶች #የሥራ #ክንዉን ተዘዋዉሮ ገመገመ❗
➖➖➖➖➖➖➖➖
የውይይትና የግምገማ ስርዓቶችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ዘርግቶ መሥራት የዳኝነት ተቋሙን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። #ተቋማት የሚያደርጉትን #የሥራ #ክንዉን እንድሁም በተጨባጭ የዘረጉትን #አሰራር እና #የተወጡትን #ኃላፊነት ብሎም #ያስገኙትን #ዉጤት በአግባቡ ለመለየት ከሪፖርት ቅብብሎሽ ባሻገር #መሬት ላይ #በተጨባጭ ያለዉን ዕውነታ #በአካል ተገኝቶ ምልከታ ማድረግ; #መገምገምና #የማስተካከያ #አቅጣጫዎችን መስጠት ሁሌም #የማይተካ ሚና አለዉ። የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ በ 2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ገምጋሚ ኮሚቴ በማዋቀር ከንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤቶች ዉጭ #በሁሉም ዋና ወረዳዎች በመዘዋወር እኝህ የወረዳ ፍርድ ቤቶች #በተቋማዊ መሪ #ዕቅዱ መሠረት እና በየጊዜው በሚሰጡ #የአሰራር #አቅጣጫዎች መሠረት የሰሯቸዉንና ያልሰሯቸውን ሥራዎችን መለየት በሚያስችል መልኩ የመገምገሚያ ቸክሊስት በማዘጋጀት ሥምሪት የወሰደዉ ኮሚቴ ድጋፍና ግምገማዉን አድርጎ ተመልሷል።

የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በቀን 24/09/2015 ዓ/ም በመ/ቁ 0202413 በዋለዉ ችሎት  የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ  አንቀጽ  630(2)ን በመተላለፍ የግል ተበዳይ ላይ የግብረ ሰዶምና ለንጽህና...
08/06/2023

የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በቀን 24/09/2015 ዓ/ም በመ/ቁ 0202413 በዋለዉ ችሎት የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 630(2)ን በመተላለፍ የግል ተበዳይ ላይ የግብረ ሰዶምና ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆነ ድርጊት የፈጸመ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሎ የ 9 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶበታል ።

03/06/2023
የላስታ አዉራጃ ፍ/ቤት በአዲስ መልክ ግንቦት 25/1985 ዓ/ም ዳኛ አሻግሬ ተበጀ ተሰይመዉ ስራዉን ጀመረ ።እነሆ 30 ዓመቱን ደፈነ ።Stare @ Stamp
02/06/2023

የላስታ አዉራጃ ፍ/ቤት በአዲስ መልክ ግንቦት 25/1985 ዓ/ም ዳኛ አሻግሬ ተበጀ ተሰይመዉ ስራዉን ጀመረ ።
እነሆ 30 ዓመቱን ደፈነ ።
Stare @ Stamp

Address

Debre Sina Kebelle
Lalibela

Telephone

+251333360003

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ላሥታ ወረዳ ፍርድ ቤት Lasta Woreda First Instance Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share