Hara online

Hara online Well Came

06/03/2026

ዛሬ እለተ ጁምአ በሁሉም ማህበራዊ ሚድያ እየተዘዋወረ እና አነጋጋሪ የሆነ አሳዛኝ ቤተሰብ:- የቻልንውን እናደርጋለን እንጂ በዚህ ጊዜ ሁሉም ሰው በተቸገረበት ወደ ማህበራዊ ሚድያ ቀርበን ዘመድ እና የኢትዩዽያን ህዝብ እርዱን ብለን አናስቸግርም ሲሉ የተደመጡ በጣም አሳዛኝ ቤተሰቦች ዛሬ የሁሉንም ቀልብ የሳበ እና መነጋገሪያ ሆነዋል።


የገጠር ሰው ካለው መስጠት እንጂ መለመን አይችልበትም የሚባለውን እውነት መሆኑን ያነፀባርቃል። እናተ የበኩላችሁን ድጋፍ አድርጉ ፣ እኛም የበኩላችንን ድጋፍ በማድረግ እና መረጃውን ለእናተ አጋርተናችኋል። #ሼርይደረግ

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላለልና ምግብ ዋስትና በሃራ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አቅመ–ደካሞችና መሳኪኖች ከ243,000 ብር በላይ የሚገመት ብረት ድስትና ደብተር ድጋፍ አደረጉ።‎‎የሰሜን ወ...
02/08/2025

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላለልና ምግብ ዋስትና በሃራ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ አቅመ–ደካሞችና መሳኪኖች ከ243,000 ብር በላይ የሚገመት ብረት ድስትና ደብተር ድጋፍ አደረጉ።

‎የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላለልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር Alemu Yimer ይህ ድጋፍ የመጀመሪያችን ሲሆን ወደፊት ኃብት በማፈላለግ በቻልነው ሁሉ በመደገፍ ከጎናችሁ እንሆናለን ብለዋል።140 ብረት ድስት፣ጭልፋ እና 30 ደርዘን ደብተር ከ243,000 ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

‎የሰሜን ወሎ ዞን ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ አሸናፊ ሰማው Ashenafi Semaw ከሃራ ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ንግግር በማድረግ ይህ ድጋፍ ወደ ሃራ እንድመጣ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

‎ሀላፊው መንግስታችን ድሃ ተኮር ስለሆነ የተቸገሩ ሰዎችን መርዳት ትልቁ አላማው ነው ብሏል።በጎነት ማለት ከተረፈን መስጠት ሳይሆን ካለን ማካፈል ሲሆን ይህ ደግሞ በፈጣሪም በሰውኛ ባህሪም እርካታ የሚሰጥ ተግባር ነው ብለዋል።

‎የሃራ ከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ጀሚላ ፋሪስ Jemila Farise ባህላችን የሆነውን መረዳዳትና መተባበር ማስቀጠል ይኖርብናል፤የኔ ሆድ ሞልቶ ጎረቤቴ ፆም ማደር የለበትም የሚል መንፈስ ሊያድርብን ይገባል።እኛ ስንተዛዘን አላህም ያዝንልናል፤በእርግጥ ለዚህ በጎ ተግባር ወሎየዎች አይታሙም ብለዋል።

‎የከተማው ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሞላ Ahmed Molla ስፖርቱን ብቻ ሳይሆን የምናነቃቃው የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራትንም ዋነኛ ሚናችን አድርገን እንሰራለን ብለዋል።

‎ « የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤አለን ከጎናችሁ እንበል »

✍️ ሀምሌ 15 - 11 - 2017 | በሀራ ከተማ አስተዳደር ለህዘብ ውሀ አገልግሎት ሲሰጠጥ የነበረ ባለ 200 kv ትራንስፈርመር በሌቦች ተዘረፈ !!!ትኩረት ይደረግ!!!የሐራ ከተማ አስተዳ...
22/07/2025

✍️ ሀምሌ 15 - 11 - 2017 | በሀራ ከተማ አስተዳደር ለህዘብ ውሀ አገልግሎት ሲሰጠጥ የነበረ ባለ 200 kv ትራንስፈርመር በሌቦች ተዘረፈ !!!

ትኩረት ይደረግ!!!
የሐራ ከተማ አስተዳደር ውሃ ልማት ፅ/ቤት ሐላፊ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም በጉዳዩ ላይእንድህ ብለዋል። ትኩረት ይደረግ!!! ''በዛሬው እለት በሃራ ከተማ አስ/ር ለውሃ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ባለ 200 kv ትራንስፈርመር እጅግ በተጠና መንገድ ሲዘረፉ አድሩዋል።

ቀጥሎም ይህ ተግባር ከጥቅም ጋር ብቻ የተያያዘ ጉዳይ አይደለም። አክለውም:- ህዝብ ሆይ እየሆነ ያለው የከተማውን ሰላም ማደፉረስ የከተማውን ህብረተሰብ በውሃ ችግር መቅጣት ከፓለቲካው ጋር ተያይዞ ህዝብና መንግስትን መነጠልን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለ አካል አለ ስለዚህ ሁሉም የህብረተሰብ ክፉል ይህን አውቆ በየ አካባቢው ያለን የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ሊጠብቅ ይገባል'' ብለዋል

በተጨማሪ:- ይህ ተግባር የህዝብን መሠረተ ልማት ማውደም እና መዝረፍ በእጅግ ዘግናኝና አስነዋሪ ድርጊት እና የከተማውን መንግስትና ህዝብ ሆን ተብሎ ለመነጣጠል የሚደረገው እንቅስቃሴ ማህበረሰቡ መታገስ የለበትም በመሆኑም ሁሉም ሰው ከመንግስት ጎን በመቆምና የአካባቢውን መሠረተ ልማቶች በጋራ መጠበቅ አለበት ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች በተላዩ ድረ ገፆቻቸው የበኩላቸውን ሀሳብ እና መልክት አስተላልፈዋል።

Hara online

20/07/2025

ሐራ ከተማ - ሀምሌ 13/11/2017

 :-ስለ ሐራ ከተማ ብንል ማጋነን አይሆንብንምሀራ ከተማ ማለት:-በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ወስጥ ይህ ውጅንብር ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም ቦሀላ የማንንም ዛዛታ ኩሽኩሽታ ...
18/12/2024

:-ስለ ሐራ ከተማ ብንል ማጋነን አይሆንብንም

ሀራ ከተማ ማለት:-በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ወስጥ ይህ ውጅንብር ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም ቦሀላ የማንንም ዛዛታ ኩሽኩሽታ ያልሰማ ፣ ለሀገሩ ሰላም ሲል በላሙ የፀና እድገትን የሚፈልግ ህዘብ አለ ቢባል ሰሜን ወሎ የሀራ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የከተማ ህዝቦች ቀዳሚ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንብኝም... የሀራ ከተማ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ትልቅ ክብር ይገባችኋል። ሰላም ለሀገራችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

® Hara Online
ይህ አድስ ፔጅ ሲሆን ላይክ ፎሎ ሼር ይደረግ

Address

Northist Wello Hara
Lalibela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hara online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share