ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም ዘኢተያ Tsedenia Mariam, Eteya

  • Home
  • Ethiopia
  • Itaya
  • ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም ዘኢተያ Tsedenia Mariam, Eteya

ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም ዘኢተያ Tsedenia Mariam, Eteya Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም ዘኢተያ Tsedenia Mariam, Eteya, Eteya, Itaya.

24/09/2024
የደመራ በዓል በኢተያ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን
27/09/2023

የደመራ በዓል በኢተያ ደብረ ገነት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን

04/09/2023

*****ጸሪቀ መበለት "*****

“ብዙ ሲኖረኝ እሰጣለሁ”

" ጌታ ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበር፤ ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር፤ አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች። ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤ ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው። " ( ማር 12፥41-44 )

ትንሽ ቢሆንም ለተቸገረው አንድ ነገር ስጡ ምንም ለሌለው ሰው ትንሽ አይደለምና የምንችለውን ከሰጠን ለእግዚአብሔርም ትንሽ አይደለም።
የባለጸጋ ጾሙ የድሃም ምፅዋቱ ታላቅ ዋጋ አለው ባለጸጋው ከለመደው ከብዙ ማዕዱ የላም የጣመውን ትቶ ይጾማልና ድሃውም ያልተረፈው ሆኖ ሳለ ከመኖሪያው ከፍሎ ይስጣልና፤ ከትርፋቸው ከሰጡት ይልቅ ካላት ጥቂት ከፍላ የሰጠችውን "ትዳሯን (መተዳደሪያዋን) ሰጠች " ብሎ ጌታችን አመስግኗታል። ጌታችን ኢየሱስ ከእነርሱ ከማንኛቸውም በላይ አስገባች አላለም። ከሁሉም በላይ እንዳስገባች ተናግሯል ሁሉም በአንድ ላይ ካስገቡት ይበልጣል አለ።

ይህች ሴቲቱ መበለት ስለነበረች እና የሚደግፋት ባል ስላልነበራት ድሀ ነበረች ነገር ግን እኔ “ብዙ ሲኖረኝ እሰጣለሁ” የሚለውን አስተሳሰብ ተገዳደረች ድህነቷንም አሸነፈች።

21/09/2022

መስከረም 10/2015 ኢተያ ቅዱስ በዓለ ወልድ፤ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም

❖ ጼዴንያ ❖❖ ጼዴንያ ❖❖ ጼዴንያ ❖ጼዴንያ ማለት፣ የታቦት ወይም የሰው ስም አይደለም፣ የሀገር ስም ናት እንጂ፡፡ ታሪኳም በሀገረ ደማስቆ፣ በጼዴንያ ክፍል፣ መሪና በምትባል ቦታ፣ ማርታ የ...
20/09/2022

❖ ጼዴንያ ❖❖ ጼዴንያ ❖❖ ጼዴንያ ❖

ጼዴንያ ማለት፣ የታቦት ወይም የሰው ስም አይደለም፣ የሀገር ስም ናት እንጂ፡፡ ታሪኳም በሀገረ ደማስቆ፣ በጼዴንያ ክፍል፣ መሪና በምትባል ቦታ፣ ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ እሷም ለእንግዳ ማደሪያ፣ የተለየ ቤት ለብቻ ሠርታ፣ እንግዶችን ስትቀበል ትኖር ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ የኢትዮጵያ መነኰሳት ሲበቁ፣ የጌታን መቃብር ሳያዩ አይቀሩም ነበርና በዚህ ልማድ አንድ አባ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ የጌታን መቃብር ለማየት ሲሄድ፣ ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረ፡፡
ማርታም ሲነጋ ወደ እንግዶች ቤት ገብታ ከእናንተ ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድ ሰው አለን፣ ብላ ብትጠይቅ፣ ቴዎድሮስ እኔ እሄዳለሁ አለ፡፡
እሷም አባቴ እንግዲያስ ሉቃስ የሳላትን የእመቤታችን ሥዕል አምጣልኝ አለችው፡፡ እሺ አላት፡፡ ገንዘብ ልስጥህ ብትለው፤ በእኔ ገንዘብ አምጥቼልሽ በኋላ ስመለስ ትሰጭኛለሽ ብሏት ሄደ፡፡ የጌታን መቃብር ተሳልሞ፣ ሥዕሊቱን ረስቶ ሲመለስ፣ አደራ ጥብቅ፣ ሰማይ ሩቅ፣ እንዲሉ፣ ያች ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ? የሚል ድምጽ ሰማ፡፡
ተመልሶ ሄዶ ሥዕሊቱን ገዝቶ ሲመለስ፣ አንበሳ ሊሰብረው መጣ፣ ሥዕሊቱም አፍ አውጥታ ብትናገር፣ አንበሳው ደንግጦ ተመልሶ ሄደ፡፡
ይህን እያደነቀ ሲሄድ ሽፍቶች ሊቀሙት ሲሉ፣ አስደንግጣቸው ተመልሰዋል፡፡ ቴዎድሮስም እንዲህ ያለ ተአምር ስትሠራ ቢያይ፣እንዲህ ያለችውን መድኃኒት ለራስ ያደርጓታል እንጂ፣ ለሰው ይሰጧታልን፣ ብሎ፣ ወደ ጼዴንያ የሚወስደውን ትቶ፣ በሌላ መርከብ ተሳፍሮ ሲሄድ፣ ሥዕሊቱ ነፋስ አምጥታ፣ ወደ ማርታ ቤት ወሰደችው፡፡ እሱም መቼም አታውቀኝ፣ ከቤቷ የሚገባው የሚወጣው ብዙ ነው ብሎ ሄዶ፣ ከቤቷ አድሮ፣ ሲነጋ ወጥቼ እሄዳለሁ ሲል፣ ዐይኑን አወረችው፡፡ ወደ ማጀት ሲሄድ ያያል፣ ወደ ደጅ ልውጣ ሲል ይታወራል፡፡ ማርታም እንዲህ እያለ ሲድበሰበስ አይታ፣ አባቴ አሞሃል እደርና ነገ ትሄዳለ አለችው፡፡ አደረ፡፡ በሁለተኛውም እንዲሁ ሆነ፤ አደረ፡፡ በሦስተኛውም እንዲሁ ሆነ፡፡ ማርታም ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው፣ ምን ሆነሃል አለችው፡፡
ቴዎድሮስም ሥዕል አምጣልኝ ያልሽኝ እኔ ነበርሁ፣ ገዝቼ ስመጣ ከመንገድ ከብዙ አደጋ ስላዳነችኝ፣ መድኃኒቴን አሳልፌ አልሰጥም ብዬ፣ ከአንቺ ከድቼ በሌላ መንገድ ስሄድ፣ በተአምር ሳላውቀው ከዚህ አመጣችኝ ፣ እሷም ይቻትልሽ ብሎ አውጥቶ ሰጣት፡፡ ማርታም ደስ አላትና፣ እየሰገደች ጉልበቱን ስማ ተቀበለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቤት ሠርታ፣ በአራት ማዕዘን መብራት ተክላ አስቀመጠቻት፡፡
ሥዕሊቱም ሥጋን የለበሰች ትመስል ነበር፡፡ ከፊቷም ወዝ ሲወጣ ይታይ ነበር፡፡ ያነን ሲቀቡ፣ ሕሙማን ይፈወሱ ነበር፡፡ ወይእቲ ሥዕል ትመስል ልብስተ ሥጋ፣ ወያንጸፈጽፍ ሐፍ እምኔሃ ፣ /እን መቅ ተአ/፡፡ ቴዎድሮስም የሥዕሊቱ አጣኝ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ከበረከቷ ያሳትፈን
'' ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ ሉቃስ ጠቢብ እም ወንጌላውያን አሐዱ ፤ ብወንጌላውያን አንዱ ዐዋቂ ሉቃስ በእጁ ለሣለት ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል "

ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከቅድስት ማርታ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።  ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ እንሳተፍ....
13/09/2022

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ እንሳተፍ....

18/08/2022

ደብረ ታቦር


👉 ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ ለኢተያ እና በአከባቢው ለምትኖሩ ህዝበ ክርስቲያን!!

የፊታችን ነሐሴ 13 በኢተያ ደብረ ታቦር ቅዱስ እግዚአብሔር አብ እና ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ እና በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበር እናትም ከሐሙስ ዋዜማው ጀምሮ የበዓሉ ተከፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

👉ከዋዜማው በኋላም

-የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐግብር
አዳር
👉በ ነሐሴ13 ያሉ መራግብራት

-ማህሌት ከለሊቱ 8:00 እስክ 4:00

- ታቦቱ ከመንበሩ ተንስቶ ህዝቡን የሚባርክበት ከረፋዱ 5:00

- የአባቶች የያሬዳዊ ዝማሬ

-የሰንበት ት/ቤት የያሬዳዊ ዝማሬ

- የስብከተ ወንጌል

- ማታ 10.00 ሰዐት የደብሩ የአብነት ነው ተማሪዎች ፕሮግራም

እናንተም የሰማችሁትን ላልሰማ አሰምታችሁ ሁላችንም በንግሱ በዓል ላይ ተገኝተን በርከት እና ረድኤት እንድናገኝ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

# ጠሪ የደብሩ አብነት ተማሪዎች

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሔጦሳ ወረዳ በሚገኘው የኡርጉባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ2ኛ ዙር የአብያተ ክርስቲያናት ጥየቃ መርሐግብር በዕለተ እሑድ ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም ተከናወነ።በዚህ...
01/08/2022

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሔጦሳ ወረዳ በሚገኘው የኡርጉባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ2ኛ ዙር የአብያተ ክርስቲያናት ጥየቃ መርሐግብር በዕለተ እሑድ ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም ተከናወነ።

በዚህም ለተጓዥ ምዕናንና ለአካባቢው ህብረተሰብ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚያስፈልጉ የተለያዩ የመጻሕፍትና የንዋያተ ቅድሳት ድጋፍ ተደርጓል።

/ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም/

"ኑ ቤተክርስቲያንን እንጠይቅ" የሐዋርያዊ ጉዞ መርሐግብር ወደ ጠዶ ደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንግንቦት7/2014ዓ.ም (ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም)
16/05/2022

"ኑ ቤተክርስቲያንን እንጠይቅ" የሐዋርያዊ ጉዞ መርሐግብር ወደ ጠዶ ደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን

ግንቦት7/2014ዓ.ም (ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም)

15/05/2022

🙏🙏🙏 የጠዶ አቦ ጉባኤ🙏🙏🙏

"ኑ ቤተ ክርስቲያንን እንጠይቅ" በሚል መርህ በማኅበረ ጼዴንያ ማርያም የተዘጋጀው ሐዋርያዊ ጉዞ መነሻውን ኢተያ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን በማድረግ በአሁኑ ሰዓት በጠዶ ደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ከተለያየ ቦታ በመጡ ተጓዥ ምዕመናን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ዘማርያን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ጋር በመሆን እንዲሁም የአካባቢው ምዕመናንን ጨምሮ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተከናወነ ይገኛል።

Address

Eteya
Itaya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ጼዴንያ ማርያም ዘኢተያ Tsedenia Mariam, Eteya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share