MeshaStack

MeshaStack From the dev .

Kadosh is a Christian ministry which delivers a Word of life By The field of technology encompasses a vast array of disciplines and innovations that have fundamentally transformed the way we live, communicate, and interact with one another.

13/10/2025

ስለ ነገ ማውቅ ለነገ ዋስትና አይሆናችሁም። ለነገ ዋስትና የሚሆናችሁ ዛሬ እግዚአብሔርን መያዛችሁ ነው። ዛሬ ያወቃችሁት ነገ መልካም የሚሆነው ዛሬ በያዛችሁት እግዚአብሔር ነውና።

“ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።”
— መዝሙር 73፥28

ይህ የሞባይል መተግበሪያ (“Sabbath School - ሰንበት ትምህርት - Barumsa Sanbataa”) ይባላል። በየሶስት ወራቱ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደ...
08/07/2024

ይህ የሞባይል መተግበሪያ (“Sabbath School - ሰንበት ትምህርት - Barumsa Sanbataa”) ይባላል። በየሶስት ወራቱ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለእናንተ ለተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ለማድረስ ተስፋ እናደርጋለን።

አንዴ ከጫኑ እንዲሁም በየሩብ ዓመቱ አዲስ ትምህርት ሲዘጋጅ አንድ ጊዜ ኢንተርኔት ላይ ሆነው አፕዴት ካደረጉ ከዚያ በኋላ ኢንተርኔት ላይ መሆን ሳያስፈልግዎ ትምህርቶቹን ማግኘት እና መጠቀም ትችላላችሁ። በአማርኛ የሰንበት ትምህርት መጽሐፍ ላይ ከሚያገኙት በተጨማሪ በዚህ መተግበሪያ ላይ የኦሮሚኛ እና የእንግሊዝኛ ሰንበት ትምህርቶች እንዲሁም በሆፕ የሰንበት ት/ት አዘጋጆች ተዘጋጅቶ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት ወደ አማርኛ የተተረጎመ የሰንበት ትምህርት ጥናት መምሪያ (Sabbath School outline by Hope SS) ይገኛሉ።

በዚህ ስራ ላይ የረዱንን ቤተ ክርስቲያናችንን ጨምሮ የትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎትን ሻሎም ቴሌ ኮንፈረንስን እና ሌሎችንም ሁሉ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

ይህ መተግበሪያ በቅርቡ ፕሌይ ስቶር (Play store) ላይ እንደሚገኝ ተስፋ እናደርጋለን።

ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ!

********

Appilikeeshiiniin mobaayilaa kun ("Sabbath School - ሰንበት ትምህርት - Barumsa Sanbataa") jedhama. Qo’annoo Kitaaba Qulqulluu Waldaa Adveentistii Guyyaa Torbaffaatiin sadarkaa idil-addunyaatti ji’a sadi sadiin (Kurmaanaan) qophaa’uudhaan isin jaallatamoo maatii keenyaa kan taatanii fi maatii keessan biraan akka geennu abdii qabna.

Erga al tokko fe’attanii (‘install’ gootanii) fi Kurmaana kurmaanaan yemmuu barnoonni haaroofni qophaa’uu Karaarra (online) irratti argamuudhaan haaromsiifattanniin (‘update’ gootaniin) booda, gonkumaa online ta'uun osoo isin hin barbaachisin barumsa sana argachuu fi itti fayyadamuu dandeessu. Appilikeeshiini kana irratti Barnoota Sanbataa Afaan Amaaraatiin dabalataan, kitaaba barnootaa Sanbataa Afaan Oromoo fi Ingliffaa, akkasumas qajeelchituu barnoota sanbataa (Sabbath School outline by Hope SS) qopheessitoota barumsa Sanbataa Hoopiitiin qophaayee Tajaajijila ‘Wongeelaa Yetinbiit Qaal’ tiin gara Afaan Amaaraatti hiikame ni argattu.

Worroota hojii kana irratti nu gargaaran Waldaa keenya dabalatee, Tajaajijila ‘Wongeelaa Yetinbiit Qaal’, Teelee koonfiraansii Shaaloom fi kanneen biroos heddu galateeffanna.

Appilikeeshiniin kun yeroo dhiyootti play store irratti akka dhiyaatu abdii qabna.

Gooftaan baay'isee Isin Haa Eebbisu!

ቴሌግራም ላይ ተለቋል ።
https://t.me/BiruhEthiopia/2262

  New and different things are being added to this Sabbath lesson, so it will be finished and delivered to you in the ne...
03/07/2024



New and different things are being added to this Sabbath lesson, so it will be finished and delivered to you in the next few days.

In this round, I will take some time to add something special, so please be patient for the next few days.

This is not to prevent you from buying Sabbath school, but to use it in addition to your purchase. It is also available for members who cannot afford it.

Stay TunedBiruh EthiopiaBiruh EthiopiaBiruh EthiopiaBiruh EthiopiaBiruh EthiopiaBiruh EthiopiaBiruh Ethiopia

አዘጋጅ : ቶማስ አር ሼፔርድትርጉም : ታምሬ ሻዕማሎይህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ የሚዘጋጀው በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መስሪያ ቤት በሆ...
27/06/2024

አዘጋጅ : ቶማስ አር ሼፔርድ
ትርጉም : ታምሬ ሻዕማሎ

ይህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ የሚዘጋጀው በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋና መስሪያ ቤት በሆነው በጄኔራል ኮንፍራንስ ውስጥ ሆኖ የጎልማሶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያን በሚያዘጋጀው ቢሮ ነው። መምሪያዎቹ የሚዘጋጁት የጄኔራል ኮንፍራንስ አስተዳደር ኮሚቴ ንዑስ ኮሚቴ በሆነውና የመጽሐፍ ቅዱስ መምሪያዎችን በሚያሳትመው የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድ ነው። የታተመው መምሪያ በውስጡ ዓለም አቀፋዊ የሆነ የምዘና ኮሚቴ ሀሳቦችንና የሰንበት ትምህርት ሕትመት ቦርድን ማረጋገጫ ስለሚያንጸባርቅ የአዘጋጁን (የአዘጋጆችን) ሀሳብ ብቻ የሚወክል አይደለም።

በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ማተሚያ ቤት ታተመ

3ኛ ሩብ ዓመት

ከሰኔ 22/2016 -- መስከረም 17/2017 ዓ.ም

የማርቆስ ወንጌል

ከማርቆስ መጽሐፍ ጅማሮ አንስቶ አንባቢው ኢየሱስ መሲህ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያውቃል (ማርቆስ 1፡1)። ነገር ግን በአጋንንት ከተያዙት ሰዎች በስተቀር በታሪኩ ውስጥ ያሉ ሰዎች እርሱ ማን እንደሆነ እና ለምን እንደመጣ ለመረዳት ተቸግረው ነበር። አጋንንት ግን እርሱ ማን እንደሆነ በትክክል አውቀው ነበር! አጋንንቶቹ አውቀውት ብርቱ በሆኑ ቃላቱ ፊት ጠወለጉ። ነገር ግን ይህንን መረጃ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው (አዘዛቸው)። ይህ ጉዳይ በምስጢር እንዲያዝ ለምን አዘዘ? የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች በየዘመናቱ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ሲያወጡና ሲያወርዱ ነበር። በትምህርታቸው ውስጥ መሲሃዊው ምስጢር የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ስለ ኢየሱስ ማንነት ዝም እንድንል ወንጌል የሚፈልገው ለምንድር ነው?

በማርቆስ ወንጌል የጥናት ጉዞ ላይ ግልጽ የሚሆን ነገር ካለ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ምስጢር ብቻ ሳይሆን አስደናቂ መገለጥም መኖሩ ነው። በትክክል መገለጥ/ የምስጢር ጭብጥ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ሲሆን በመጨረሻ ምሥጢራዊነቱ በሚያስደንቅ ሁኔታ አብቅቶ ኃይለኛ በሆነ የኢየሱስ መገለጥ የሚተካ ቢሆንም በማርቆስ ወንጌል ውስጥ በሙሉ ይታያል።

የማርቆስ መጽሐፍ በሁለት ተለይተው በሚታወቁ ክፍሎች ሊከፈል ይችላል። ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ የስምንተኛው ምዕራፍ ማብቂያ አከባቢ እስኪደርስ ድረስ ያለው ኢየሱስ ማን ነው? የሚለውን ወሳኝ ጥያቄ ይመልሳል።

መልሱ በትምህርቶቹና በተዓምራቶቹ ውስጥ እንዲታይ ተደርጓል። በተደጋጋሚ ክፉን አሸንፏል፣ ለተጨቆኑት ተስፋን አምጥቷል፣ ወደ ሰብአዊ ዘር የኑሮ እምብርት ዘልቀው የሚገቡ አሳማኝ እውነቶችን አስተምሯል፡ ይህ ሁሉ ለአንባቢው ኢየሱስ የዕብራውያን ሕዝብ ለረዥም ጊዜ ሲጠብቁት የነበረ መሲህ፣ ክርስቶስ መሆኑን ጮክ ብሎ ይናገራል። ነገር ግን አንድ በአጋንንት ያልተያዘ ሰው የመጽሐፉን አጋማሽ እስኪደርስና ከዚህም የተነሣ የመጽሐፉ የመጀመሪያው አጋማሽ ስለ ክርስቶስ ማንነት የሚያነሳውን ጥያቄ እስኪመልስ ድረስ እርሱ ማን እንደሆነ በትክክል መናገር አይችልም። “አንተ ክርስቶስ ነህ” ብሎ ያወጀው ያ ሰው ጴጥሮስ ነው(ማርቆስ 8:29)። የማርቆስ መጽሐፍ ሁለተኛው አጋማሽ ከማርቆስ 8፡31 እስከ መጽሐፉ መጨረሻ ያለው ክፍል ሲሆን ኢየሱስ ወዴት እየሄደ ነው? የሚለውን ሌላኛውን ጥያቄ ይመልሳል። መልሱ አስደንጋጭ ነው። በሮም ዓለም እጅግ አዋራጅና አሳፋሪ ወደ ሆነው ወደ መስቀል ሞት እየሄደ ነበር። ሮምን አሸንፎ እሥራኤልን ኃይለኛ ሕዝብ አድርጎ ይመሰርታል ብለው ለሚያስቡ ተከታዮቹ የመሲሁ መዳረሻ በፍጹም ያልተጠበቀ ነበር።

ግራ የተጋቡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እርሱ ይናገር የነበረውን ነገር መረዳት አልቻሉም ነበር። መጽሐፉ ወደ ፊት እየቀጠለ ሲሄድ ስለዚህ የሚያም ርዕስ ማንሳታቸው እየቀነሰ የሄደ ሲሆን በመጨረሻም በዚህ የማይወደድ እውነት ፊት ዝም ወደማለት ደርሰው ነበር።

ኢየሱስ ስርዓተ ቀብሩን ለመፈጸም የሚዶልቱ የኃይማኖት መሪዎችን ሲጋፈጣቸው ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተስፋ አስቆራጭ ይመስሉ ነበር። ባለግርማ የሆነ መንግሥትን ተስፋ ያደርጉ የነበሩ ደቀ መዛሙርት ከጠበቁት በተቃራኒ እርሱ ሲያዝ፣ ወደ ፍርድ ሲቀርብና ሲሰቀል እጅግ ደንግጠው ነበር።

ነገር ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ኢየሱስ ወዴት እየሄደ እንደሆነና እርሱ ሙቶ ከሙታን መነሳት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልጽና ዘለቄታ ያለው መልእክት እያስተላለፈ ነበር። የመጨረሻው እራት እንጀራና ጽዋ አካሉንና ደሙን የሚወክል ሲሆን (ማር. 14፡22-25) እርሱ ለብዙዎች ቤዛ ይሆናል (ማር. 10፡45)።

ይህ ማለት እርሱ ወደ መስቀል የሄደው ስቃዩን በማይገልጽ ጸጥታ ነው ማለት አይደለም። በጌተሰማኔ ከውሳኔው ጋር ትግል ያደረገ ሲሆን (ማርቆስ 14፡ 32-42) በመስቀል ላይ ተስፋ በመቁረጥ “ አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውከኝ?” ብሎ ጩኾአል (ማር. 15:34)። የማርቆስ ወንጌል ክርስቶስ የተለማመደውን ጨለማና ድነታችን ያስከፈለውን ዋጋ ያሳየናል። ነገር ግን መስቀል የጉዞው መጨረሻ አይደለም። ከትንሣኤው በኋላ በገሊላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት አቀደ። እንደምናውቀው ከዚህ የተነሣ የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ተጀመረ። ከወንጌል ጸሐፊው ከራሱ ምንም ተጨማሪ ሀሳብ ሳያካትት በአጭሩ እና ፈጣን እንቅስቃሴ በሚታይበት ዘይቤ የተነገረ እጅግ አስደናቂ ታሪክ ነው።

የናዝሬቱ ኢየሱስን ሕይወትና ሞት በተመለከተ ዝም ብሎ ታሪኩን በመንገር ቃላቶቹ፣ ሥራዎቹና ተግባሮቹ ለራሳቸው እንዲናገሩ ትቷል።

ቶማስ አር ሼፔርድ (ፒ ኤች ዲ) በአንድሪውስ ዩኒቨርሲቲ ባለው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሰሚናሪ ውስጥ የአዲስ ኪዳን አንጋፋ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው።

እሳቸውና ባለቤታቸው ሼሪ ሁለት ጎልማሳ ልጆችና ስድስት የልጅ ልጆች አሏቸው።

እግዚአብሔር በባሕሪው በምህረት የተሞላ አምላክ ነው፣ የእርሱ የሆኑትም በዚህ ባሕርይ ጥላ ሥር ናቸው፡፡ የአርሱ ልጆች ምህረትን ለማድረግ የሚቸገሩ አይደሉም፡፤ ምክንያቱም፣ የወረሱት ባሕርይ ...
06/02/2024

እግዚአብሔር በባሕሪው በምህረት የተሞላ አምላክ ነው፣ የእርሱ የሆኑትም በዚህ ባሕርይ ጥላ ሥር ናቸው፡፡ የአርሱ ልጆች ምህረትን ለማድረግ የሚቸገሩ አይደሉም፡፤ ምክንያቱም፣ የወረሱት ባሕርይ የአባታቸው ነው፡፡ አንድ አማኝ ምህረትን ለማድረግ እቸገራለሁ ካለ፣ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፡፡ ምህረትን የማድረግ ውጤቱም ከመልካም ነገር መጥገብ ይሆናል፡፡

“For the LORD God is a sun and shield: the LORD will give grace and glory: no good thing will he withhold from them that walk uprightly.”
— Psalms 84:11 (KJV)

SINQ

ሁሉን በፈጠረው በእግዚአብሔር ተወደናል ። እርሱ በግል ያውቀናል ፤ እርሱ ስለ እኛ እጅግ ያስባል ። ምንም እንኳን እግዚአብሔር ድካማችንንና ኃጢአታችንን ቢያውቅም እኛን ለማዳን መተኪያ የሌለ...
05/02/2024

ሁሉን በፈጠረው በእግዚአብሔር ተወደናል ። እርሱ በግል ያውቀናል ፤ እርሱ ስለ እኛ እጅግ ያስባል ። ምንም እንኳን እግዚአብሔር ድካማችንንና ኃጢአታችንን ቢያውቅም እኛን ለማዳን መተኪያ የሌለው ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ ነበር ። ይሁን እንጂ በድካምና በአመጸኝነት እየተመላለስን እንኳን እርሱ ይወደናል ፣ በኃጢአታችን ተናዘን እና ወደ እርሱ ከመጣንም ተመልሶ ይቀበለናል ፤ ይቅርም ይለናል ። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደዚህ በማያወላውል ፣ በታማኝነትና በጸጋው ከወደደን እንዴት እኛስ እርስ በርሳችን መዋደድ አይገባን ?

"Dear friends, since God so loved us, we also ought to love one another."
1 Jhon 4:11

Address

Irgalem

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MeshaStack posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share