Endalewgeta Magazine

Endalewgeta Magazine Disability is not an inability it is a different ability

15/07/2026
01/07/2026
01/07/2026
30/05/2026

ግንቦት 22/2028 ዓ.ም
ለተወደዳችሁና ለማከብራችሁ ውድ አፍሪካውያን ልጆቼ፡
ፈጣሪ በድንቅ አሠራሩ ውብና ድንቅ አድሮጎ የፈጠራችሁ የአምላክ የእጁ የስራ፡ የራዕዩ ማስፈፀሚያ፣ የቃል ኪዳኑ ማረፊያ እንደምን አደራችሁልኝ፡፡ እናንተ ታላቅ ሕዝብ ትሆኑ ዘንድ የተመረጣችሁ የአባቴ ብሩካን ይህንን ቀን እንድናይ እድል የሠንን ፈጣሪ እናመሠግነዋለን፡፡
የዛሬ መልዕክቴ ሁላችሁም አንድ ናችሁና አንድ ሁኑልኝ የሚል ነው፡፡
ውድ ልጆቼ፡ መልካችሁ፣ ቋንቋችሁ፣ አስተሳሰባችሁ፣ አመጋገባችሁ፣ አኗኗራችሁ፣ አጨዋወታችሁ ሌሎች ሌሎችም ሊለያዩ ይችላሉ፤ ነገርግን በፈጣሪ ሁላችሁም አንድ ናችሁ፡፡ በፈጣሪ ዘንድ ጥቁር የለም፣ ቀይ የለም፣ ረጅም የለም፣ አጭር የለም፣ ደሃም የለም፣ ሀብታም የለም ሁሉም በእርሱ ፊት አንድ ነው፡፡ የትኛውም ዘር፣ ጎሳ፣ ብሔር አባል ሁኑ እናንተ አንድ ናችሁ፡፡ መነሻችሁ አንድ ነው፡፡ ሐይማኖታችሁ የትኛውንም ይሁን የፈጠራችሁ አንድ ነው፡፡ መከፋፈላችሁ፣ እርስ በእርስ መለያየታችሁን ዛሬ አቁሙ፡፡ ሁላችሁም አንድ ናችሁ፡፡ ልዩነታችሁ፣ ውበታችሁ ነው፡፡ ነገር ግን አንድነታችሁ ጥንካሬያችሁ ነው፡፡ እባካችሁ አንድ ሁኑ! አንድ ስትሆኑ ትፈራላችሁ፣ አንድ ስትሆኑ በጋራ ትጀግናላችሁ፣ አንድ ስትሆኑ በጋራ ባለጠጎች ትሆናላችሁ፡፡ ድህነትን፣ ረሃብን፣ ጦርነትን ከምድራችን ታጠፋላችሁ፡፡ እባካችሁን አንድ ሁኑልኝ፡፡
እወዳችኃለው፡፡
አባታችሁ እንዳለውጌታ ነኝ
ካለሁበት

እውነት ነው "ተረጂነት ውርደት፤ ምርታማነት ክብር ነው።"
07/03/2026

እውነት ነው "ተረጂነት ውርደት፤ ምርታማነት ክብር ነው።"

የካቲት 23/2018 ዓ.ምእንዳለውጌታ የሕፃናት መንደር ከሆለታ ከተማ አረጋውያን ማህበርና ከአንበሳ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን 130ኛ የአደዋን በዓል ምክንያት በማድረግ ለ141 አረጋውያንና ...
02/03/2026

የካቲት 23/2018 ዓ.ም
እንዳለውጌታ የሕፃናት መንደር ከሆለታ ከተማ አረጋውያን ማህበርና ከአንበሳ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን 130ኛ የአደዋን በዓል ምክንያት በማድረግ ለ141 አረጋውያንና የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ግምቱ 352,500.00 የአይን መነፅር ድጋፍ አድርጓል።

23/02/2026

Address

Holeta

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Endalewgeta Magazine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share