18/08/2026
ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ወጣቶች ምክርቤት 2018 አፈጻጸም ግምገማና የክረምት ወረት ስራ አስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች ተገምግመዋል።
የውይይት መድርክ ንግግር ያደረገው አቶ ቶማስ ጫዊታ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፋ ኃለፍ ሲሆን እስከ አሁን የተሰሩ ስራዎች ሪፓርት ያቀረቡት ወጣት ወንዳቸው ወልደ የዞኑ ወጣቶች ምክር ቤት ፐረስዳንት አቅርቧል።
ወጣቶች ጉልበታቸውን አስተባብረው ማህበረሰቡን የሚደግፉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ማከናወናቸው ተገምግሟል።በክረምት ወራት ለታዳጊ ህፃናት እና ተማሪዎች የሚደረጉ የማጠናከሪያ ትምህርቶች እና የቁሳቁስ ድጋፎች አፈጻጸም ተቃኝቷል።
መድረኩን የመሩት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ወጣቶች ምክርቤት ፕረዚዳንት ወጣት ወንደቸው ተወልደና የዞኑ ምክርቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንት ወጣት ንጉሰ ከቻራ በጋራ የመሩት ስሆን ወጣቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በበጎ ፈቃድ እና በሀገራዊ የልማት ስራዎች ያላቸው ንቁ ተሳትፎ እና የፈጠራ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።
በዕቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመለየት ለቀጣይ ወራት የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
መድረኩም ስራውን በቅንጅት ለመፈፀምና እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ የዞን ምክርቤት አበላት ፣ የወረዳና የዳዬ ከተማ የወጣቶች ምክርቤት ፕረዚዳንት እና የወጣቶች ምክርቤት ስራ አፌፃምዮች ተሳትፈዋል።